Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ተማሪዎች በትምህርት ውጤታቸው ብቻ ሳይሆን በሥነምግባራቸውም አርአያ መሆን እንዳለባቸው ተገለፀ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 25/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሥነምግባራቸው ተምሳሌት በመሆን ውጤታማ ለሆኑ ተማሪዎች የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ባሉበት የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አካሄደ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ መሆን እንዳለባቸው ሁሉ በሥነምግባራቸውም አርአያ መሆን ይኖርባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለው ከማህበረሰቡ እሴቶች ውጭ የሆኑ መጥፎ ባህሪያትን ባለመከተል ሌብነትንና ብልሹ አሰራሮችን የሚፀየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሰላም፣ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የሚቻለው በሥነምግባራቸው ምስጉን የሆኑ ተማሪዎችን ማፍራት ሲቻል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አቶ ሙሉነህ አክለው ሥነምግባር የሁሉም ነገር መለኪያ በመሆኑ ኮሚሽኑ በትምህርት ተቋማት ላይ እየሰራ ያለው ተግባር የሚበረታታ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው አለምዓቀፍ ተወዳዳሪ፣ የነቃና የበቃ ትውልድ ለመገንባት ተማሪወችን በሥነምግባራቸው አርአያ እንዲሆኑ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የተማሪዎች ሥነምግባር ይመለከተኛል በሚል ኮሚሽኑ ለሌሎች ምሳሌና ተምሳሌት የሆኑ ተማሪዎችን የማበረታቻ ሽልማት መስጠቱ እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አቶ አሰፋ ቶላ እንደገለፁት በሥነምግባራቸው የታነፁ ተማሪዎችን ስናመሰግን የታማኝነትና የሥነምግባር ባህልን ለማዳበር ኮሚሽኑ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልፀው፥ ዛሬ የተመሰገኑ ተማሪዎች ሽልማት ተቀባይ ብቻ ሳይሆኑ ለሌሎች ተማሪዎችም መነሳሳትን የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል፡፡

ሙስናን ለመዋጋትና ፍትሃዊ የሆነ ማህበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል ጥንካሬና ድፍረት ያላቸው በሥነምግባራቸው የተሻሉ ተማሪዎችን ሁልግዜም ሊከበሩ ይገባል ሲሉ ም/ኮሚሽነሩ አሳስበዋል፡፡

እውቅናና ሽልማት የተበረከተላቸው ተማሪወችም ለዚህ እድል በመመረጣቸው ኮሚሽኑን አመስግነው፣ በቀጣይም ምስጉን የሆኑ ተማሪዎችን ለማበራከት በሚሰሩ ስራዎች ሚናቸውን እንደሚወጡ መናገራቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሸገር ከተማ “የሥነ-ምህዳር አወቃቀር እንቀይራለን” በሚል ከግለሰቦች ገንዘብ የተቀበሉ ተከሳሾች እስከ 20 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 27/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሸገር ከተማ “የሥነ-ምህዳር አወቃቀር እንቀይራለን’’ በማለት በማጭበርበር ገንዘብ ከግለሰቦች የተቀበሉ ተከሳሾች እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ።

የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹም፥ 1ኛ ደረጄ ካሳዬ ኢፋ፣ 2ኛ አቡና አያና ገመቹ፣ 3ኛ ሹሚ መስቀል ገዳ፣ 4ኛአለማየሁ ገዛኸኝ ደምስ፣ 5ኛ ጉታ ጫካ ሁንዴ እና 6ኛ ደበላ ረጋሳ ፉፋ ናቸው።

የኦሮሚያ ፍትሕ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቢ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ እና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር881/2007 አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል በማለት በሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ተደራራቢ ክስ አቅርቦባቸዋል።

በቀረበው ክስ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሾቹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በ2014 ዓ.ም በተለያዩ ጊዜያት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የአካባቢውን ሥነ-ምህዳር አወቃቀር ለመቀየር ከባለስልጣናት እንደታዘዙ በማስመሰል ማህበር በማደራጀት ‘‘መሬት ሸንሽነን እናከፋፍላለን’’ የሚሉ ሀሰተኛ የማግባቢያ ቃላት መጠቀማቸው በክሱ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።

እንደአጠቃላይ በማህበር ላደራጇቸው የተለያዩ ግለሰቦች ለእያንዳንዳቸው ‘‘200 ካሬ ሜትር ይዞታ ሸንሽነን እንሰጣለን’’ በማለት ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ከግለሰቦች በመቀበል የመንግስት ይዞታ የሆነውን 3 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታ ሸንሽነው ሲያከፋፍሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቀሰው ዐቃቤ ሕግ የተከሳሾቹን የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ደረጃ በመጥቀስ ዝርዝር ክስ አቅርቦባቸዋል።

ተከሳሾቹ የቀረበባቸው ክስ በችሎት እንዲደርሳቸው ከተደረገ በኃላ የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ማረጋገጡን በመግለጽ ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ድንጋጌ እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሾቹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን ማስተባበል ባለመቻላቸው የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ አስተያየትንና የተከሳሾቹን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመያዝ 1ኛ ተከሳሽን በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

2ኛ ተከሳሽን በሚመለከት በ16 ዓመት ከ6 ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነው ፍርድ ቤቱ ፤ ከ3ኛ እስከ 6ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾችን ደግሞ እያንዳንዳቸውን በ20 ዓመት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን ፋና ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡