Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
መልካም ሥነምግባር ያለውና ሙስናን የሚፀየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሃይማኖት አባቶች በማስተማርም ሆነ በግል ህይወታቸው አርአያ መሆን እንዳለባቸው ተገለፀ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 28/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ) የአዲስ አበባ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሃይማኖት አባቶችና መምህራን ጋር በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ላይ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ እንደገለፁት ሀገራችን ኢትዮጵያ የአማኞች ሀገር በመሆኗ የሃይማኖት ተቋማት፣ አባቶችና መምህራን የሚያስተምሩት አስተምህሮ ታማኝነትን፣ ርህራሄን፣ ትዕግስትን፣ አብሮነትን፣ ደግነትን እና ይቅርታን የተላበሰ መሆን አለበት ብለዋል።

የሙስና እና ብልሹ አሰራር ችግሮች መነሻቸው የአስተሳሰብ ጉደለት ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፥ የሃይማኖት አባቶች እሴቶች ለማስረፅ ጠንካራ ስራ መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ በበኩላቸው የሃይማኖት ተቋማት ማህበራዊ ትስስርን፣ አብሮነትንና በጎነትን የሚያጠናክሩ እሴቶችን የሚሰብኩ መሆን እንዳለባቸው ገልፀው፥ ማህበረሰቡ ጠንካራ የሥነምግባር እሴቶች እንዲላበስና ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ጭምር ሥነምግባራዊና ከጥላቻ የራቁ ንግግሮችን እንዲያደርጉ እና መልካም ውሳኔዎችን እንዲወስኑ የሚያስችሉ መሆን አለባቸው ብለዋል።

በሥነምግባራቸው ተምሳሌት የሆኑ የሃይማኖት አባቶችና መምህራን በመልካም ባህሪ የታነፀ ትውልድ ለመፍጠር ያላቸው ሚና የላቀ መሆኑን አመላክተዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የሃይማኖት አባቶችና መምህራን በሥነምግባር የታነፀና ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሚናቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል። አክለውም መንግስት ለሌብነትና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን ተከታትሎ በማረም እና ተጠያቂነትን በማጠናከር የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

"የሃይማኖት ተቋማት መልካም ባህሪ ያለውና ሙስና የሚፀየፍ ትውልድ ከመገንባት አንፃር ያላቸው ሚና" የሚል የመወያያ ሰነድ በኮሚሽኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ ቀርቦ ውይይት መካሄዱን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ለኮሚሽኑ  የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው ሥልጣና ተጠናቀቀ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ  ጥር 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ) ለፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ሥልጠናው "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ሀሳብ እንደ ሀገር እየተሰጠ ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን በዕለቱም ‹‹በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የመንግስት ሰራተኛው ሚና›› በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

በመድረኩ ከቀረበው ሰነድ በመነሳት ጥያቄዎችና ሀሳቦች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ለቀረቡ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ማብራሪያና ምላሽ የሰጡት የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው ለሁሉም እኩል የሆነ አገልገሎት መስጠት የሚያስችል የዘመነ ሲቭል ሰርቪስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ወዶ አጦ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ተስፋ ያላት ሀገር እንደመሆኗ አጀንዳዎችን አስተሳስረን በአንድ ዓላማ ወደፊት መራመድ አለብን ብለዋል፡፡ እንደ ሀገር ተግዳሮቶች ቢኖሩም ተግዳሮቶችን በጋራ እየፈታን ከዕዳ ወደ ምንዳ መሄድ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) እንደ ሀገር የተሰጠውን ተልዕኮ ሰርቶ ማሳየት የሚችልና ነጻ፣ ገለልተኛና አካታች የሆነ ሲቪል ሰርቫንት በመያዝ ሀገርን ወደፊት ማራመድ የሚችል ሥራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በሲቭል ሰርቪሱ የተቀመጡ 8 የትኩረት አቅጣጫዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም ዝግጁ መሆን ይገባዋል፡፡ ለዚህም ደግሞ ሰራተኛው ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን እራሱን መፈተሽ አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ ከዕዳ ወደ ምንዳ በሚል ርዕስ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መንግስተና ህዝብ በጋራ አጀንዳዎች ዙሪያ እንዲወያይና ከምንም በላይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስቀደም ላይ አብሮ ለመስራት ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ በማጠቃለያቸው እንደ ሀገር ያለንን ሀብት በማወቅ፣ ሀብት በመፍጠርና  ሌብነትን በማስወገድ ሀገረ መንግስቱን እናጽና ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡  

ከሥልጠናው ጎን ለጎን ለኢትዮጵያ ደም ባንክ አገልግሎት በኮሚሽኑ  የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የደም ልገሳ የተደረገ ሲሆን በኢትዮጵያ ደም የሚያስፈልጋቸው ብዙ እናቶች እና ህጻናት እንዳሉና ለዚህም ሁላችንም የምንችለውን ማድረግ እንዳለብን ከአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የመጡ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ህገ ወጥ የመሬት ወረራ እና ግንባታን እንዲሁም ሙስናን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ) ህገ ወጥ የመሬት ወረራ እና ግንባታን እንዲሁም ሙስናን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን የከተማ ልማት እና ኮንስራክሽን ቢሮ የ2016 አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡

የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡትን የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ አሚና አብዱከሪም ባለፉት ስድስት ወራት በተለይ ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራን በመከላከል ረገድ ሰፊ ስራዎች መስራታቸውን ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል 16 ፕሮጀክቶችን ስራ ማስጀመር መቻሉን ጠቁመው ኪራይ ሰብሳቢነት ላይ እርምጃ በመውሰድ ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በተሰራው ስራ የተሻለ ለውጥ መመዝገቡን ባቀረቡት ሪፖርት አመላክተዋል፡፡

ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት የግንባታ እቃዎች ዋጋ መጨመር፣ አስፈላጊ ግብዓቶች አለመሟላትና መዝገቦች በጊዜ አለመቅረብ፣ የተሽከርካሪ እጥረት እና የበጀት ችግር ምክኒያት ተግባራትን በሚገባው ልክ እንዳይሰራ እንቅፋት መሆኑን ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡

ህገ ወጥ የመሬት ወረራ እና ግንባታን እንዲሁም ሙስናን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እና ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው መግለፃቸውን ከሀረሪ ማስሚዲያ ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጅብሪል መሀመድ በሰጡት አቅጣጫ የተጀመሩ ስራዎች የተሻሉ ቢሆኑም ህገ ወጥ ግንባታና መሬት ወረራን መከላከል የከተማ ልማት ዘርፍ ስራዎችን የሚያግዝ በመሆኑ አሁንም በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ለህብረተሰቡ ተገቢ አገልግሎት ከመስጠት ጋር ተያይዞ ቢሮው ክፍተቶችን አርሞ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡