Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
የሥነ-ምግባር ጥሰት ፈጽመዋል በተባሉ አመራር እና ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ አሌክትሪክ አገልግሎት የሥነ-ምግባር ጥሰት ፈጽመዋል በተባሉ አመራር እና ሰራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰዱን አስታወቀ።

አገልግሎቱ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ የተጠያቂነት ስርዓትን ለማስፈን ባከናወነው ስራ እርምጃው መወሰዱን ነው የገለጸው።

ተቋሙ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ከደንበኞች ከቀረቡለት 63 ጥቆማዎች ውስጥ የማጣርት ስራ በማከናወን፤ በ23 አመራር እና ሰራተኞች ላይ ላይ ከጹሑፍ ማስጠንቂያ እስከ ስንብት የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰዱን አስታውቋል።

በተጨማሪም በተቋሙ በውስጥ የሥነምግባር ችግር በታየባቸው 409 ሰራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንደወሰደም ገልጿል።

በዚህም በ106 ሰራተኞች ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ በ282 ሰራተኞች ላይ የደመወዝ ቅጣት፣ በ11 ሰራተኞች ላይ ስንብት እንዲሁም በ10 ሰራተኞች ላይ ባደረገው ማጣራት ነጻ እንዳላቸው ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ተቋሙ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች እና ጥቆማዎችን ለመቀበል ከተዘረጉ የ905 እና 904 ነጻ የጥሪ ማዕከላት በተጨማሪ፤ ደንበኞች ቅሬታቸውን ቀላልና ምቹ በሆነ መንገድ ማቅረብ የሚችሉበት ዘመናዊ የሙስና ጥቆማ መቀበያ ስርዓት ለመዘርጋት በሂደት ላይ መሆኑን መጠቆሙን የኢትዮጵያ ብርድካስት ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሙስና እና ብልሹ አሰራር በሀገር የዕድገት ጉዞ ላይ የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህብራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ በመረዳት በጋራ ልንታገል ይገባል!

***************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሥነምግባር የታነፀና የህብረተሰብ ጥቅም የሚያከብር ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን "በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና ፀረ-ሙስና ጉዳዮች" ትኩረት አድርገው በተዘጋጁ የስልጠና ሞጁሎች ላይ ማረጋገጫ አውደ ጥናት አካሄደ፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ እንደገለፁት ለሀገር ዕድገትና ለልማት ፀር የሆነውን ሙስናን ለመዋጋት የዜጎችን ሥነምግባር መገንባት ይገባል ብለዋል፡፡

አክለውም በሥነምግባር የታነፀና የህብረተሰቡን ጥቅም የሚያከብር ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ በበኩላቸው የአውደ ጥናቱ ዓላማ የትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስናን በመለየት ለመከላከልና ለመፍታት የሚያስችል ዕውቀትና ክህሎት ለማስታጠቅ የተዘጋጀውን የስልጠና ሞጁሎች ለማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡

የፀረ-ሙስና ትግል የግለሰብ ብቻ ሳይሆን የጋራ ኃላፊነት ጭምር መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ በዚህ አውደ ጥናት ለራሳችን እና ለመጪው ትውልድ የተሻለ ሁኔታ ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት ለማሳየትና የስልጠና ሞጁሎቹን ለማዳበር በቂ አስተያየት መስጠት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ በሥነምግባርና መልካም አስተዳደር፣ የሙስና ጽንሰ ሀሳብ እና የመከላከል ስልቶች፣ የሃብት ማሳወቅ እና ማስመዝገብ ስርዓት፣ ሙስናና የመንግስት ግዢ፣ የሙስና ወንጀል ምርመራ፣ የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር፣ የሙስና ወንጀል በጠቅላላው፣ የፖሊስና ዓቃቢ ህግ የሙያ ሥነምግባር፣ የሙስና ስጋት ዳሰሳ ጥናት እና ሥነምግባራዊ አመራር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማዘጋጀት ወንጀል የተከሰሰው የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኛ በእስራት ተቀጣ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን በማዘጋጀት ወንጀል የተከሰሰው የሻንቡ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኛ በ8 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ውሳኔ አሳለፈ።

የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ የሙስና አዋጅ 881/2007 ድንጋጌን መተላለፉን ጠቅሶ ሶሬሳ አፋታ ላይ ክስ መስርቶበታል።

ተከሳሹ በጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሻንቡ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የተማሪዎች ምዝገባ ኦፊሰር ሆኖ ሲሰራ በተቋሙ አመራሮች ፊርማ የተዘጋጀ የሚመስል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችና የሙያ ማረጋገጪያ ምስክር ወረቀቶችን በ34 ግለሰቦች ስም አዘጋጅቶ የተገኘ መሆኑ በክሱ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።

በዚህ መልኩ የቀረበበት ክስ ለተከሳሹ እንዲደርስ ከተደረገ በኋላ ተከሳሹ ወንጀሉን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰውና የሰነድ ማስረጃን መርምሮ በተከሰሰበት ድንጋጌ እንዲከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሹ መከላከል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን ከመረመረ በኋላ ተከሳሹን ጥፋተኛ በተባለበት ድንጋጌ በ8 ዓመት ከ5 ወራት ጽኑ እስራትና በ1 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጣ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዙሪያ የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር የተደረገ ቆይታ

***************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በልጆች ሥነምግባር ግንባታ የቤተሰብ ሚና (ክፍል ሶስት)

***************

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በበይነመረብ አማካኝነት የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ክህሎት ሥልጠና እና ግንዛቤ ማጎልበቻ ፕሮግራም ሥራዎችን እያቀረበ ሲሆን ‹‹ለልጆች የሥነምግባር ግንባታ የቤተሰብ ሚና›› በሚል ርዕስ ክፍል ሶስት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡