Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ኮሚሽኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 02/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2016 በጀት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡

ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየሰራ ያለው ሥራ አበረታች መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አክለውም የኮሚሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች እያንዳንዱን ተግባራት በቁርጠኝነት በመምራታቸው የተሻለ ውጤት መምጣቱን ገልፀው፥ በቀጣይም የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ በበኩላቸው የሙስና መከላከልና የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግ ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሙስናና ብልሹ አሰራር የሰላምና ፀጥታ ፀር በመሆኑ ኮሚሽኑ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት ባለፉት 6 ወራት በርካታ ስራዎችን እንዳከናወነ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

በግምገማው ላይ የተገኙት የቋሚ ኮሚቴው አባላት ኮሚሽኑ ረጅም እድሜ ካላቸው ተቋማት በላይ ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ በቀጣይ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ምቹ የስራ ሁኔታን እንዲፈጠርና የሰው ሃይል እንዲያሟላ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በኮሚሽኑ ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ተግባራትን የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ ለቋሚ ኪሚቴው አባላት በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት መደረጉን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄዱ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ4/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለማዕከላዊ፣ ለምዕራብና ለሰሜን ጎንደር ዞን እንዲሁም ለጎንደር ከተማ ለወረዳና ለተቋማት የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች እንዲሁም ለአብክመ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለሙያዎች ሙያዊ ስልጠናና የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አደረገ።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡