Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ለሚኒስቴር መ/ቤቱና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች ሥነምግባራዊ አመራርን የተመለከተ ስልጠና እየተሰጠ ነው

********

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 27/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሥነምግባራዊ አመራርን የተመለከተ ስልጠና ቡድን መሪ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ለከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች እየተሰጠ ነው፡፡

የፌዴራል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሥነምግባር መከታተያ ስራ አስፈጻሚ ጋር በመተባበር ለመስሪያ ቤቱ እና ለተጠሪ ተቋማት በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች ሥነምግባራዊ አመራርን ለመፍጠር የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና በአለም ገና ከተማ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በምህንድስና የስልጠና ማዕከል እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የስልጠናው ዓላማ በዘርፉ ለሚሰሩ ተግባራት ሥነምግባራዊ አመራርን በማጎልበት ከሙስና እና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አመራርን እንዲከተሉ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ነው፡፡

የስልጠናውን መድረክ በንግግር ያስጀመሩት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ወንድሙ ሴታ(ኢንጂነር) እንደገለፁት የሥነምግባራዊ አመራር ጽንሰ ሀሳብን በመረዳት እና በተቋማችን ለማስተግበር ዘርፉ ሰፊ ሀብትና አገልገሎት የሚሰጥበት በመሆኑ የተመደበለትን ሀብት ለታለመለት ዓላማ ለማዋል ያለንን ግንዛቤ ለማዳበር ይረዳል ብለዋል፡፡

አያይዘውም በኮንስትራክሽን እና በመሠረተ ልማት ዘርፍ በጣም ብዙ አገልግሎቶች የሚሰጡበት በመሆኑ የህዝባችንን ጥያቄ ለመመለስ፣ የተጣሉብንን ሀላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት፣ በተቋማችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እና የመንግስትን ሀብት ለተገቢው አገልግሎት ለማዋል ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል በተግባር ላይ ማዋል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ስልጠና ክፍል ዴስክ ሀላፊ የሆኑት አቶ አንተነህ ኃይሌ በሥነምግባራዊ አመራር ጽንሰ ሀሳብ፣ አስፈላጊነት፣ ክህሎቶች እና መርሆዎች ላይ ገለጻ ሲያደርጉ እንደተናገሩት በተቋማቶች ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል አመራሮች ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ገልፀው፥ የከተማና መሠረተ ልማት ዘርፍ ለሀገር እድገትና ልማት ቁልፍ የሆነና ከፍተኛ የሀገር ሀብት የሚፍስበት እንደመሆኑ መጠን ሥነምግባራዊ አመራር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ስራን በእውቀትና በብልሃት መስራት የሚችል፣ ሰራተኛውን ግንባር ቀደም ተሳታፊ የሚያደርግ፣ የሰራተኛውን ችግር የሚያውቅና መፍትሔ የሚሰጥ፣ ውሳኔን በወቅቱ መስጠት የሚችልና ሙስና የሚፈጠርባቸው ቦታዎች ላይ አጥብቆ የሚመራ መሪ ያስፈልጋል ሲሉ ለተሳታፊ አመራሮች መግለፃቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች "ከዕዳ ወደ ምንዳ " በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 28/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ሀገርን ወደ ላቀ የእድገት ደረጃ ለማሻገር በሚያስችሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአመራሮች እና ሰራተኞች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

"ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ እንደ ሀገር እየተደረገ ያለዉን ውይይት ዓላማው የመንግሥት ሰራተኛውን ከእዳ ወደ ምንዳ ለመሸጋገር የሚያስችሉ ወቅታዊ፣ ሀገራዊ፣ ህዝባዊ እና መንግስታዊ አጀንዳዎች ላይ በመወያየትና በመመካከር የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠር ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ማስቻልና የሀገራችንን አንድነት ለማስቀጠልና ህዝባችንን ወደ ላቀ የእድገት ደረጃ ለማሻገር ያለመ ነዉ ተብሏል።

በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋዉ እንደገለፁት የስልጠናው ዓላማ የመንግሥት ሰራተኛዉ የመንግሥት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን አዉቆ ስራውን እንዲሰራ ለማስቻል ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ሰፊ ታሪክ ያላት ሀገር ናት ያሉት ኮሚሽነሩ ሰላምን በማምጣት፣ በቂ ሀብትን በመፍጠርና ያለዉን ሀብት በወጉ በማስተዳደር ወደፊት መራመድ ይገባል ብለዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም ውይይቱ መልካም ነገሮችን ወደፊት በማምጣት የጋራ የሆነች ኢትዮጵያን መገንባት የሚያስችል ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በመድረኩ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከሰራተኞች እና አመራሮች ጥያቄዎችና ሀሳቦች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ተገኝተው ለተነሱ ጥያቄችና ሀሳቦች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) እንደ ሀገር ያለንን ሀብት አውቀን ሰላምን በጋራ በማስፈን በቁጭት መስራት አለብን ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም የልማት ሥራዎችን ሲሰሩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ተግዳሮቶችን ወደ እድል እየቀየርን መስራት አለብን፥ ይህንን ማድረግ ደግሞ የሁሉም ሀላፊነት ነው ብለዋል፡፡

የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ብዙ ሀብት ያላትና ሀብቷን አውቀን በጋራ ከሰራን ለነገ ብዙ ተስፋ ያላት ሀገር ናት ብለዋል፡፡

እንደ እኛ ተቋም የሥነምግር ብልሹነትን በማረም እና ሙስናን በመከላከል ሀብት እንዳይመዘበር በጋራ መስራት አለብን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ውይይቱ በሁለት ምዕራፎችና በአራት ርዕሶች ተከፍሎ እየተሰጠ ሲሆን፥ ነገም የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡