Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ሀሰተኛ ሰነዶችን በማጋለጥ የፀረ-ሙስና ትግሉን እናጠናክር !

****

በመንግስት ተቋማት፣ በልማት ድርጅቶች እና ህዝባዊ ተቋማት ያጋጠመዎትን ሙስና እና ብልሹ አሰራር በመጠቆም የዜግነት ግዴታውን ይወጡ!

የሙስና እና ብልሹ አሰራር ድርጊቶች ካጋጠመዎት👇

በኮሚሽኑ ሀገራዊ የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et

በኮሚሽኑ የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et

በኮሚሽኑ ስልክ ቁጥር፦ 09 35 94 75 33 ወይም ካዛንቺስ ከልማት ባንክ ጉን በሚገኘው የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 2ኛ ወለል/ፎቅ በአካል ተገኝተው ጥቆማ ማቅረብ ይችላሉ።

ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ፣ መብትዎትን ያስከብሩ!
በመልካም ሥነምግባር የታነጸ አመራር ማፍራት ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት መሰረት ይሆናል!

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ኃላፊዎችና ሰራተኞች ሀብታቸውን ማስመዝገባቸው ተገለፀ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 13/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በክልሉ ውስጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ለመለየት ማንኛውም የመንግስት ተሿሚ፣ የህዝብ ተመራጭ እና ምዝገባው የሚመለከታቸውን የመንግስት ሰራተኞች በመጀመሪያ እና በዳግም ምዝገባ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለትም የኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ባለሙያዎች በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ በመገኘት የተቋሙን ኃላፊዎችና ሰራተኞች በመጀመሪያ ምዝገባ እና በዳግም ምዝገባ ሀብታቸውን ማስመዝገብ መቻላቸው ተገልጿል።

በዚህ ወቅት የኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ባለሙያዎች እንደገለፁት በሌሎች ተቋምም ቁጥራቸው 30 እና ከዛ በላይ የሆኑ ሀብት ማስመዝገብ የሚችሉ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ካሉ የሀብት ምዝገባ ቅጹን በመያዝ በስራ ቦታቸው ድረስ በመገኘት የሀብት መመዝገብ ስራ እንደሚያከናውኑ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ከፍ እንዲል ሁለንተናዊ የአመራር ብቃት የማይተካ ሚና አለው - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 13/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከፍ ለማድረግ ሁለንተናዊ የአመራር ብቃት የማይተካ ሚና እንዳለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ አስገነዘቡ።

ሁለንተናዊ የሥነ-ምግባር አመራር ላይ ያተኮረ ሥልጠና በምክር ቤቱ እየተሰጠ ነው።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ እንደገለፁት የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችን በተከታታይ አቅም በመገንባት ከህዝብ የተጣለባቸውን አደራ በብቃት እንዲወጡ በማድረግ ሀገርን ከፍ የሚያደርጉ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ይጠበቃል ብልዋል።

ስልጠናውን የሠጡት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ምሁር ታሪኩ ፉፋ(ዶ/ር) የኢትዮጵያን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከፍ ለማድረግ እና የህዝቡን ግንዛቤ ለማጎልበት የአመራር ብቃትን ማሳደግ ድርሻው የጎላ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በውስጡ ዕውነታን የተላበሰ አመራር ማፍራት እንዲቻል ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ተሞክሮዎችን በማጣቀስ የአመራር ብቃት ለአንድ ሀገር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል፡፡

ምክር ቤቱ ህግ አውጭ እንደመሆኑ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ሁለንተናዊ የሥነ-ምግባር አመራር ዘዴን መተግበር አጋዥ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

በሥልጠናው የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት የስራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡