ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል በተባሉ ግለሰቦች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈ
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 24/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የጉምሩክ ሥርዓት ባልተፈፀመባቸው ተሽከርካሪዎች ሐሰተኛ ሊብሬና ታርጋ በማውጣት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል በተባሉ ግለሰቦች ላይ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላለፈ።
ተከሳሾቹ የክልሉ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሰበታ ቅርንጫፍ ሠራተኛ የነበሩት ለሚ በየነ እና ያይላል ንጋቱ እንዲሁም በግል ሥራ የሚተዳደሩት መሪማ ጀማል፣ ጌታቸው ንጉሴ እና ቃልኪዳን አሰፋ ናቸው።
በተከሳሾቹ ላይ የኦሮሚያ ክልል የፍትሕ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ክሶችን አቅርቦባቸው ነበር።
ክሱም÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 እና አንቀጽ 33 እና የሙስና አዋጅ 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2፣ አንቀጽ 33 እና የጉምሩክ አዋጅን አንቀጽ 167 ንዑስ ቁጥር 1፣ አንቀጽ 168 ንዑስ ቁጥር 1 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና ንዑስ ቁጥር 2 (ለ) ሥር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ነው።
1ኛና 2ኛ ተከሳሾች በ2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሰበታ ቅርንጫፍ ባለሙያነት ሲሠሩ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር ከተጠቀሱ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ከሕግና አሠራር ውጪ የጉምሩክ ሥርዓት ያልተፈጸመባቸው በአካል ባልቀረቡ ሦስት የV8 ተሽከርካሪዎች የታርጋ ቁጥር፣ ሊብሬና ቦሎ የተለያዩ የማረጋገጫ ሠነዶች እንዲወጣላቸው ማድረጋቸውን ዐቃቤ ሕግ በክሱ አመላክቷል።
ጌታቸው ንጉሴና ቃልኪዳን አሰፋ የተባሉ ተከሳሾች ደግሞ የጉምሩክ ሥርዓት ያልተፈጸሙባቸው በተጠቀሱና ከሰበታ ቅርንጫፍ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ በሕገ ወጥ መንገድ የወሰዱትን የተሽከርካሪ የማረጋገጫ ሠነዶች ለባንክ በማቅረብ 26 ሚሊየን ብር ብድር መውሰዳቸው በክሱ ተጠቅሷል፡፡
ግለሰቦቹ ፈጽመዋል በተባለው ሕገ-ወጥ ተግባር በመንግሥት ላይ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው በዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ክሶች ተመስርቶባቸው ነበር።
ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ከደረሳቸውና በንባብ ከተሰማ በኋላ ወንጀሉን አልፈጸምንም በማለት የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ስድስት የሰው ምስክር ቃልና የተለያየ የሠነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ ማቅረቡን ፋና ዘግቧል።
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾቹ በተከሰሱባቸው ድንጋጌዎች እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ቢሆንም÷ ተከሳሾቹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መንገድ መከላከል ባለመቻላቸው ተከላከሉ በተባሉበት ድንጋጌ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ከ13 ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ሃብታቸውን ማስመዝገባቸው ተገለጸ
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 24/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደብረብርሃን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሙስናን ለመከላከል በተሠራው ሥራ ከ13 ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ማስቻሉን ገልጿል።
የአማራ ክልል መንግሥት ለሙስና ተጋላጭ የኾኑ የሥራ መስኮችን በመለየት የሃብት ምዝገባ እንዲካሄድ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሠራሩ ግለጽነት እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለማስቻል ታሳቢ ተደርጎ የመንግሥት ሠራተኞች የሃብት ምዝገባ እንዲካሄድ በአዋጅ ቁጥር 187/2003 ወሳኔ በማሳለፍ ወደ ሥራ ከገባ ዓመታት ተቆጥረዋል።
በአማራ ክልል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የደብረብርሃን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሃብት ማሳወቅ እና ማስመዝገብ ቡድን መሪ ራሄል ወርቁ የመንግሥት ተሿሚዎች፣ ተመራጮች እና የመንግሥት ሠራተኞች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ የወጣዉ አዋጅ ያስገድዳል ብለዋል።
ሃብት እንዲያስመዘግቡ ተጠይቀው ኾን ብለው የማያስመዘግቡ ግለሰቦች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው 1 ሺህ ብር በመክፍል ሃብት እንዲያስመዘግቡ አሊያም እንደ ሙስና ተጋላጭነታቸው ክብደት እና ቅለት ታይቶ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ አዋጁ እንደሚያስገድድም ነው ያስገነዘቡት።
የሃብት ማስመዝገብ ሂደቱ በየሁለት ዓመት ተኩል እንደሚታደስ ያነሱት ቡድን መሪዋ፥ የሙስና ወንጀል ሲፈጸም ዜጎች በስልክ ቁጥር 011 637 59 64 በመደወል አለያም በሰሜን ሸዋ ዞን አሥተዳደር በደብረብርሃን ከተማ ባለው መሥሪያ ቤት በአካል በመገኘት ጥቆማ መስጠት እንደሚቻልም ማሳሰባቸውን አሚኮ ዘግቧል።