Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
በሥነምግባር የታነፀና የህብረተሰብ ጥቅም የሚያከብር ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን "በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና ፀረ-ሙስና ጉዳዮች" ትኩረት አድርገው በተዘጋጁ የስልጠና ሞጁሎች ላይ ማረጋገጫ አውደ ጥናት አካሄደ፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ እንደገለፁት ለሀገር ዕድገትና ለልማት ፀር የሆነውን ሙስናን ለመዋጋት የዜጎችን ሥነምግባር መገንባት ይገባል ብለዋል፡፡

አክለውም በሥነምግባር የታነፀና የህብረተሰቡን ጥቅም የሚያከብር ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ በበኩላቸው የአውደ ጥናቱ ዓላማ የትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስናን በመለየት ለመከላከልና ለመፍታት የሚያስችል ዕውቀትና ክህሎት ለማስታጠቅ የተዘጋጀውን የስልጠና ሞጁሎች ለማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡

የፀረ-ሙስና ትግል የግለሰብ ብቻ ሳይሆን የጋራ ኃላፊነት ጭምር መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ በዚህ አውደ ጥናት ለራሳችን እና ለመጪው ትውልድ የተሻለ ሁኔታ ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት ለማሳየትና የስልጠና ሞጁሎቹን ለማዳበር በቂ አስተያየት መስጠት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ በሥነምግባርና መልካም አስተዳደር፣ የሙስና ጽንሰ ሀሳብ እና የመከላከል ስልቶች፣ የሃብት ማሳወቅ እና ማስመዝገብ ስርዓት፣ ሙስናና የመንግስት ግዢ፣ የሙስና ወንጀል ምርመራ፣ የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር፣ የሙስና ወንጀል በጠቅላላው፣ የፖሊስና ዓቃቢ ህግ የሙያ ሥነምግባር፣ የሙስና ስጋት ዳሰሳ ጥናት እና ሥነምግባራዊ አመራር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማዘጋጀት ወንጀል የተከሰሰው የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኛ በእስራት ተቀጣ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን በማዘጋጀት ወንጀል የተከሰሰው የሻንቡ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኛ በ8 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ውሳኔ አሳለፈ።

የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ የሙስና አዋጅ 881/2007 ድንጋጌን መተላለፉን ጠቅሶ ሶሬሳ አፋታ ላይ ክስ መስርቶበታል።

ተከሳሹ በጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሻንቡ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የተማሪዎች ምዝገባ ኦፊሰር ሆኖ ሲሰራ በተቋሙ አመራሮች ፊርማ የተዘጋጀ የሚመስል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችና የሙያ ማረጋገጪያ ምስክር ወረቀቶችን በ34 ግለሰቦች ስም አዘጋጅቶ የተገኘ መሆኑ በክሱ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።

በዚህ መልኩ የቀረበበት ክስ ለተከሳሹ እንዲደርስ ከተደረገ በኋላ ተከሳሹ ወንጀሉን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰውና የሰነድ ማስረጃን መርምሮ በተከሰሰበት ድንጋጌ እንዲከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሹ መከላከል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን ከመረመረ በኋላ ተከሳሹን ጥፋተኛ በተባለበት ድንጋጌ በ8 ዓመት ከ5 ወራት ጽኑ እስራትና በ1 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጣ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዙሪያ የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር የተደረገ ቆይታ

***************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በልጆች ሥነምግባር ግንባታ የቤተሰብ ሚና (ክፍል ሶስት)

***************

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በበይነመረብ አማካኝነት የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ክህሎት ሥልጠና እና ግንዛቤ ማጎልበቻ ፕሮግራም ሥራዎችን እያቀረበ ሲሆን ‹‹ለልጆች የሥነምግባር ግንባታ የቤተሰብ ሚና›› በሚል ርዕስ ክፍል ሶስት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የዜጎችን የፍትህ ፍላጎት በማርካት በፍትህ በሥርዓቱ ላይ ያለውን ዕምነት ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቆመ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ክቡር ጌዲዮና ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል።

የፍትህ ሥርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግና በቴክኖሎጂ ለማገዝ ምን ጥረት እየተደረገ ይገኛል፣ ለጠቋሚዎችና ለምስክሮች እየተሰጠ የሚገኝ የህግ ከለላ ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ እና ሌሎችም ጥያቄዎች ከምክር ቤቱ አባላትና ከህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ተነስተዋል፡፡

ከህዝብና ከመንግስት የተመዘበሩና ወደ ሌሎች አገራት የሸሹ ሀብቶችን ለማስመለስ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ምን ይመስላሉ፣ ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓትን ወጥነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ምን ታስቧል፣ ለታራሚዎች የሚሰጥ ምህረት ለብልሹ አሰራር ተጋልጧል፣ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያለው የመሰረታዊ አገልግሎት አቅርቦት ችግር አለባቸው የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡

ለተነሱ ጥያቄዎች የፍትህ ሚንስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል። ዘርፉን በቴክኖሎጂ ከማዘመን አንፃር የሰነዶችን ምዝገባና ማረጋገጥ ፋይሎችን ማደራጀትን ክፍያዎችን የመፈፀም አገልግሎቶች መጀመራቸውን የገለፁት ሚንስትሩ፥ ፋይሎችን የፍትህ ሂደት መከታተያ ዘዴዎች በመበልፀግ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ወደ ውጪ አገራት የአገር ሃብትን ይዘው የሚኮበልሉ ተጠርጣሪዎችን በብዛት የሚኮበሉልባቸውን አገራት በመለየት ከሀገራቱ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የማዕቀፍ ስምምነቶች እየተፈፀሙ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን፥ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስና ደቡብ አፍሪካ እንደሚገኙበት ጠቁመዋል፡፡

የኦዲት ግኝት ያለባቸውን ተቋማት ተጠያቂ ለማድርግ በዘርፉ ዕውቅና እና ልምድ ያለው የሰው ሃይል ዕጥረት መኖሩን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፥ ለምስክሮችና ለጠቋሚዎች ከሚሰጥ የህግ ከለላ አንጻር አገራችን የህግ ክፍተት ባይኖርባትም የሃብት ዕጥረት መኖሩ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም ብለዋል፡፡

የባህላዊ ፍትህ ሥርዓቱን ለመጠቀም ከየክልሎቹ ባህልና ዕሴት ጋር የተስማማ የፍትህ ሥርዓት ረቂቅ ሞዴል ተዘጋጅቶ ከክልሎች ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጠም ወደ ስራ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንሚገኝ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ዕፀገነት መንግስቱ በበኩላቸው የፍትህ ሚኒስቴር ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር ለእንግልት በሚዳርጉ ህገ ወጥ ደላሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ለሌሎች አስተማሪ መሆን ይገባዋል ብለዋል። ለታራሚዎች ምህረት የሚሰጥባቸው ዕድሎችን አሰራሮችን ግልፅ ማድረግ እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ አሳስበዋል፡፡

የማህበረሰቡን የፍትህ ፍላጎት ለማርካትና በሥርዓቱ ላይ ያለውን ዕምነት ማሳደግ እንደሚገባ የተከበሩ ወ/ሮ ዕፀገነት የጠቆሙ ሲሆን፤ አቅም ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጠው ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎትም በስፋት ተደራሽ ሊደረግ እንደሚገባው መግለፃቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ከ1 ሚሊዮን ብር በላይና የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ በመኖሪያ ቤቱ በህገ ወጥ መንገድ አከማችቶ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ1 ሚሊየን ብር በላይና በርካታ ዶላርና የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ በመኖሪያ ቤቱ በህገ ወጥ መንገድ አከማችቶ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ለመቆጣጠር እያደረገ ያለውን ክትትል አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ነዋሪነቱ በክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ያከማቸ መሆኑን ባሰባሰበው መረጃ ማረጋገጡን ተከትሎ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትእዛዝ በማውጣት በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት ጥር 23 ቀን 2016 ዓ/ም ባደረገው ብርበራ 1ሚሊዮን 199ሺህ 290 ብር ፣ 26ሺህ 405 የአሜሪካ ዶላር ፣ 5ሺህ 100 የካናዳ ዶላር ፣ 34 ሺህ 150 ዮሮ እና 1ሺህ 635 የሳውዲ ሪያል እና 27 ጥይት በኤግዚቢትነት ይዟል፡፡

ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ እና ለወንጀል መፈፀም መንስኤ በመሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ክትትሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡም በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን በመጠቆም እና መረጃ በመስጠት ለፖሊስ ተባባሪ መሆን እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።