Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

*****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 18/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ልዩ ልዩ ሐሰተኛ ሰነዶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩና ሲያታልሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የመንግስት ባለስልጣናትን ስም በማንሳት ''እነ እከሌን እናውቃለን፤ ጉዳያችሁን እንጨርስላችኋለን'' በማለት የተለያዩ ሰዎችን በማጭበርበር ገንዘብ እየተቀበሉ ባሉበት ወቅት ከማስረጃ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ባለሃብትና ከፍተኛ ገንዘብ እንዳላቸው ለማስመሰል በርካታ የአሜሪካን ዶላር በሳምሶናይት ይዘው ፎቶግራፍ በመነሳት እና እራሳቸውን በማሳየት ሲያጨብረብሩ መቆታቸው ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የመከላከያ ሠራዊት እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት የስራ ባልደረባ አባል ነን በሚል በሐሰተኛ መታወቂያ ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩና ሲያታልሉ እንደቆዩ ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አካባቢ በሚገኘው የአንደኛው ተጠርጣሪ ሞቱማ ደለሳ ቦሮቃ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባደረገው ብርበራ ለወንጀል ተግባር ማስፈፀሚያ የሚገለገሉበት 90 ሺህ ብር፣ አንድ ሽጉጥ ከ24 መሠል ጥይቶች እና ከ2 ካዝና ጋር፣ አይፎንና ሳምሳንግ ሞባይል፣ አንድ አፒድ ላፕቶፕ እና ሦስት ፍላሾች ተይዘዋል፡፡

ህብረተሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችንና ቡድኖችን በሚመለከትበት ጊዜ በማጋለጥ እና አሳልፎ ለፖሊስ በመስጠት እንዲተባበር የፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በልጆች ሥነምግባር ግንባታ የቤተሰብ ሚና (ክፍል ሁለት)

***************

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በበይነመረብ አማካኝነት የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ክህሎት ሥልጠና እና ግንዛቤ ማጎልበቻ ፕሮግራም ሥራዎችን እያቀረበ ሲሆን ‹‹ለልጆች የሥነምግባር ግንባታ የቤተሰብ ሚና›› በሚል ርዕስ ክፍል ሁለት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩት እነ ኤልቤቴል ሀብቴ ላይ የክስ መመስረቻ ጊዜ ተሰጠ

*****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 20/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የቀድሞ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር እነ ኤልቤቴል ሀብቴ ላይ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል የክስ ለመመስረት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ለዐቃቤ ሕግ 15 ቀን ሰጠ።

ተጠርጣሪዎቹ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የቀድሞ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር ኤልቤቴል ሀብቴ፣ የፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር ፍቅሩ ኦላና እንዲሁም በግል ስራ ይተዳደራሉ የተባሉት ቅዱስ መስፍን፣ አማኑኤል መስፍንና ተክሌ ከቡ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ ከ17 ነጋዴዎች ከውጭ ሀገር እቃ ለማስመጣት በሚል ከተወሰደ ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ጋር ተያይዞ ስልጣንን ያለአግባብ በመገልገል እና ከማታለል ተግባር ጋር ተያይዞ በወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ ሲከናወንባቸው ቆይቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ሲያከናውን የቆየውን የምርመራ ስራ ማጠናቀቁንና የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን አስታውቋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ ለመወሰንና ክስ ለመመስረት እንዲያስችለው በወ/መ/ስ/ህ/ ቁጥር 109/1 መሰረት የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች የዐቃቤ ሕግ የክስ መመስረቻ ጥያቄን በመቃወም የተጠረጠሩበት ወንጀል ተራ መሆኑን ጠቅሰው የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድ ጠይቀዋል።

ዐቃቤ ሕግ በተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት የደረሰ መሆኑን በመጥቀስ ዋስትናን በሚያስነፍግ እና ከ10 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ በከባድ የሙስና ድንጋጌ ሊከሰሱ እንደሚችሉ ገልጾ፤ የዋስትና ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተከታተለው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ለዐቃቤ ሕግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ መስጠት አስፈላጊነትን በማመን 15 ቀናትን መፍቀዱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽኑ ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያ የመሪዎች ሥነምግባራዊ መሪነት ላይ የአቅም ግንባታ፣ የምዘና እና አገርዓቀፍ የዕውቅና እንዲሁም የሽልማት ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በስምምነት መድረኩ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ዓላማው አመራሩ ሥነምግባርና ኢንተገሪቲ ኑሮት ለሀገር ጥሩ ሥራ እንዲሰራ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ማዕከሉ በተለያዩ ጉዳዮችና ተቋማት የመሰረተ ልማት ቅንጅት ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ከፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋርም በሀገራችን በአመራሩ ሥነምግባርና ኢንተግሪቲ ላይ ሀሳብ እንዲይዝ በጋራ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማዕከሉ ሀገራት ሥነምግባርንና ኢንተገሪቲን ማዕከል የሚያደርጉበት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ይህን ማዕከል አድርገው የማይሰሩ አመራሮች ጥሩ ተግባር ስለማያከናውኑ ይህን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አመራሩ ሥነምግባር እንዲኖረው ሥልጠና እየሰጠን እና ጥሩ ሥነምግባር ያላቸው አመራሮችን ደግሞ እውቅና አና ሽልማት በመስጠት ሀገራችን በፀረ-ሙስና ትግል የምታደርገውን አስተዋጾኦ ለማጠናከር ከኮሚሽኑ ጋር አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡ መንግስትም ሙስናን በመታገል በኩል የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የስምምነቱ ዓላማ በመንግስት ተቋማት፣ በህዝባዊ ድርጅቶች እና በልማት ድርጅቶች ያሉ አመራሮች ሥነምግባረዊ እንዲሆኑና ሙስናን እንዲከላከሉ በጋራ ለመስራት መኆኑን ገልፀዋል፡፡

ማዕከሉ ዓላማው በሀገር ደረጃ ጥሩ አመራርን ማፍራት ሥለሆነና የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደግሞ ሥነምግባርን በመገንባት ሙስናን የሚከላከል በመሆኑ ለጋራ ውጤት በትብብር ማዕቀፍ እንደሚሰሩ አመላክተዋል፡፡

አመራር ከማልማት አንጻር ኃላፊነት ከተሰጠው ተቋምጋር አብሮ መስራት የሀብት ብክነትን ለመቀነስ ያስችላል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ችግር ፈች የአመራር ክፈተቶችን በማጥናት እና አመራሩን ለማብቃት የሚያስችል ሥልጠናዎችን በመስጠት አርዓያ ለሆኑት ደግሞ ዕውቅና እና ሽልማት በመስጠት በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሐሰተኛ ሰነድ ከባለሀብት 13 ሚሊዮን 888 ሺህ ብር ተቀብሎ የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሐሰተኛ ሰነድ አጭበርብሮ ከባለሃብት 13 ሚሊዮን 888 ሺህ ብር ተቀብሎ የተሰወረው ቱጁባ ቶልቻ ሰንበታ የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታ ሴንትራል ማተሚያ ቤት አካባቢ በሐሰተኛ ሠነድ አጭበርብሮ ከባለሀብቱ 13 ሚሊዮን 888 ሺህ ብር ተቀብሎ የተሠወረውን ቱጁባ ቶልቻ ሰንበታ የተባለውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዚህ ግለሰብ ተታለልኩ ወይም ተጭበረበርኩ የሚል ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ ቀርቦ ሪፖርት እንዲያደርግ ተቋሙ ያስታውቃል።

ኅብረተሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ተግባር እንዳይታለል ራሱን እንዲጠብቅና በወንጀል መከላከል ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው የፍርድ ቤት ዳኛ ላይ ክስ የመመስረቻ ጊዜ ተሰጠ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው የፍርድ ቤት ዳኛ ላይ ክስ የመመስረቻ ጊዜ ለዐቃቤ ሕግ ሰጠ።

ተጠርጣሪው የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ እና የፍርድ ቤቱ የኢንስፔክሽን ኃላፊ የሆነው ተስፋዬ ደረጄ፤ ከዚህ በፊት በሙስና ወንጀል ተከሶ የነበረ ሀብተማርያም ገ/መስቀል የተባለ ግለሰብን ጉዳይ የሚመለከቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች አብረውት እንደተማሩና እንደሚያውቃቸው በመጥቀስ እንዲሁም አንደኛውን ዳኛ “የስራ አለቃዬ ስለሚያውቀው ነጻ አወጣሃለው” በማለት በማግባባት የሙስና ገንዘብ ተቀብሏል ተብሎ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ሲከናወንበት ነበር።

ምርመራውን ሲያከናውን የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ስራውን አጠናቆ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን አስታውቋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ ክስ ለመመስረት እንዲያስችለው በወ/መ/ስ/ህ/ ቁጥር 109/1 መሰረት የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቧል።

ተጠርጣሪው በበኩሉ የተጠረጠረበት የወንጀል ተግባር በሙስና ወንጀል ጉዳይ ሊታይ አይገባም በማለት በመከራከር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱን እንዲያከብርለት ጠይቋል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ግለሰቡ የተጠረጠረበት የወንጀል ድርጊት ዋስትናን የሚያስከለክልና ከ10 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል በከባድ የሙስና ድንጋጌ የሚያስከስስ መሆኑን በመጥቀስ የተጠርጣሪው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ እንዲደግ መጠየቁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተከታተለው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለዐቃቤ ሕግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ መስጠት አስፈላጊነትን በማመን 15 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡