Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.87K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
በመኪና መንገድ ዘግተው በማስቆም እና ድብደባ በመፈፀም ገንዘብ ወስደዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችና የፌደራል ፖሊስ አባል ላይ ክስ ተመሰረተ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በመኪና መንገድ ዘግተው በማስቆም እና ድብደባ በመፈፀም 112 ሺህ ገንዘብ ወስደዋል ተብለው የተጠረጠሩት 5 ግለሰቦች እና አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ላይ ክስ ተመሰረተ።

1ኛ ተከሳሽ ዋ/ሳጅን ሰለሞን ሐብታሙ የፌዴራል ፖሊስ አባል እና የፖሊስ ፓትሮል ሹፌር፣ 2ኛ ተከሳሽ እሱባለው ምህረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ጽ/ቤት ሹፌር፣ 3ኛ ተከሳሽ ረ/ኢ/ር አዲሱ ደርበው የቀድሞ ፌዴራል ፖሊስ አባል፣ 4ኛ ተከሳሽ ምስጋናው ጌታቸው እና 5ኛ ተከሳሽ ጌታዬ ጥላሁን እንዲሁም 6ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ አዱኛ በግል ስራ የሚተዳደሩ ናቸው።

በ02/04/2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው ወይራ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ፤ ተከሳሾች በጋራ በመሆን የግል ተበዳዮች ወደያዙት ተሽከርካሪ በመምጣት እና ከፊት ለፊት መንገዱን በመዝጋት የግል ተበዳዮችን እንዳስቆሟቸው የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ቀጥሎም የግል ተበዳዮቹን ሕገወጥ መሳሪያ ትነግዳላችሁ ብለው በማዋከብ እና ድብደባ በመፈፀም ይዘውት በመጡት መኪና ወደሌላ ስፍራ ይዘዋቸው በመሄድ አጠቃላይ ግምቱ 112 ሺህ ብር የሚያወጣ ንብረትና ጥሬ ገንዘብ በመውሰድ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል ነው የሚለው የፍትህ ሚኒስቴር አቃቤህግ ክስ፡፡

ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት ስልጣንን አላግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 3ኛ የፀረ-ሙስና ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ክሱን በነገው ዕለት እንደሚመለከተው ታውቋል፡፡

ተከሳሾች ከቀን 03/04/2016 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሀሰተኛ ሰነዶች ግለሰቦች ሳያውቁ ቤታቸውን ለመሸጥ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የተቀበለው ተከሳሽ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ግለሰቦች ሳያውቁ ቤታቸውን ለመሸጥ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ተቀብሏል የተባለው ተከሳሽ በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ወሰነ።

በአ/አ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ኗሪና በግል ስራ የሚተዳደረው ተካ ዲኖ ሰይድ የሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 2(ሀ) እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በተዘጋጁ ሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነዶች መገልገል የሙስና ወንጀል እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦበት ነበር።

ከቀረቡበት ክሶች መካከል ተከሳሹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት፤ ለሌሎችም ለማስገኘት በማሰብ በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም ከስንታየው አበበ አወቀ ያልተሰጠውን ሀሰተኛ የውክልና ሰነድ፤ ሃሰተኛ የመሬት ይዞታ መብት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እና ሃሰተኛ ያላገባ የምስክር ወረቀት በመጠቀም በፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጽ/ቤት አቅርቦ ሽያጭ ውል መፈጸሙ ተመላክቷል።

በፈጸመው የሽያጭ ውል መሰረት ደግሞ በስንታየው አበበ ስም ተመዝግቦ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የሚገኘውን የቦታው ስፋት 94 ነጥብ 64 ካ/ሜትር የሆነ ጅምር የመኖሪያ ቤት ለግል ተበዳይ እንዳለ መኩሪያ ለመሸጥ በመስማማት በቅድሚያ 5 ሚሊየን 100 ሺህ ብር በባንክ ሂሳቡ እንዲገባለት በማድረግ እና የገባለትንም ገንዘብ ወደ ተለያዩ ግለሰቦች ሂሳብ በማስተላለፍ በሃሰት በተዘጋጁ መንግስታዊ ሰነዶች መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡

በሁለተኛው ክስ ደግሞ ተከሳሹ ንብረትነቱ የአሊ ሃይረዲን መሃመድ የሆነ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር አዲስ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤት ለመሸጥ እንዲያስችለው በሃሰተኛ የተለያዩ ሰነዶችን በመጠቀም ከባለንብረቱ ያልተሰጠውን ውክልና እንደተሰጠው በማስመሰል ከመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ያልተሰጠ ተመሳስሎ የተዘጋጀ የመሬት ይዞታ መብት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ኮፒ እና ከኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ወሳኝ ኩነት የተሰጠ የሚል ሃሰተኛ የባለንብረቱ ያላገባ የምስክር ወረቀት ቅጂ በማቅረብ ቤቱን በ40 ሚሊየን ብር ለግል ተበዳይ እድሪስ ቡንሱር አብደላ ለመሸጥ መስማማቱ በክሱ ተጠቅሷል።

በግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም ደግሞ የመንደር ሽያጭ ውል የተፈረመ ቅድሚያ ክፍያ 10 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር ከግል ተበዳይ እድሪስ ቡንሱር የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ቤተል ቅርንጫፍ ወደ ተከሳሽ የባንክ ሂሳብ ዝውውር የተፈጸመለት መሆኑም በክሱ ተጠቅሷል።

በአጠቃላይ ተከሳሽ ከአሊ ሃይረዲን ያልተሰጠውን ውክልና ሰነድ፣ ሃሰተኛ የመሬት ይዞታ መብት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እና ሃሰተኛ ያላገባ የምስክር ወረቀት በማቅረብና የሽያጭ ውል በመፈጸም 10 ሚሊየን 500 ሺህ ብር በባንክ ሂሳቡ እንዲገባለት በማድረግና ገንዘቡን ወደተለያዩ ግለሰቦች ሂሳብ በማስተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሱ እና ለሌሎችም ያስገኘ በመሆኑ በፈጸመው በሃሰት በተዘጋጁ መንግስታዊ ሰነዶች መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡

ከ4ኛ እስከ 5ኛ ባሉ ክሶች ላይ ደግሞ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ ግለሰቦች በባንክ ሂሳቡ የገባለትን ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ለመደበቅ እና ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ በማሰብ ገንዘቡን በተለያዩ ግለሰቦች ስም በተለያዩ መጠኖች በማስተላለፍ እንዲሁም በራሱ ስም ደግሞ በባንክ በተከፈተ ሂሳቡ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ያስተላለፈ መሆኑ ተጠቅሶ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል ተከሶ ነበር።

ተከሳሹ በዚህ መልኩ የቀረቡበት የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የሰጠውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን የመረመረው ችሎቱ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም ማስረጃዎቹን ማስተባበል ባለመቻሉ ተከላከል በተባለበት ድንጋጌ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ዐቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ አስተያየት፤ በተከሳሹ በኩል ደግሞ ሰባት የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በጽሁፍ ቀርበዋል።

የግራ ቀኙን አስተያየት የመረመረው ፍርድ ቤቱ ሰባት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 30 መሰረት ተከሳሹ በ11 አመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ለተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ሥነምግባራዊ አመራርን በማጎልበት ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በብሔራዊ ቤተ-መዛግብት እና ቤተ-መፃህፍት አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡

ሙስናን የመከላከል እና የመግታት ጥረት በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን የተቋሙ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች በሥነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ግንዛቤ በመያዝ ግልጸኝነትን እና ተጠያቂነትን ተላብሰው እንዲሰሩ ለማስቻል ያለመ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል፡፡

በስልጠናው ሙስና እና ብልሹ አሰራር በኢትዮጵያ አብዝቶ መንሠራፋቱንና ለዚህም ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች መካከል በአመራሩ ዘንድ በሥነ-ምግባር ዙሪያ የጠራ ግንዛቤ፣ ስልጠና እና ክትትል አለመኖር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሰዓቱ ምላሽ ያለማግኘት፣ በተቋም ውስጥ ችግሮች በሚከሰቱበት ወቅት የችግሩ መነሻ ምክንያት ከስሩ አለማወቅ ዋነኛ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

ስልጠናው በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ባለሙያ የተሰጠ ሲሆን፥ በዛሬው ዕለት የተሰጠው ስልጠና በሥነ-ምግባር ምንነት፣ ጽንሰ ሃሳብ፣ መርሆዎች እና አስፈላጊነት ዙሪያ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

ስልጠናው በነገው እለትም ሙስና እና የአመራር ሥነ-ምግባር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሚቀጥል እንደሚሆን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ህፃናትንና ወጣቶችን በመልካም ሥነምግባር ማነፅ በሙስና የፀዳች ሀገር ለመገንባት መሠረት ነው!

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡