Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
CORRUPTION PERCEPTION INDEX GLOBAL RANKING
አገልግሎትን በገንዘብ በመሸጥና ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ ተገለፀ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 01/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት ላይ የተሰማራ ህገ-ወጥ ደላላ፣ አንድ የሌላ ተቋም ሰራተኛ እንዲሁም ላልተገባ ግለሰብ በገንዘብ አገልግሎት የሰጠ የተቋሙን ሰራተኛ እና ተገልጋዮችን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ኤጀንሲው አሳውቋል።

የኤጀንሲው የሥነ-ምግባር እና ፀረ -ሙስና ዳይሬክቶሬት በዋና መስርያ ቤት ሰነድ ማረጋገጥ ማጣራት ሂደት የአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የስራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት ሰራተኛ የሆነ ተጠርጣሪ 30 ሺህ ብር በመቀበል፣ በወረዳ 5 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ እና የጋብቻ ሰርትፍኬት በማዘጋጀት፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የልደት ሰርተፍኬት እና የመሸኛ ማስረጃ /Clearance / በ10 ሺህ ብር ጉቦ በመቀበል ላይ የነበሩ ግለሰቦችን ከየክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች ጋር በተደረገ ኦፕሬሸን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

በተመሳሳይ ኤጀንሲው ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በደረሰው ጥቆማ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 4 እና አዲስ ከተማ ወረዳ 9 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ጽ/ቤት ሰራተኛ የሆኑ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ግለሰቦች የነዋሪነት መታወቂያ እና የልደት ማስረጃ በመስጠታቸው በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

ኤጀንሲው በመዋቅሩ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል በማድረግ ከሌብነት የፀዳ ተቋም ለመገንባት ጥረት እያደረገ ያለ ሲሆን፥ ህብረተሰቡ በተቋሙ ስም ከሚያጭበረብሩ ህገ-ወጥ ግለሰቦች እራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት እያስተላለፈ በተቋሙ ጥቂት ሰራተኞች የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ ተግባራት በቅንነት እና ታማኝነት ጥቆማ በማቅረብ አጋዥ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከባድ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ አራት ግለሰቦች በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 01/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ) ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከባድ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ አራት ግለሰቦች በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ።

ተከሳሶቹ 1ኛ አብዱልሰላም ራህመቶ፣ 2ኛ ሳራ በኃይሉ፣ 3ኛ ወንደሰን ፀጋዬ እና 4ኛ ረኢስ ሙህዲን የተባሉ ግለሰቦች ሲሆን፥ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) እና የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23(2)/ሀ/ እና የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 (በጉሙሩክ አዋጅ(ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀጽ 2(46) እንደተሻሻለው አንቀጽ 169(3) ስር የተደነገገውን ከባድ የሙስና እና የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀል በመተላለፋቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው 1ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነዶችን በመጠቀም የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ተወካይ ለግሪን ኢንተርናሽናል ሎጅስቲክስ አገልግሎት ስም የአውሮፕላን ማስጫኛ ሰነድ ቁጥር 071-41949935 የቢሮ ዕቃ በማስመሰል በህገ ወጥ መንገድ የመኪና መለዋወጫዎች፣ ሞባይሎች፣ ፍላሾችና ሚሞሪዋችን ህጋዊ አስመስለው በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-17640/21 የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት በመፈጸም ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባታቸው የታክስ መጠን ከ39.7 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት እንዳደረሱ የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

ዐቃቤ ሕግ ከአስር በላይ የሰው ምስክሮችን ቃል እና የሰነድ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾቹን ለፍርድ ቤት አቅርቧል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት 1ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው መቅረብ ባለመቻላቸው በሌሉበት ጉዳያቸው ታይቶ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

በዚህም መሰረት ተከሳሾችን ያርማል መሰል አጥፊዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ፍርድ ቤቱ 1ኛ ተከሳሽ በሀሰተኛ ሰነድ በመገልገሉና በጉሙሩክ ማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ 13 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራትና 110 ሺህ ብር፥ 3ኛ ተከሳሽ ደግሞ ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ወንጀል 5 ዓመት ፅኑ እስራትና 15 ሺህ ብር፣ 4ኛ ተከሳሽ 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በመተባበር ከባድ የሙስና ወንጀል በመፈጸሙ 8 ዓመት ከ3 ወር ፅኑ እስራትና 100 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ የተወሰነባቸው ሲሆን፥ 2ኛ ተከሳሽ ላይ ደግሞ በቀላል ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

ፍርድቤቱ 1ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾችን በተገኙበት አፈላልጎ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ትዕዛዝ መስጠቱን ከፌደራል ፖሊስ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
አራት ግለሰቦችን ያለ አግባብ በማሰር ገንዘብ እንዲከፍሉት አስገድዷል የተባለ የፖሊስ አባል በእስራት ተቀጣ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 01/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አራት ግለሰቦችን ያለ አግባብ በማሰር ገንዘብ እንዲከፍሉት አስገድዷል የተባለ የፖሊስ አባል በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ወሰነ።

የዞኑ ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ ረዳት ሳጅን ጌታቸው መኮንን በቅጽል ስሙ (ተረፈ) ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 423 የሙስና አዋጁን 881/2007 አንቀጽ 10 ንዑስ ቁጥር 1 እና አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላለፏል በማለት ተደራራቢ ክስ አቅርቦበታል።

ተከሳሹ ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረ ጃርሶ ወረዳ የፖሊስ አባል ሆኖ ሲሰራ በተለያየ ጊዜ አራት ግለሰቦችን ያለ አግባብ በማሰር ከ5 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መጠን ''ካልከፈላችሁ ከእስር አትፈቱም '' በማለት በማስፈራራት ከግለሰቦቹ 180 ሺህ ብር መቀበሉን ጠቅሶ ዐቃቤ ህግ በክሱ ዝርዝር ላይ አስፍሯል።

ተከሳሹ የቀረበበት ክስ ዝርዝር በችሎት ከደረሰው በኋላ ወንጀሉን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የሰጠውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ህግ የግል ተበዳዮቹን ጨምሮ የተለያዩ የሰው ምስክሮች እና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦበታል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ህግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ እንዲከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል አለመቻሉ ተጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ህግን የቅጣት ማክበጃ አስተያየትና የተከሳሹን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት መርምሮ ተከሳሹንም ሆነ ሌሎችን ያስተምራል በሚል በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በኮሚሽኑ የሚዘጋጀው የጥር ወር 19ኛ ዕትም ዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ

****

የዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ ሙሉ መረጃን ለማግኘት ሊንኩን ያስፈጥሩ...https://drive.google.com/file/d/11Mji1lg1H1bYuWcDMyPbRsS7yeCyZKTu/view?usp=drivesdk
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 02/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2016 በጀት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡

ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየሰራ ያለው ሥራ አበረታች መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አክለውም የኮሚሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች እያንዳንዱን ተግባራት በቁርጠኝነት በመምራታቸው የተሻለ ውጤት መምጣቱን ገልፀው፥ በቀጣይም የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ በበኩላቸው የሙስና መከላከልና የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግ ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሙስናና ብልሹ አሰራር የሰላምና ፀጥታ ፀር በመሆኑ ኮሚሽኑ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት ባለፉት 6 ወራት በርካታ ስራዎችን እንዳከናወነ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

በግምገማው ላይ የተገኙት የቋሚ ኮሚቴው አባላት ኮሚሽኑ ረጅም እድሜ ካላቸው ተቋማት በላይ ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ በቀጣይ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ምቹ የስራ ሁኔታን እንዲፈጠርና የሰው ሃይል እንዲያሟላ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በኮሚሽኑ ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ተግባራትን የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ ለቋሚ ኪሚቴው አባላት በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት መደረጉን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡