የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕከል ከተሞችን የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት የማዘመኑ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 7/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕከል የሆኑ የስድስት ከተሞችን የመሬት መሬጃ አያያዝ ስርዓት የማዘመኑ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።
የከተሞች የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት ማዘመን መሬት ለህገ-ወጥ ተግባር ተጋላጭ እንዳይሆንና ነዋሪዎች ላፈሩት ሀብት ዘላቂ ዋስትና እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተመልክቷል።
ክልል አቀፍ የከተሞች ንቅናቄ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደበት ውቅት የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንዳሉት፤ በክልሉ ከተሞች የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት ባለመዘመኑ ለህገ-ወጥ ተግባራት ሲጋለጥ ቆይቷል።
በዚህም ምክንያት የክልሉ መንግስት የከተሞችን ልማት በማፋጠን የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት እያደናቀፈ ይገኛል ብለዋል።
የመሬት አስተዳደር ስርዓትን ለማዘመን ቀደም ሲል ጥረት ቢደረግም የሚፈለገው ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን ጠቅሰው፤ የከተማ መሬት በአግባቡ በመለየትና በመመዝገብ ችግሩን ማቃለል እንደሚቻል ተናግረዋል።
ለዚህም እስከ መጪው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የክልሉ ማዕከል የሆኑት ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ዲላ፣ ጂንካ፣ ሳውላና ካራት ከተሞች የሚገኝ ማንኛውም የመሬት መረጃ ስርዓት ማዘመን የሚያስችል መመሪያ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ለመግባት የክልሉ መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የክልሉ ማዕከል ከተሞችን የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት የማዘመኑን ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተካሄደ ያለውን ስራ ለማሳካት የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከተሞችን የብልጽግና ማዕከል ለማድረግ የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ጠቁመው፤ የአመራር አባላት በውጤት የታጀበ ስራ በማከናወን የታሪክ ተወዳሽ ለመሆን በቁጠኝነት መምራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በክልሉ ጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ ከንቲባ አቶ ታምራት ተሰማ በበኩላቸው፤ እስካሁን የነበረው የከተማ መሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት ችግሮችን በዘላቂነት የሚፈታ ሆኖ ባለመገኘቱ ህገ-ወጥነት እየተስፋፋ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በሊዝ የተላለፉና ነባር ይዞታዎች እንዲሁም በማስፋፊያ አካባቢዎች የሚገኙ የመሬት ምዝገባ ስርዓት ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
እስከ ሰኔ 30 ለዲጅታል መረጃ ስርዓት መሠረት የሚሆን የማኑዋል መረጃ ስራ እናጠናቅቃለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የአመራር አባላት ቁርጠኛ ያለመሆንና ደላሎች በሚፈጥሯቸው ችግሮች ምክንያት አጠቃላይ የመሬት አስተዳደር ስርዓቱ ማዘመን አለመቻሉን የገለጹት ደግሞ የወላይታ ሶዶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ዮናስ ናቸው።
በነበረው የሶዶ ከተማ መሬት መረጃ በካዳስተር 10 በመቶ ብቻ መያዝ መቻሉን ጠቅሰው፤ የክልሉ መንግስት በያዘው አቋም ልክ የከተማ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት ለማዘመን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እስከ ሰኔ 30 ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል።
የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት ማዘመን መሬት ለህገ-ወጥ ተግባር ተጋላጭ እንዳይሆን የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ ነዋሪዎች ላፈሩት ሀብት ዘላቂ ዋስትና የሚሰጥና የገቢ አሰባሰብን በማሻሻል የከተሞችን ዕድገት ለማፋጠን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተመልክቷል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው የፍርድ ቤት ዳኛ ላይ ለተጨማሪ ማጣሪያ 14 ቀን ተፈቀደ
*****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 7/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው የፍርድ ቤት ዳኛ ላይ ለተጨማሪ ማጣሪያ 14 ቀን መፈቀዱ ተገለጸ፡፡
ለፖሊስ የተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።
ተጠርጣሪው የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ እና የኢንስፔክሽን ኃላፊ የሆነው ተስፋዬ ደረጄ ረጋሳ የሚባል ሲሆን ÷ የአዲስ አበባ ፖሊስ መርማሪ የተጠረጠረበት መነሻን ዛሬ ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አብራርቷል።
በዚህም የአቢሲኒያ ባንክ መስቀል ፍላወር ቅርጫፍ ስራ አስኪያጅ የነበረ እና በሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሀብተማርያም ገ/መስቀል የተባለ ግለሰብ መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ ቢሮ በእስር ላይ በነበረበት ወቅት ሚካኤል ታደሰ በተባለ ግለሰብ አማካኝነት ተጠርጣሪው በእስር ቤት በአካል በመሄድ ከተዋወቀው በኋላ ዳኛ መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩን እንደሚያስጨርስለት እና መዝገቡን የሚያዩለት ዳኞችን ስም ደውለህ ንገረኝ በማለት ስልክ ቁጥሩን ሰጥቶት መሄዱን ፖሊስ ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አብራርቷል።
ከዚህም በኋላ የግል ተበዳይን ጉዳይ የያዙት ዳኞች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሙስና ጉዳይ ችሎት ዳኞች መሆናቸውን ስማቸውንም ከግል ተበዳይ ጠይቆ ከተረዳ በኋላ ሀለቱ ዳኞች በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አብረውት የተማሩ መሆናቸውንና እንደሚያውቃቸው በመጥቀስ ፤ አንደኛውን ዳኛ ደግሞ የስራ ባልደረባዬ አለቃዬ ያውቀዋል በማለትና ነጻ እንደሚያስወጣው ያግባባው እና የተስፋ ቃል የሰጠው መሆኑን ፖሊስ ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ገልጿል።
ከዚህ በኋላ የግል ተበዳዩ ጉዳዩን በማረሚያ ቤት ሆኖ እንዲከታተል ታዞ ማረሚያ ቤት ከወረደ በኋላ ተጠርጣሪው '' አብረውኝ የተማሩ ዳኞቹን እያነጋገርኩልህ ነው፤ ከዳኞቹ ጋር ምሳ አብረን እየበላን ነው ፤ ነጻ እንደምትወጣም ነግረውኛል በማለት ''በስልክ ሲያናግረው እንደነበረ መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።
በተጨማሪም የግል ተበዳዩ በችሎት በቀጠሮ በሚቀርብበት ዕለት ተጠርጣሪው ችሎት ተገኝቶ ከግል ተበዳይ ኋላ በመቀመጥ ዳኞቹ እንዳዩት ለግል ተበዳይ በመናገር እንዲያምነው በማድረግ እና ዳኞቹ ጋር እየሄድኩ ጉዳይህን እንዳስፈጽም ለመንቀሳቀስ እንዲመቸኝ በማለት የግል ተበዳይ ንብረት የሆነውን ኮድ 2- 10944 የሆነ የቤት መኪና በመውሰድ 1 ዓመት ከ8 ወራት ተሽከርካሪውን ሲጠቀምበት እንደነበር ጠቅሶ ፖሊስ ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አብራርቷል።
ከዚህም በኃላ የግል ተበዳዩ ላይ ምስክር ተሰምቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ደግሞ ለዳኞቹ የሚሰጥ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር እንዲሰጠው በመጠየቅና አስቀድሞ ለቀብድ በሚል 400 ሺህ ብር በተጠርጣሪ ወንድም የንግድ ባንክ ሂሳብ መቀበሉን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ ፥ የግል ተበዳይ የጥፋተኝነት ፍርድ ከተሰጠበት በኋላ ደግሞ በገደብ እንድትወጣ አስደርግኃለው በማለት ተጨማሪ 400 ሺህ ብር እንዲሰጠው ጠይቆ በድርድር ላይ እያለ በደረሰ ጥቆማ ባሳለፍነው አርብ ጥር 3 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ገልጿል።
መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪ ዳኛውን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ የግል ተበዳይና የተጠርጣሪውን ቃል መቀበሉንና የተወሰኑ ማስረጃዎችን መሰብሰቡን ተናግሯል።
ቀሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሰብ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጾ በወ/መ/ስ/ህ/ቁ 59/1 መሰረት የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።
ተጠርጣሪው በበኩሉ ፥ በቁጥጥር ስር ሲውል በስራ ቦታ ላይ ሆኖ ካለፍርድ ቤት መያዣ መያዙን ጠቅሶ አቤቱታ አቅርቧል።
በተጨማሪም የተጠረጠረበት የወንጀል ድርጊትን አለመፈጸሙን በመግለጽ የግል ተበዳይ ጋር ዝምድና እንዳለውና የእህትማማች ልጆች ነን በማለት አብራርቷል።
በተጨማሪም በወንድሜ ሂሳብ የተቀበልኩት 400 ሺህ ብር ለግል ተበዳዩ ለጠበቃ ማቆሚያ የሚከፈል ነው በማለት ተከራክሯል።
የግል ተበዳይ ተሽከርካሪን በሚመለከት ደግሞ ገራጅ ገብቶ እንደነበር ጠቅሶ ፥ ለተሽከርካሪ የተለያዩ ወጪዎች የሚሆን 55 ሺህ ብር ከፍሎ ከገራጅ አውጥቶ ካቆመበት መኖሪያ ቤት ኢብሳ የሚባል ወንድሙ ወደ ወለጋ ተሽከርካሪውን ይዞ እንደሄደ ተጠርጣሪው ጠቅሶ ተከራክሯል።
ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የዋስትና መብቱን እንዲያከብርለትም ጠይቋል።
መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ÷ ተጠርጣሪው በችሎት የገለጻቸው ሁሉ ሀሰት እንደሆኑና ከግል ተበዳይም ጋር ምንም ዝምድና እንደሌላቸው መግለጹን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ተጠርጣሪው በሌላ ግለሰብ አማካኝነት በእስር ቤት ሄዶ የግል ተበዳይን ከተዋወቀው በኋላ ጉዳይህን አስፈጽማለሁ ፤ ነጻ አወጣሃለው ፤ ጉዳይህን ከያዙት ከዳኞች ጋር ምሳ እየበላሁ ነው ፤ ነጻ እንደሚያወጡህ ነግረውኛል በማለት ከግል ተበዳይ ጋር የተለዋወጠው የስልክ ልውውጥ ማስረጃ መኖሩን ጠቅሶ ፖሊስ መልስ ሰጥቷል።
በተጨማሪም ፖሊስ ተጠርጣሪው ምስክሮች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰ መሆኑን ጠቅሶ አመልክቷል።
የግራ ቀኙን ክርክር የተከታተለው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ምርመራው ጅምር ከመሆኑ አንጻር ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መስጠት እንደሚያስፈልግ በማመን የተጠርጣሪውን ዋስትና ጥያቄ ለጊዜው አለመቀበሉን ጠቅሶ የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ ፈቅዷል።

ልጆች በመልካም ሥነምግባር እንዲታነጹ የወላጅ ሚና የላቀ ነው!
****

የልማት ሥራ ውጤታማ እንዳይሆንና በገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ ማነቆ የሚፈጥሩ ከአመራሮች ጀምሮ እስከ ባለድርሻ አካላት ድረስ ብልሹ አሠራር ውሰጥ ሲገቡ በሕግ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል - የውይይቱ ተሳታፊዎች
********************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የልማት ሥራ ውጤታማ እንዳይሆንና በገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ ማነቆ የሚፈጥሩ ከአመራሮች ጀምሮ እስከ ባለድርሻ አካላት ድረስ ብልሹ አሠራር ውሰጥ ሲገቡ በሕግ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
የወላይታ ዞን መንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ተመስገን ዓለማየሁ በንቅናቄው መድረኩ ላይ በከተማው የስራ አጥነት ችግር፣ የኑሮ ውድነት እና የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የውስጥ ገቢ አሟጦ መሰብሰብና ህዝቡን ማሳተፍ ቁልፍ ነው ብለዋል።
የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ያለመዘመኑና በሀሰተኛ ደረሰኞች ምክንያት መገኘት የሚገባው ገቢ እንዳይገኝ ማነቆ ሆኖ መቆየቱን ተናግረዋል።
የአረካ ከተማ ከንቲባ አቶ ደመቀ ደጀኔ በበኩላቸው በከተሞች ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎቸን፣ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ሰፊ ርብርብ በማድረግ መሬት ላይ ለማውረድ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች በማዘመን እና ዲጂታላይዝ በማድረግ ለህብረተሰቡ የሚቀርብ አገልግሎት ተደራሽ፣ ፍታሃዊና ቀልጣፋ መሆን ይገባል ብለዋል፡፡
በልማት ሥራ ላይ ሥር ነቀል ውጤት ለማምጣት በገቢ አሰባሰብ በየደረጃው ካለው አመራር ጀምሮ እስከ ኅብረተሰብ ክፍል ድረስ ብልሹ አሠራር ውሰጥ ሲገቡ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል ብለዋል አስተያየት ሰጪዎች።
በከተሞች አካባቢ የሚስተዋሉ ብልሹ አሠራርን በማስወገድና ተጠያቂነትን በማስፈን ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣት በገቢ አሰባሰብ ላይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የአረካ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ አይዛ ኅብረተሰቡ ከመንግሥት ጋር ከተባበረና ከተጋገዝን የልማት ሥራን ማፋጠን ቀላል እንደሆነ ገልፀዋል።
የአገልግሎት አሰጣጡ የህዝቡን እርካታ ያረጋገጠ እና ከእጅ መንሻ፣ ጉቦና ምልጃ ነጻ በሆነ መልኩ ለሁሉም ነዋሪዎች በፍትሃዊነት የሚሰጥ መሆኑን ማረጋገጥ ወሳኝ ተግባር አድርጎ መዉሰድና በትኩረት እንደሚፈጸም ይሰራልም ነው ያሉት፡፡
በከተሞች ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እና ተወዳደሪ ከተሞችን ለማድረግ የዉስጥ አቅም ማጎልበት የሞት ሽረት ትግል የሚጠይቅ አጀንዳ ነው ብለዋል፡፡
የከተማው ነዋሪዎች እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት በገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም ዙሪያ የሚሰተዋል በተለያዩ አካላት የሚገለጽ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማስቀረት የሚካሄድ ብርቱ ትግል መደገፍና ዉጤታማ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበትም ተገልጿል።
የልማት ሥራ ውጤታማ እንዳይሆንና በገቢ አሰባሰብ ሂደት ማነቆ የሚሆኑ አመራሮች ጀምሮ እስከ ኅብረተሰብ ክፍሉ ድረስ ብልሹ አሠራር ውሰጥ ሲገቡ በሕግ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል ብለዋል የወይይቱ ተሳታፊዎች።
መንግስት የልማት ሥራ እንዳይሰራ የሰለጠኑና ለሕዝብ ልማት ቦታ የማይሰጡ አጨበርባሪ አካላት በሕግ መጠየቅ ተገቢ መሆኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።
በመድረኩ የከተማ አመራሩ፣ ከተማ ነዋሪ የተወጣጡ ህብረተሰብ ክፍሎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን ከወላይታ ዞን ማህበረሰብ ኤፍኤም ሬዲዮ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።