Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ከፍ እንዲል ሁለንተናዊ የአመራር ብቃት የማይተካ ሚና አለው - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 13/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከፍ ለማድረግ ሁለንተናዊ የአመራር ብቃት የማይተካ ሚና እንዳለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ አስገነዘቡ።

ሁለንተናዊ የሥነ-ምግባር አመራር ላይ ያተኮረ ሥልጠና በምክር ቤቱ እየተሰጠ ነው።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ እንደገለፁት የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችን በተከታታይ አቅም በመገንባት ከህዝብ የተጣለባቸውን አደራ በብቃት እንዲወጡ በማድረግ ሀገርን ከፍ የሚያደርጉ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ይጠበቃል ብልዋል።

ስልጠናውን የሠጡት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ምሁር ታሪኩ ፉፋ(ዶ/ር) የኢትዮጵያን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከፍ ለማድረግ እና የህዝቡን ግንዛቤ ለማጎልበት የአመራር ብቃትን ማሳደግ ድርሻው የጎላ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በውስጡ ዕውነታን የተላበሰ አመራር ማፍራት እንዲቻል ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ተሞክሮዎችን በማጣቀስ የአመራር ብቃት ለአንድ ሀገር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል፡፡

ምክር ቤቱ ህግ አውጭ እንደመሆኑ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ሁለንተናዊ የሥነ-ምግባር አመራር ዘዴን መተግበር አጋዥ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

በሥልጠናው የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት የስራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ከ9 ሚሊየን ብር በላይ መንግስትን አሳጥተዋል የተባሉ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው

********

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 13/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ዓመታዊ ግብር ክፍያ መንግስትን አሳጥተዋል የተባሉ ግለሰቦች በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው።

የጥፋተኝነት ፍርዱን የሰጠው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ በግል የስራ ተቋራጭ የሆኑት አብይ አማረ ዋሴ እና የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ የሒሳብ ባለሙያ የነበሩት ተረፈ ቦጃ ናቸው።

የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ የተሳትፎ ደረጃቸውን ጠቅሶ ሁለት የወንጀል ክሶችን በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ባጠቃላይ በ3 ተከሳሾች ላይ ክስ መመስረቱን መዘገባችን ይታወሳል።

ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 እና አንቀጽ 33 እንዲሁም ሙስናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 2 ላይ የተመላከተውን ድንጋጌና የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 203/2009 አንቀጽ 118 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ነበር።

በዚህም በአንደኛ ክስ በሁሉም ተከሳሾች ላይ የቀረበ ሲሆን በሁለተኛው ክስ ላይ ደግሞ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ ነው የቀረበው።

በዚህም ክስ እንደተመላከተው 1ኛ ተከሳሽ የታክስ አስተዳደር አዋጁን በመተላለፍ ዓመታዊ የግብር ገቢ መክፈል ሲገባቸው የከፈሉ ለማስመሰል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ የተሰጠ የሚመስል ሀሰተኛ የኦሮሚያ ገቢዎች ሒሳብ ያልሆነ የባንክ ስሊፕ ማቅረባቸው ተመላክቷል፡፡

2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በመመሳጠር ያቀረቡትን ሐሰተኛ የባንክ ስሊፕ ሕጋዊነት እና የሌሎች ሰነዶችን ትክክለኛነት ሳያረጋግጡ በመቀበል የገቢ ግብር ከፍለዋል በማለት የገቢ ደረሰኝ መስጠታቸው ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ በኋላ ደግሞ ስራ ተቋራጩ ዓመታዊ ግብር ከነቅጣቱ እንደከፈለ በማስመሰል ዓመታዊ ግብር ባለመክፈላቸው ምክንያት የተጣለባቸው የንብረት እግድ እንዲነሳላቸው በ3ኛ ተከሳሽ በኩል ለህግ ክፍል መጻፉ በክሱ ተጠቅሷል።

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ መንግስትን 9 ሚሊየን 292 ሺህ 127 ብር ከ83 ሳንቲም ገቢ አሳጥተዋል በማለት ዐቃቤ ሕግ ክስ አቅርቦባቸዋል።

ተከሳሾቹ የቀረበባቸው ክስ ዝርዝር ደርሷቸውና በችሎት በንባብ ከተሰማ በኋላ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃላቸው በመስጠታቸው ዐቃቤ ሕግ የሰው ምስክሮችንና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን የመረመረው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ድንጋጌ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቶ ተከሳሾቹ የመከላከያ ማስረጃ ያቀረቡ ሲሆን 1ና 2ኛ ተከሳሾች ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው አላስተባበሉም በማለት ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ መስጠቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በዚሁ መዝገብ 1ኛ ተከሳሽ ዓመታዊ ግብር ባለመክፈላቸው ምክንያት የተጣለባቸው የንብረት ዕግድ እንዲነሳላቸው ለህግ ክፍል ደብዳቤ በመጻፍ ዕግዱን አስነስቷል ተብሎ ተከሶ የነበረው የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ የቀድሞ የግብር ክትትል ቡድን መሪ መንግስቱ ሙሉነህ በሚመለከት ግን ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ማስረጃ ተከላክሏል ብሎ በነጻ አሰናብቶታል።

በነጻ የተሰናበተውን ተከሳሽን በሚመለከት ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የመረጃ ክትትልና ትንተና ቡድን መሪ አቤል ጌታቸው በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 14/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቀድሞ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የመረጃ ክትትል እና ትንተና ቡድን መሪ አቤል ጌታቸው እና በግል ሥራ የሚተዳደሩት አቶ ፉፋ ዳባ ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ተወሰነ።

የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ሁለት ክሶችን አቅርቦ ነበር።

አቤል ጌታቸው በተባለው ግለሰብ ላይ የቀረበው ክስ ተከሳሹ የሙስና ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 እና ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተጠቀሰውን ድንጋጌ ተላልፏል የሚል ነው።

ሁለተኛ ተከሳሽን ፋፋ ዳባን በሚመለከት ደግሞ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ሕጋዊ አድርጎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ ፣ ስር ያለውን ድንጋጌ በመተላለፍ የሚል ክስ ነው የቀረበው።

አቶ አቤል ጌታቸው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ውስጥ የመረጃ ክትትልና ትንተና ቡድን መሪ ሆነው ሲሰሩ የተቋሙን አሰራር ባልተከተለ መልኩ የባለሃብቶችንና የድርጅቶችን የባንክ ሒሳብ አስቀድሞ በማጥናትና መረጃ በመውሰድ በተለያዩ ጊዜያት ለባለሃብቶች ስልክ በመደወል በአካል በማግኘት ገንዘብ እንዲከፍሉ በመጠየቅ የማይከፍሉ ከሆነ ደግሞ የፋይናንስ እንቅስቃሴያቸውን በተመለከተ ለፖሊስ በማስተላለፍ የወንጀል ክስ እንደሚመሰረትባቸው በመግለጽ አስፈራርተዋል በማለት ነው ዐቃቤ ሕግ በክሱ የጠቀሰው።

በዚህ መልኩ ተከሳሹ በ2013 እና በ2014 ዓ.ም በተለያዩ ጊዜያት ባለሃብቶችን በማስፈራራት ከ3 ግለሰቦች 3 ሚሊየን 70 ሺህ ብር ገንዘብ ፉፋ ዳባ በተባለው 2ኛ ተከሳሽ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘቡ ገቢ እንዲደረግ በማድረግ በዋና ወንጀል አድራጊነት ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ ሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት ነበር።

ሁለተኛ ተከሳሽ ፉፋ ዳባን በሚመለከት ደግሞ በወንጀል የተገኘ 3 ሚሊየን 70 ሺህ ብር የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቁ የገንዘቡን ምንጭ ለመደበቅ በስሙ በባንክ የገባውን ገንዘብ በተለያዩ መጠን በመጠቀም ሕገ ወጥ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሚል ክስ በዐቃቤ ሕግ ቀርቦበታል።

በዚህ መልኩ ክሱ ለተከሳሾች የክስ ዝርዝሩ ደርሷቸው በችሎት በንባብ ተሰምቷል።

ከዚህም በኋላ ተከሳሾች የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በዐቃቤ ሕግ የቀረቡ አምስት የሰው ምስክሮችን ቃል እና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በተከሰሱበት ድንጋጌ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።

ይሁንና ተከሳሾቹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል አለመቻላቸውን ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ ከዚህም በኋላ የግራ ቀኝ የቀረቡ የቅጣት ማክበጃና የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን መርምሯል።

በዚህም አንደኛ ተከሳሽ አቶ አቤልን በሚመለከት በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በሰላም ማስከበር ረገድ እንዲሁም በበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ጨምሮ አጠቃላይ ያቀረበውን የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 86 እና በአንቀጽ 82 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) መሰረት አጠቃላይ 7 የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን ፍርድ ቤቱ ይዞላቸዋል።

ሁለተኛ ተከሳሽ ፉፋ ዳባን በሚመለከት ደግሞ ለሕዳሴ ግድብ ያበረከቱትን የቦንድ ግዢ ጨምሮ አጠቃላይ 5 የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶች ተይዞላቸዋል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የቅጣት ማክበጃ አስተያየት ያቀረበ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በዝቅተኛ ደረጃ በመያዝ አንደኛ ተከሳሽን በዕርከን 16 መሰረት በ3 ዓመት ጽኑ እስራትና በ1 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

ሁለተኛ ተከሳሽ ፉፋ ዳባ ደግሞ በዕርከን 22 መሰረት በ5 ዓመት ከ 6 ወራት ጽኑ እስራት እና በ6 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሥነምግባርን የተላበሰ አመራር የግልፀኝነትንና የተጠያቂነትን መርህ ተግባራዊ በማድረግ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የሚታገልና ለሀገር እድገት በትኩረት የሚሰራ ነው!

****************

ሥነምግባርን የተላበሰ አመራር መገለጫዎች

 ህጎችን በትክክል ተግባራዊ ያደርጋል፥
 ሌብነትንና አግበስባሽነትን ይፀየፋል፥
 ለሥሙ ይጠነቀቃል፥
 የእኔ ይቅደም ከማለት ይልቅ የሀገር ጉዳይን ያስቀድማል፥
 ለሐገር እድገት በትኩረት ይሰራል፥
 ሰዎችን በአግባቡ ያገለግላል፥
 የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህን፥ ተግባራዊ የደርጋል፥
 የተቋሙን አላማ በትክክል ያስፈጽማል፥
 ሙስናን በጽኑ ይታገላል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽኑ የሙስና ሥጋት ባለባቸው ስድስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲያካሄድ የቆየዉን የሙስና መከላከል ጥናት ግኝት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 14/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና ሥጋት ባለባቸው ስድስት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ባካሄደዉ የሙስና መከላከል ጥናት ግኝት ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በይርጋለም ከተማ ምክክር አድርጓል፡፡

ጥናቱ የተካሄደባቸው ስድስቱ ርዕሰ ጉዳዮች በክልሉ በስራ እድል ፈጠራ፣ በገቢ አሰባሰብ ሂደት፣ በሰራተኞች ዝዉዉርና ቅጥር፣ በፋይናንስና ግዢ፣ በትምህርት ቤቶች ገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም እንዲሁም የመድሀኒት አቅርቦትና ስርጭት ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ያላቸዉን ተጋላጭነት ለይቶ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ለችግሩም መንስኤ የሆኑትን መለየት መቻሉ ተገልጿል፡፡

የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋዉ ጎነሳ መንግስት የጀመረዉን የኢኮኖሚ፣ የእድገት፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዞ ለማስቀጠል በየደረጃዉ ካሉ አካላት ጋር ሰፋፊ ስራ እየተከናወነ መቆየቱን ገልፀዋል።

አቶ አስፋዉ አያይዘዉም እንደሀገር ሙስና እና ብልሹ አሰራር በሀገር ላይ የሚያደርሰዉን አሉታዊ ተጽእኖ ለመታገል ሰፊ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዉ፤ እንደክልላችንም ኮሚቴ በማዋቀር የህዝብንና የመንግስትን ሀብት ለመመዝበር በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ጠንካራ ህጋዊ፣ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ የእርምት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ አስፋው የሀገር ልማትና እድገት አደናቃፊ የሆነዉን ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በህብረት ልንታገል ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የክልሉ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ በበኩላቸዉ ኮሚሸኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጀምሮ የሙስና ወንጀል ተከስቶ ሲገኝ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የበኩሉን ሲወጣ መቆየቱን ተናግረዋል።

በመድረኩም ሁሉም የሙስና መከላከል ጥናት ግኝቶች ቀርበው ከመድረኩ ተሳታፊዎች ጋር ምክክር በማካሄድ ጥናቱ ከተካሄደባቸው ተቋማት ጋር የትግበራ የዉል ስምምነት መካሄዱን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡