ኮሚሽኑ ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያ የመሪዎች ሥነምግባራዊ መሪነት ላይ የአቅም ግንባታ፣ የምዘና እና አገርዓቀፍ የዕውቅና እንዲሁም የሽልማት ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በስምምነት መድረኩ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ዓላማው አመራሩ ሥነምግባርና ኢንተገሪቲ ኑሮት ለሀገር ጥሩ ሥራ እንዲሰራ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ማዕከሉ በተለያዩ ጉዳዮችና ተቋማት የመሰረተ ልማት ቅንጅት ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ከፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋርም በሀገራችን በአመራሩ ሥነምግባርና ኢንተግሪቲ ላይ ሀሳብ እንዲይዝ በጋራ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ማዕከሉ ሀገራት ሥነምግባርንና ኢንተገሪቲን ማዕከል የሚያደርጉበት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ይህን ማዕከል አድርገው የማይሰሩ አመራሮች ጥሩ ተግባር ስለማያከናውኑ ይህን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አመራሩ ሥነምግባር እንዲኖረው ሥልጠና እየሰጠን እና ጥሩ ሥነምግባር ያላቸው አመራሮችን ደግሞ እውቅና አና ሽልማት በመስጠት ሀገራችን በፀረ-ሙስና ትግል የምታደርገውን አስተዋጾኦ ለማጠናከር ከኮሚሽኑ ጋር አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡ መንግስትም ሙስናን በመታገል በኩል የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የስምምነቱ ዓላማ በመንግስት ተቋማት፣ በህዝባዊ ድርጅቶች እና በልማት ድርጅቶች ያሉ አመራሮች ሥነምግባረዊ እንዲሆኑና ሙስናን እንዲከላከሉ በጋራ ለመስራት መኆኑን ገልፀዋል፡፡
ማዕከሉ ዓላማው በሀገር ደረጃ ጥሩ አመራርን ማፍራት ሥለሆነና የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደግሞ ሥነምግባርን በመገንባት ሙስናን የሚከላከል በመሆኑ ለጋራ ውጤት በትብብር ማዕቀፍ እንደሚሰሩ አመላክተዋል፡፡
አመራር ከማልማት አንጻር ኃላፊነት ከተሰጠው ተቋምጋር አብሮ መስራት የሀብት ብክነትን ለመቀነስ ያስችላል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ችግር ፈች የአመራር ክፈተቶችን በማጥናት እና አመራሩን ለማብቃት የሚያስችል ሥልጠናዎችን በመስጠት አርዓያ ለሆኑት ደግሞ ዕውቅና እና ሽልማት በመስጠት በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
በሐሰተኛ ሰነድ ከባለሀብት 13 ሚሊዮን 888 ሺህ ብር ተቀብሎ የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ
***************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሐሰተኛ ሰነድ አጭበርብሮ ከባለሃብት 13 ሚሊዮን 888 ሺህ ብር ተቀብሎ የተሰወረው ቱጁባ ቶልቻ ሰንበታ የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታ ሴንትራል ማተሚያ ቤት አካባቢ በሐሰተኛ ሠነድ አጭበርብሮ ከባለሀብቱ 13 ሚሊዮን 888 ሺህ ብር ተቀብሎ የተሠወረውን ቱጁባ ቶልቻ ሰንበታ የተባለውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዚህ ግለሰብ ተታለልኩ ወይም ተጭበረበርኩ የሚል ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ ቀርቦ ሪፖርት እንዲያደርግ ተቋሙ ያስታውቃል።
ኅብረተሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ተግባር እንዳይታለል ራሱን እንዲጠብቅና በወንጀል መከላከል ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው የፍርድ ቤት ዳኛ ላይ ክስ የመመስረቻ ጊዜ ተሰጠ
***************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው የፍርድ ቤት ዳኛ ላይ ክስ የመመስረቻ ጊዜ ለዐቃቤ ሕግ ሰጠ።
ተጠርጣሪው የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ እና የፍርድ ቤቱ የኢንስፔክሽን ኃላፊ የሆነው ተስፋዬ ደረጄ፤ ከዚህ በፊት በሙስና ወንጀል ተከሶ የነበረ ሀብተማርያም ገ/መስቀል የተባለ ግለሰብን ጉዳይ የሚመለከቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች አብረውት እንደተማሩና እንደሚያውቃቸው በመጥቀስ እንዲሁም አንደኛውን ዳኛ “የስራ አለቃዬ ስለሚያውቀው ነጻ አወጣሃለው” በማለት በማግባባት የሙስና ገንዘብ ተቀብሏል ተብሎ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ሲከናወንበት ነበር።
ምርመራውን ሲያከናውን የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ስራውን አጠናቆ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን አስታውቋል።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ ክስ ለመመስረት እንዲያስችለው በወ/መ/ስ/ህ/ ቁጥር 109/1 መሰረት የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቧል።
ተጠርጣሪው በበኩሉ የተጠረጠረበት የወንጀል ተግባር በሙስና ወንጀል ጉዳይ ሊታይ አይገባም በማለት በመከራከር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱን እንዲያከብርለት ጠይቋል።
ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ግለሰቡ የተጠረጠረበት የወንጀል ድርጊት ዋስትናን የሚያስከለክልና ከ10 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል በከባድ የሙስና ድንጋጌ የሚያስከስስ መሆኑን በመጥቀስ የተጠርጣሪው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ እንዲደግ መጠየቁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
የግራ ቀኝ ክርክሩን የተከታተለው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለዐቃቤ ሕግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ መስጠት አስፈላጊነትን በማመን 15 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
***************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው የፍርድ ቤት ዳኛ ላይ ክስ የመመስረቻ ጊዜ ለዐቃቤ ሕግ ሰጠ።
ተጠርጣሪው የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ እና የፍርድ ቤቱ የኢንስፔክሽን ኃላፊ የሆነው ተስፋዬ ደረጄ፤ ከዚህ በፊት በሙስና ወንጀል ተከሶ የነበረ ሀብተማርያም ገ/መስቀል የተባለ ግለሰብን ጉዳይ የሚመለከቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች አብረውት እንደተማሩና እንደሚያውቃቸው በመጥቀስ እንዲሁም አንደኛውን ዳኛ “የስራ አለቃዬ ስለሚያውቀው ነጻ አወጣሃለው” በማለት በማግባባት የሙስና ገንዘብ ተቀብሏል ተብሎ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ሲከናወንበት ነበር።
ምርመራውን ሲያከናውን የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ስራውን አጠናቆ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን አስታውቋል።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ ክስ ለመመስረት እንዲያስችለው በወ/መ/ስ/ህ/ ቁጥር 109/1 መሰረት የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቧል።
ተጠርጣሪው በበኩሉ የተጠረጠረበት የወንጀል ተግባር በሙስና ወንጀል ጉዳይ ሊታይ አይገባም በማለት በመከራከር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱን እንዲያከብርለት ጠይቋል።
ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ግለሰቡ የተጠረጠረበት የወንጀል ድርጊት ዋስትናን የሚያስከለክልና ከ10 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል በከባድ የሙስና ድንጋጌ የሚያስከስስ መሆኑን በመጥቀስ የተጠርጣሪው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ እንዲደግ መጠየቁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
የግራ ቀኝ ክርክሩን የተከታተለው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለዐቃቤ ሕግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ መስጠት አስፈላጊነትን በማመን 15 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
የመሬት አያያዝ መረጃን በማዘመን በዘርፉ የሚታየውን ብልሹ አሠራር ለመቅረፍ ከመቸውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ሥራ መሥራት ይገባል
***
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የመሬት አያያዝ መረጃን በማዘመን በዘርፉ የሚታየውን ብልሹ አሠራር ለመቅረፍ ከመቸውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ ጠቁመዋል፡፡
ይህ የተጠቆመው በምከር ቤቱ 12ኛ መደበኛ ስብሰባ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ነው፡፡
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ጫልቱ ሳኒ የተቋሙን የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው በምከር ቤቱ አስገምግመዋል፡፡
የአፈፃፀም ሪፖርቱ ከተደመጠ በኋላ የመሬት አያያዝ መረጃን በማዘመን በዘርፉ የሚታየውን ብልሹ አሠራር ለመቅረፍ ከመቸውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ አሳስበዋል፡፡
የምክር ቤት አባላት የመረጣቸውን ሕዝብ በሚያወያዩበት ጊዜ ሕዝቡ ቅሬታ ከሚነሳባቸው አንዱ የመንገድ ፕሮጀክቶች በመሆናቸው ሚንስቴር መ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የተከበሩ ወይዘሮ ሸዊት ጨምረው አሳስበዋል፡፡
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ችግሮች፣ እንዲሰሩ እቅድ ተይዞላቸው ያልተሰሩ መንገዶችን፣ ሥራቸው ተጀምሮ የተጓተቱ የመንገድ ፕረጀክቶችን፣ በከተሞች ያለው የመሬት አስተዳደር ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ መሆኑንና በትክክል ካሳ ለተገመተላቸው የመሬት ባለቤቶች በወቅቱ ካሳ እየተከፈለ አለመሆኑን አንስተው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጣቸው የምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በሰጡት ምላሽ ማብራሪያ፤ ለክልልና ለፌዴራል ፕሮጀክቶች የሚሰጠው የካሳ ግምት የተለያየ በመሆኑ የምክር ቤት አባላት ሊረዷቸው እንደሚገባ ጠቁመው፤ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ችግር ያለበት መሆኑን በጥናት ስላረጋገጡ በቀጣይ ትኩረት ሰጥተው የሚሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቶችን አስመለክቶም ለተነሱ ጥያቄዎች በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የሚሠሩ ተለይተው እንቅስቃሴ የተጀመረ በመሆኑ ችግሩ በየደረጃው የሚፈታ መሆኑን ጠቁመው፤ የመሬት መረጃ አስተዳደርን ለማዘመን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ለምክር ቤት አባላት ማስረዳታቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጩ ያልታወቀን ሀብት በመጠቆም በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ ከዘረፋ ከተመለሰው ሀብት እስከ 25% የሚሆንው ሀብት ለጠቋሚው ማበረታቻ ይሰጣል - ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ
***
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በክልሉ ውስጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የሀብት ምዝገባና የማሳወቅ እንዲሁም የማጣራት ስራ እያካሄደ ይገኛል።
የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ በዛሬው እለት ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሀብት ማሳወቅ፣ ምዝገባና ማረጋገጥ ዙሪያ መረጃ ሰጥተዋል።
የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እንዲሁም ማረጋገጥ ስራ ዓላማው የግልፀኝነትና ተጠያቂነት ስርዓት እንዲሰፍን፣ ተሿሚዎች፣ የህዝብ ተመራጮችና ለሙስና ተጋላጭ ከሆኑ መደቦች ላይ የተመደቡ/የተቀጠሩ ባለሙያዎች ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ከገቢ ምንጫቸው በላይ ሀብት ማካበት እንዳይችሉ እንዲሁም የጥቅም ግጭት እንዳይኖር ለመከላከል ታስቦ የተደረገ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ።
በመሆኑም ማንኛውም ሀብት አስመዝጋቢ በተገደበና በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ሀብቱን ማስመዝገብ እንዳለበት በአዋጅ የተቀመጠ መሆኑን ጠቅሰው ማንኛውም ሰው የሌላን ሰው ሀብት ህጋዊ በሆነ መልኩ ማወቅ ከፈለገ የማንኛውንም ሰው የሀብት መረጃ የማግኘትና የማየት መብት አለው ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ማንኛውም ሰው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት መኖሩን አውቆ በማስረጃ አስደግፎ ጥቆማ የሰጠ እና የተጠቆመው ሀብት መኖሩ ተረጋግጦ በፍትህ ክስ ተመስርቶበት በፍ/ቤት ጥፋተኛነቱ ታውቆ ለመንግስት የሚመለስ ሀብት ካለ ለጠቋሚው ከሚመለሰው ሀብት እስከ 25% የሚደርስ ሀብት ጠቋሚው የማግኘት መብት አለው ብለዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም በዚህ ዓመት ሙስናን ለመከላከል ያጋጠሙ ችግሮች ወቅታዊ የክልሉ የሰላም አለመረጋጋትና ሁሉም ተቋማት በሚፈለገው ልክ አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆኑ ምክንያት ለሙስና እና ብልሹ አሰራር፣ ለዘረፋና የማጭበርበር ተግባር ለሌቦች አመች ሁኔታ ፈጥሯል፤ የፀጥታ አካላት በወቅታዊ ስራ በመጠመዳቸው ምክንያት የሙስና ወንጀል የፈፀሙ አካላትን ተከታትሎ መያዝ አለመቻል፣ ህብረተሰቡ በሚፈለገው ልክ ተዘዋዉሮ ጥቆማዋችንና ማስረጃዎችን ማድረስ አለመቻሉ በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ የመቀዛቀዝ ሁኔታ ፈጥሯል ብለዋል።
እንደኮሚሽን በተቋማት ውስጥ የህዝብን እሮሮ በመስማትና ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ተቋማትን በመለየት የአሰራር ስርዓት ጥናት በማድረግ ብልሹ አሰራሮች እንዲስተካከሉ በማድረግ፤ በክልሉ ውስጥ ያሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችንና አጋር አካላትን በማጠናከር ወደ ሙስና መከላከል ተግባር እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ገልፀው፤ ሙስናን በዚህ ተቋም ብቻ መከላከል ስለማይቻል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና ተቋማት ድጋፍና ተሳትፎ ይጠይቃል ብለዋል።
የፀረ-ሙስና ትግሉን ይበልጥ ለማቀጣጠል ህብረተሰቡ በባለቤትነት ይዞ ጥቆማዎችንና ማስረጃዎችን በመስጠት እንዲሁም አጋር አካላት ከዚህ በፊቱ የተሻለ ቅንጅት በመፍጠር ሁሉም አካባቢ እየታዩ ያሉ የሙስና ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ጥረትና ትግል ያስፈልጋል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኃላፊነታቸውን ተገን በማድረግ ሙስና የፈፀሙ ግለሰቦች ተቀጡ