Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
በክልሉ ያለ ደረሰኝ ግብይት የሚፈፅሙ 117 ግብር ከፋዮችና የሥነምግባር ጉድለት ያሳዩ 28 ባለሙያዎች ተጠያቂ ተደርገዋል - ዘይኔ ቢልካ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 10/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያለ ደረሰኝ ግብይት የሚፈፅሙ 117 ግብር ከፋዮችና የሥነምግባር ጉድለት ያሳዩ 28 ባለሙያዎች ላይ ህጋዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘይኔ ቢልካ ገልጸዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የተቋሙን የ6 ወራት የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክተው ለደሬቴድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የክልሉን የገቢ አቅም ለማሳደግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ 91 ሺህ ግብር ከፋዮች ያሉ ሲሆን፥ ከነዚህም መካከል 90 ሺህ 479ኙ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ግብር መክፈል ችለዋል። በቅንጅት በተሠራው የገቢ ማሰባሰብ ሥራ በግማሽ አመቱ 85 በመቶ አፈፃፀም መመዝገቡንም ኃላፊው ገልፀዋል።

ደረሰኝ የመስጠትና የመቀበል ባህል አለመዳበሩ በገቢ አሰባሰብ ሂደቱ ያጋጠመ ችግር ነው ብለዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተደረገው ክትትል በክልሉ 140 ግብር ከፋዮች የደረሰኝ ጉድለት የተገኘባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

እስከአሁን ድረስ 117 የሚሆኑትን በህግ ተጠያቂ ማድረግ መቻሉንም አስታውቀዋል።

በሥነምግባር ጉድለትና ከተለያዩ የብልሹ አሰራር ጥሰቶች ጋር ተያይዞ 28 ባለሙያዎችም ተጠያቂ ተደርገዋል ብለዋል አቶ ዘይኔ በመግለጫቸው። ባለሙያዎቹ ከአንድ ወር እስከ አራት ወር የደመወዝ ቅጣትና ከሥራ እስከ ማሰናበት ድረስ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነው ያሉት።

አመራሩ በቀጣይ ሳምንት ውስጥ በገቢ አሰባሰብ ሂደት በተለይም ከደረሰኝ ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን የብልሹ አሰራር ችግር ለማረም እና ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ ከደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች ጋር እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

የገቢ ሥርዓትን በቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረግ በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት መሆኑን ኃላፊው በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የፍትህ እጆች ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዱ መሆን አለባቸው!

****

በመንግስት ተቋማት፣ በልማት ድርጅቶች እና ህዝባዊ ተቋማት ያጋጠመዎትን ሙስና እና ብልሹ አሰራር በመጠቆም የዜግነት ግዴታውን ይወጡ!

የሙስና እና ብልሹ አሰራር ድርጊቶች ካጋጠመዎት👇
በኮሚሽኑ ሀገራዊ የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
በኮሚሽኑ የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
በኮሚሽኑ ስልክ ቁጥር፦ 09 35 94 75 33 ወይም ካዛንቺስ ከልማት ባንክ ጉን በሚገኘው የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 2ኛ ወለል/ፎቅ በአካል ተገኝተው ጥቆማ ማቅረብ ይችላሉ።

ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ፣ መብትዎትን ያስከብሩ!
እንኳን ለከተራና ጥምቀት በዓል አደረሣችሁ!

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የቀድሞ የአ/አ ከተማ ከንቲባ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር እነ ኤልቤቴል ሀብቴ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል 10 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ተፈቀደ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 10/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀድሞ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር እነ ኤልቤቴል ሀብቴ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል 10 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቀደ።

ተጠርጣሪዎቹ የቀድሞ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር ኤልቤቴል ሀብቴ እና የፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር ፍቅሩ ኦላና እንዲሁም በግል ስራ ይተዳደራሉ የተባሉት ቅዱስ መስፍን፣ አማኑኤል መስፍንና ተክሌ ከቡ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።

ችሎቱ ከዚህ በፊት በሰጠው የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ውስጥ በፖሊስ የተሰሩ የምርመራ ውጤቶችን ተመልክቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ከዚህ በፊት በተሰጠው 14 ቀናት ውስጥ በርካታ ማስረጃዎችን ማሰባሰቡን፣ በተጠርጣሪዎቹ ስም የተንቀሳቀሱ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ እንቅስቃሴን የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት ማቅረቡን፣ የአራት የሰው ምስክርና የተጠርጣሪዎችን ቃል መቀበሉን አብራርቷል።

በተጨማሪም የዋጋ ግምቱ 2 ሚሊዮን 500 ሺህ የሆነ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2 (B) 81421 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪን ለስራ ተገልግለን እንመልሳለን በሚል ምክንያት መወሰዱን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ፤ የሞተርና የሻንሲ ቁጥርን በመለወጥ አዲስ በማስመሰል ሀሰተኛ ዲክላራሲዮን በማዘጋጀት የሰሌዳ ቁጥሩ ተቀይሮ ለሌላ ግለሰብ ተላልፎ መሸጡን የሚያመላክት አዲስ የምርመራ ግኝት መገኘቱን ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪማ ወንጀሉ የተፈጸመው በአንደኛ ተጠርጣሪ ስም ኬኬ የመኪና አስመጪ በሚል በተመሰረተ ድርጅት ስም መሆኑን ፖሊስ ጠቅሶ ይህን ድርጅት በሚመለከት ማስረጃ የማሰባሰብ ስራ እንደሚቀረው አብራርቷል።

በአጠቃላይ ወንጀሉ የተፈጸመው በቡድን መሆኑን የጠቀሰው መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምስክር ቃል ለመቀበልና ቀሪ የምርመራ ስራ ለማከናወን ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጾ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸ የፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ ምክንያቶች ተጠርጣሪዎችን በእስር ለማቆየት የሚያስችሉ አይደሉም በሚል የመከራከሪያ ነጥቦችን አንስተዋል።

ተሽከርካሪ ታርጋ ተቀይሮ ሀሰተኛ ዲክላራሲዮን ተዘጋጅቶ ለሌላ ግለሰብ ተሽጧል የተባው አዲስ ግኝትን በሚመለከት ማን ለማን ሸጠ የሚለውን ተለይቶ አልቀረበም በሚል ተከራክረዋል።

1ኛ፣ 2ኛ እና 5ኛ ተጠርጣሪዎችን በሚመለከት የ1ኛ ተጠርጣሪ ወንድም በህግ እንዳይጠየቅ ወደ ግል ተበዳዮች ስልክ በመደወል በቀነኒሳና ደሳለኝ ሆቴሎች ውስጥ ስብሰባ እየጠሩ ''አርፋችሁ ተቀመጡ ለዕቃ ማስመጫ ተብሎ ስለተወሰደው 47 ሚሊዮን 345 ሺህ ብር ጉዳይ እንዳታነሱ” እያሉ ያስፈራሯቸው ነበር በማለት ፖሊስ ያቀረበው ነጥብን በሚመለከት በተጠርጣሪ ጠበቆች በኩል ሆቴል የጠሯቸው ለማስፈራራት ሳይሆን ለሽምግልና ነው በሚል ተከራክረዋል።

በተጨማሪም የተጠርጣሪ ጠበቆች የፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ምክንያቶች ላይ የተጠርጣሪ ተሳትፎ ተለይቶ አልቀረበም በማለት የተከራከሩ ሲሆን የፖሊስ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

ከዚህም ባሻገር ጠበቆቹ ከግል ተበዳዮች የተወሰደ ገንዘብን ለማስመለስ ነው በፖሊስ እየተሰራ ያለው የሚል ገለጻ ማቅረባቸውን ተከትሎ በፖሊስ በኩል መልስ ተሰጥቷል።

በዚህም መርማሪ ፖሊስ የግል ተበዳይን ገንዘብ የማስመለስ ስራ የኛ ሚና አይደለም በማለት ተጠርጣሪዎቹ በቡድን በመሆን የሙስናና የማታለል ወንጀል ፈጽመዋል በተባሉበት ጉዳይን በሚመለከት ተገቢውን የምርመራ ስራ እያከናወነ ማስረጃም እያሰባሰበ እንደሚገኝ አብራርቶ መልስ ሰጥቷል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን እና የፖሊስን የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የመረመረው ችሎቱ ከወንጀሉ ውስብስብነት አንጻር ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ለፖሊስ መሰጠት እንዳለበት በማመን የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ እንደሚያስፈልገው በማመን 10 ቀናት የምርመራ ማጠቃለያ ጊዜ ለፖሊስ መፍቀዱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ ሰነዶችን በማጋለጥ የፀረ-ሙስና ትግሉን እናጠናክር !

****

በመንግስት ተቋማት፣ በልማት ድርጅቶች እና ህዝባዊ ተቋማት ያጋጠመዎትን ሙስና እና ብልሹ አሰራር በመጠቆም የዜግነት ግዴታውን ይወጡ!

የሙስና እና ብልሹ አሰራር ድርጊቶች ካጋጠመዎት👇

በኮሚሽኑ ሀገራዊ የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et

በኮሚሽኑ የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et

በኮሚሽኑ ስልክ ቁጥር፦ 09 35 94 75 33 ወይም ካዛንቺስ ከልማት ባንክ ጉን በሚገኘው የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 2ኛ ወለል/ፎቅ በአካል ተገኝተው ጥቆማ ማቅረብ ይችላሉ።

ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ፣ መብትዎትን ያስከብሩ!
በመልካም ሥነምግባር የታነጸ አመራር ማፍራት ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት መሰረት ይሆናል!

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ኃላፊዎችና ሰራተኞች ሀብታቸውን ማስመዝገባቸው ተገለፀ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 13/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በክልሉ ውስጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ለመለየት ማንኛውም የመንግስት ተሿሚ፣ የህዝብ ተመራጭ እና ምዝገባው የሚመለከታቸውን የመንግስት ሰራተኞች በመጀመሪያ እና በዳግም ምዝገባ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለትም የኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ባለሙያዎች በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ በመገኘት የተቋሙን ኃላፊዎችና ሰራተኞች በመጀመሪያ ምዝገባ እና በዳግም ምዝገባ ሀብታቸውን ማስመዝገብ መቻላቸው ተገልጿል።

በዚህ ወቅት የኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ባለሙያዎች እንደገለፁት በሌሎች ተቋምም ቁጥራቸው 30 እና ከዛ በላይ የሆኑ ሀብት ማስመዝገብ የሚችሉ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ካሉ የሀብት ምዝገባ ቅጹን በመያዝ በስራ ቦታቸው ድረስ በመገኘት የሀብት መመዝገብ ስራ እንደሚያከናውኑ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡