አትሌት ድሪባ መርጋን ጨምሮ 3 ግለሰቦች ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በማቅረብ የሙስና ወንጀል ተከሰሱ
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 15/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) አትሌት ድሪባ መርጋን ጨምሮ 3 ግለሰቦች ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመገልገል የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ተከሳሾቹ አትሌት ድሪባ መርጋ እጅጉ በግል ስራ የሚተዳደሩት ወ/ሮ መንበረ አበበ ገብረጻዲቅ እና አቶ ስዩም አሰፋ ወንድማገኝ ናቸው።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ ተደራራቢ ክስ አቅርቦባቸዋል።
በዚህም በአንደኛው ክስ በአትሌት ድሪባ ላይ ብቻ በቀረበው ክስ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፏል የሚል ነው።
ተከሳሹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ 1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር በሆነውና በስራ አስኪያጅነት የሚተዳደረውን የናይስ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሆነውንና በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ስር የሚገኘውን 4 ሺህ 972 ካሬ ሜትር ይዞታን ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ ሰነዶችን ማለትም በመጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከሚመለከተው ተቋም እንደተሰጠ በማስመሰል የተዘጋጀ ሀሰተኛ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለሶስተኛ ወገን ለሽያጭ ማቅረቡን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክሱ አስፍሯል።
በተጨማሪም አትሌት ድሪባ የተባለው ተከሳሽ በውል ቁጥር 2036/2012 ዓ.ም ደግሞ በውል ሰጭ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ዝግጅት እና ማስተላለፍ ዘርፍ እና በውል ተቀባይ ናይስ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል የተፈረመ በማስመሰል የተዘጋጀ ሀሰተኛ የሊዝ ውል፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተሰጠ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም በኮድ ቁጥር 2929/2929/2015 የሊዝ ውልን በማሻሻል እንደላከ በማስመሰል የተዘጋጀ ሀሰተኛ የሊዝ ውል ለሽያጭ አቅርቧል በማለት ዐቃቤ ሕግ በክሱ አመላክቷል።
በተጨማሪም ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ውክልና ባልሰጠችበት ሁኔታ ላይ በህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለ1ኛ ተከሳሽ ይዞታውን በሽያጭ እስከ ማስተላለፍ ድረስ እንዲያስተዳድር ውክልና እንደሰጠች ተደርጎ የተዘጋጀ ሀሰተኛ የውክልና ሰነድ ማቅረቡን በክሱ ላይ አመላክቷል።
በአጠቃላይ 1ኛ ተከሳሽ በታህሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በይዞታው ላይ የተጠቀሱ ሀሰተኛ ሰነዶችን ትክክለኛ አስመስሎ ይዞ በማቅረብ ይዞታውን በ700 ሚልየን ብር ለመሸጥ ሲደራደር የተያዘ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነድ መገልገል የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦበታል።
በ2ኛና በ3ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ በቀረበው ክስ ደግሞ ተከሳሾቹ በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) ስር የተመለከተውን ተላልፈዋል የሚል ነው።
በዚህም 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስበው በ1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር በሆነው እና በስራ አስኪያጅነት የሚተዳደረው ናይስ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ይዞታ የሆነውንና በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ስር የሚገኘውን 4 ሺህ 972 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ተመሳስሎ የተሰራ ሀሰተኛ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ የሊዝ ውልና የውክልና ሰነድ ያዘጋጁ መሆኑን ጠቅሶ ሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነድ ማዘጋጀት የሙስና ወንጀል ክስ ዐቃቤ ሕግ አቅርቦባቸዋል።
3ኛ ክስ ደግሞ በ2ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ የቀረበ ሲሆን ይኸውም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 390 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን መተላለፍ የሚል ክስ ቀርቦባታል።
በዚህም በታህሳስ 4 ቀን በ 2016 ዓ.ም በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው አረንጓዴ ሰፈር ተብሎ ከሚታወቀው ቦታ አካባቢ በሚገኘው የስራ ቦታዋ ውስጥ በፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰረት በተደረገ ብርበራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በልደታ ክ/ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጽ/ቤት የዕውቀት ለህብረት የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ካርድ እና በትምህርት ሚኒስቴር አባይ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ ውጤት መግለጫ ካርድ የተገኘባት በመሆኑ የሐሰት ስራ ለመፈጸም የሚያገለግሉ መሳርያዎችና መስርያዎች ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሳለች።
በዚህ መልኩ የቀረበባቸው ክስ ዝርዝር በችሎት እንዲደርሳቸው መደረጉን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
በግብር ከፋዩ ማህበረሰብ የታክስ ህግ ተገዥነት ላይ የሚስተዋሉ የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለማረም በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉም ባለድርሻ የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ተገለፀ
***************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽህፈት ቤት በታክሲ ህግ ተገዥነት ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
የመንግስትን ግብር መሰወርና ማጭበርበር ለታክስ ህጉ ተገዥ ካለመሆን የሚመነጭ ህገወጥ ተግባር ነው።
በታክስ ህጉ ተገዥነት ዙሪያ ከዚህ ቀደም የተስተዋሉ ክፍተቶችን በመለየት ግንዛቤ በመስጠት ግብርን በተገቢው ለመሰብሰብና ግብር ከፋዩንም ከተጠያቂነት ማዳንን ዓላማ በማድረግ የተዘጋጀ መድረክ ሰለመሆኑ የሆሳዕና ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፀጋነሽ ዮሐንስ በመወያያ ጽሑፉ ገልፀዋል።
ለታክስ ህጉ ተገዥ ካለመሆን የተነሳ ግብርን መሰወርና ማጭበርበር ግብይትን ያለደረሰኝ በማካሄድ፣ ሀሰተኛ ደረሰኝ መጠቀም፣ የገቢ ተቋም ባለሙያዎችን በጥቅም በመደለል፣ ህገወጥ ንግድ በመስፋፋቱና ሌሎችም የታክስ ስርዓቱን የሚፈታተኑ ምክንያቶች መሆናቸውን አስረድተዋል።
በቀጣይ ብርቱ ክትትል በማድረግ የታክስ ህጉን በሚጥሱ አካላት ጠንካራ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልፀዋል።
መድረኩን የመሩት የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ የመንግስትን ግብር በታማኝነት መክፈል በህግም በሃይማኖት አስተምሮ ዘንድም መልካም ተግባር እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ሁሉም ግብር ከፋይ ለታክስ ህጉ ተገዥ የመሆን ግዴታ አለበት ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በግብር አሰባሰብ ሂደቱ ህገወጥነትን ህጋዊ ስርዓት ለማስያዝ ከፍትህ ተቋማት ጋር በሚደረግ እንቅስቃሴ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን በማውገዝ ሁሉም ባለድርሻ መተባበር እንዳለበትም አሳስበዋል።
በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገቢዎች ቢሮ የደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደግፍ መለሰ በበኩላቸው ክልሉ የሚያመነጨውን ገቢ በተገቢው ለመሰብሰብ እንዲቻል ከታክስ ህግ ተገዥነት አንፃር የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሸፈን የንቅናቄ መድረኩ አጋዥ ነው ብለዋል።
ለንግድ ስርዓቱ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን ለመፍታት በየደረጃው እንደሚሰራም ገልፀዋል።
ግብርን መሰወርና ማጭበርበር ሌብነት ነው፤ ሌብነት ደግሞ ክብርን መጣል፣ ህግን መናቅና ህገወጥነትን ማስፈን በመሆኑ ሀሉም ግብር ከፋይ ግብርን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ያሉት ደግሞ የሆሳዕና ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ አቶ ሊሬ ጀማል ናቸው።
በመድረኩ የተሳተፉ ግብር ከፋዮችም በተለይ በአዲስ አበባና በሌሎችም ከተሞች የሚገኙ አንዳንድ የጅምላ ዕቃ አቅራቢ ነጋዴዎች ላይ የሚታይ የደረሰኝ አቆራረጥ ችግርና በመግቢያና መውጫ መንገዶች ላይ አልፎ አልፎ የሚታይ የፀጥታ ችግር መፍትሄ አንዲሰጠው ጠይቀዋል።
ግብር ከራስ ለራስ የሚከፈል ገቢ በመሆኑ ለታክስ ህጉ ተገዥ በመሆን ግብርን በታማኝነት እንደሚከፍሉ ተናግረዋል።
በንቅናቄ መድረኩ ግብር ከፋዮች፣ የፍትህ አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የገቢ ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በልጆች ሥነምግባር ግንባታ የቤተሰብ ሚና (ክፍል አንድ)
***************
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በበይነመረብ አማካኝነት የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ክህሎት ሥልጠና እና ግንዛቤ ማጎልበቻ ፕሮግራም ሥራዎችን እያቀረበ ሲሆን ‹‹ለልጆች የሥነምግባር ግንባታ የቤተሰብ ሚና›› በሚል ርዕስ ክፍል አንድ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ማረሚያ ቤት በሚገኝ ግለሰብ ስም ሀሰተኛ ሊብሬና ከዕግድ ነጻ ሰነዶችን በመጠቀም ገንዘብ ተበድረዋል የተባሉ በሙስና ወንጀል ተከሰሱ
***************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ማረሚያ ቤት በሚገኝ ግለሰብ ስም ሀሰተኛ የቪ8 ተሽከርካሪ ሊብሬና ከዕግድ ነጻ ሰነዶችን በመጠቀም ገንዘብ ተበድረዋል የተባሉ 4 ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተከሰሱ።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ተከሳሾቹ በወንጀል ተግባር ክስ ተመስርቶበት በማረሚያ ቤት የሚገኘው 1ኛ ተከሳሽ ሱራፌል በቀለ ደግፌ፣ 2ኛ ወ/ሮ ራኬብ መንግስቱ፣ 3ኛ ወ/ሮ ቤተልሄም መንግስቱ እና 4ኛ ወ/ሮ ማህሌት በቀለ ይባላሉ።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 2 (ሀ) እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል በማለት ክስ አቅርቦባቸዋል።
በዚህም ተከሳሾቹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ከአ/አ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት በማረሚያ ቤት በሚገኝ ሱራፌል በቀለ በሚባል ግለሰብ ስም የተመዘገበ በማስመሰል የቪ8 ተሽከርካሪ ማረጋገጫ ሊብሬና ከዕግድ ነጻ የሚል የተዘጋጁ ሀሰተኛ ሰነዶችን መጠቀማቸው በክስ ዝርዝሩ ላይ ተመላክቷል።
በዚህ ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም በ2013 ዓ.ም በፀደቀ የብድር ውል ስምምነት መሰረት ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ ከሚባል ህዝባዊ ድርጅት በተለያዩ መጠኖች በአጠቃላይ 4 ሚሊየን 575 ሺህ 547 ብር ገንዘብ ተበድረው ጥቅም አግኝተውበት ያልመለሱ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነዶችን መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።
ዐቃቤ ሕግ ገላጭና አስረጂ ያላቸውን የሰነድ ማስረጃዎችን የክስ ዝርዝሩ ላይ ጠቅሶ አቅርቧል።
ከአንደኛ ተከሳሽ ውጪ ያሉ ተከሳሾች ችሎት ቀርበው ክሰ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
አንደኛ ተከሳሽን በሚመለከት ግን ከማረሚያ ቤት አልቀረበም።
ፍርድ ቤቱም አንደኛ ተከሳሽ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት ክሱን ለመመልከት ለጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ኮሚሽኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እንዲሁም ማጣራት ስራ እያካሄደ እንደሚገኝ ገለፀ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በክልሉ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እንዲሁም ማጣራት ስራ እያካሄደ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት የኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳ/ዳይሬክተር አቶ ይልቃል ወርቅነህ በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እንዲሁም ማጣራት ላይ ለጋዜጠኞች መረጃ ሰጥተዋል።
አቶ ይልቃል በመግለጫቸው የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዋና ዓላማው የግልፀኝነትና ተጠያቂነት ስርዓት ለማስፈንና ተሿሚዎች ስልጣናቸውን ያለአግባብ መከታ አድርገው ከገቢ ምንጫቸው በላይ ሀብት ማካበት እንዳይችሉ እንዲሁም የጥቅም ግጭት ለመከላከል መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።
ሀብት ማስመዝገብ ያለባቸው አካላት የህዝብ ተመራጮች፣ በየትኛውም እርከን ላይ ያሉ የመንግስት ተሿሚዎች እና ለሙስና ተጋላጭ ከሆኑ መደቦች ላይ የተመደቡ/የተቀጠሩ ባለሙያዎችን መሆናቸውን ገልፀዋል።
ሀብት አስመዝጋቢዎች የመጀመሪያ ምዝገባ ሀብታቸውን ማስመዝገብ ያለባቸው የህዝብ ተመራጮች በተመረጡ፣ የመንግስት ተሿሚዎች በተሾሙ እና ባለሙያዎች በተቀጠሩ ወይም በተመደቡ በ45 ቀናት ውስጥ ሲሆን፥ ለእድሳት ደግሞ የመጀመሪያ ምዝገባ ካስመዘገቡ በኋላ በ2.5 (በሁለት ዓመት ከአምስት ወር) መሆኑን በመግለጫው አንስተዋል።
አቶ ይልቃል አክለውም ሀብት አስመዝጋቢዎች በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ሀብታቸውን ሳያስመዘግቡ ከቀሩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1000 ብር ይቀጡና በ30 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል ብለዋል። በመደበኛም ሆነ በተራዘመላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ እና ትክክለኛ ሀብት ያላስመዘገቡ ካሉ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ እስራት የሚያስቀጣና ማንኛውም ያልተመዘገበ ሀብት የሚወረስ መሆኑን በመግለጫቸው ገልፀዋል።
በመጨረሻም አቶ ይልቃል የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ የሚካሄድባቸው ከወረዳ እስከ ክልል ባሉ ተቋማት በተመደቡ የሥነምግባር መኮንኖች፣ በደሴ፣ በጎንደርና ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና በክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሚካሄድ ሲሆን፥ ለሀብት ምዝገባው በየደረጃው የሚገኛው የተቋማት አመራሮች እገዛ ወሳኝ በመሆኑ በቅርበት ለሥነምግባር መኮንኖች የሀብት ምዝገባውን ሊያግዙና ሊያማክሩ ይገባል በማለት መልክታቸውን ማስተላለፋቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከ9 ሚሊየን ብር በላይ መንግስትን አሳጥተዋል የተባሉ ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ዓመታዊ ግብር ክፍያ መንግስትን አሳጥተዋል የተባሉ ግለሰቦች በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ እስከ 13 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ወሰነ።
የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ተከሳሾቹ 1ኛ በግል የስራ ተቋራጭ የሆኑት አብይ አማረ ዋሴ እና የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ የሒሳብ ባለሙያ የነበሩት ተረፈ ቦጃ ናቸው።
የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ የተሳትፎ ደረጃቸውን ጠቅሶ ሁለት የወንጀል ክሶችን በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ባጠቃላይ በ3 ተከሳሾች ላይ ክስ መመስረቱን መዘገባችን ይታወሳል።
ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 እና አንቀጽ 33 እንዲሁም ሙስናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 2 ላይ የተመላከተውን ድንጋጌ እና የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 203/2009 አንቀጽ 118 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ነበር።
በዚህም በአንደኛ ክስ በሁሉም ተከሳሾች ላይ የቀረበ ሲሆን፥ በሁለተኛው ክስ ላይ ደግሞ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ ነው የቀረበው።
በክሱ እንደተመላከተው 1ኛ ተከሳሽ የታክስ አስተዳደር አዋጁን በመተላለፍ ዓመታዊ የግብር ገቢ መክፈል ሲገባቸው የከፈሉ ለማስመሰል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ የተሰጠ የሚመስል ሀሰተኛ የኦሮሚያ ገቢዎች ሒሳብ ያልሆነ የባንክ ስሊፕ ማቅረባቸው በክስ መዝገቡ ላይ ተመላክቷል፡፡
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በመመሳጠር ያቀረቡትን ሐሰተኛ የባንክ ስሊፕ ሕጋዊነት ማረጋገጥ ሲገባቸው÷ ሳያረጋግጡ ሀሰተኛ ስሊፑን እና ሌሎች ሰነዶችን ትክክለኛነት ሳያረጋግጡ በመቀበል የገቢ ግብር ከፍለዋል በማለት የገቢ ደረሰኝ መስጠታቸው ተጠቅሷል፡፡
ከዚህም በኋላ ደግሞ ስራ ተቋራጩ ዓመታዊ ግብር ከነቅጣቱ እንደከፈሉ በማስመሰል ዓመታዊ ግብር ባለመክፈላቸው ምክንያት የተጣለባቸው የንብረት እግድ እንዲነሳላቸው በ3ኛ ተከሳሽ በኩል ለህግ ክፍል መጻፉም በክሱ ተጠቅሷል።
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ መንግስትን 9 ሚሊየን 292 ሺህ 127 ብር ከ83 ሳንቲም ገቢ አሳጥተዋል በማለት ዐቃቤ ሕግ ክስ አቅርቦባቸዋል።
ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ ዝርዝር ደርሷቸውና በችሎት በንባብ ከተሰማ በኋላ በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃላቸው ሰጥተዋል።
ይህን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ከ3 በላይ የሰው ምስክሮችን እና ሌሎች ገላጭና አስረጂ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።
የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን የመረመረው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን የመከላከያ ማስረጃ ያቀረቡ ሲሆን፥ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው አላስተባበሉም በማለት በፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
3ኛ ተከሳሽ የነበሩት የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ የግብር ክትትል ቡድን መሪ መንግስቱ ሙሉነህን በሚመለከት የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን አስተባብለዋል በሚል ከቀረበባቸው ክስ ነጻ ተብለዋል።
ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ እንዲሁም ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ አስተያየትን መርምሮ ዛሬ በዋለው የችሎት ቀጠሮ የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህም የተከሳሾችን የቅጣት አስተያየት በመያዝ 1ኛ ተከሳሽን ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በዕርከን 32 መሰረት በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ85 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል።
2ኛ ተከሳሽን በሚመለከት ፍርድ ቤቱ በአንድ አመት እስራትና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ የወሰነ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ በኩል ይግባኝ እንደሚጠይቅ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል።