Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.87K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ባለፉት ስድስት ወራት በሙስና ወንጀል የተከሰሱ 175 ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ መሰጠቱ ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 3/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በፌደራል ደረጃ በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ ቤት ከቀረቡ ተከሳሾች መካከል 175 የሚሆኑት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት እንደተወሰነባቸው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ዘላለም ፈቃዱ ገለፁ፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ የሙስና ወንጀሎችን የፈፀሙ ተከሳሾች በ191 መዝገቦች ክስ ተመስርቶባቸው፣ አጠቃላይ በክርክር ላይ ከነበሩ 489 መዛግብት መካከልም በ100 መዝገቦች የተከሰሱ 175 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለው እስከ 19 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደተወሰነባቸው ዳይሬክተር ጀኔራሉ ገልፀዋል፡፡

በተለይም ከአገልገሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚፈፀም ጉቦና የማይገባ ጥቅም መቀበል፣ በመንግስት አሰራር ላይ የሚፈፀም በሥልጣን አላግባብ መገልገል፣ ከመሬት እና ካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የሚፈፀም ሙስና፣ ሃሰተኛ መንግስታዊ ሰነዶችን ከማዘጋጀትና ከመጠቀም እንዲሁም ከባንክ ደንበኞች እውቅና ውጪ በሃሰተኛ ሰነዶችና በሞባይል ባንኪንግ የባንክ ሒሳብን በማንቀሳቀስ ከሚፈፀም ምዝበራ ጋር በተያያዘ በርካታ የሕግ ማስከበር ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

ዳይሬክተር ጀኔራሉ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ከፓስፖርትና ሌሎች አገልግሎቶች አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ሲፈፀም በነበረ ስር የሰደደ የሙስና ወንጀል ላይ በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ብቻ ማግኘት የሚገባቸውን የኢትዮጵያ ፓስፖርት በሺዎች የሚገመት ዶላርና የኢትዮጵያ ብር በመቀበል ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ፓስፖርት በመስጠት፣ ከእያንዳንዱ አገልግሎት ፈላጊ ከ10 ሺ ብር እስከ 300 ሺ ብር በማስከፈል ጉዳያቸውን በሕገ-ወጥ መንገድ በመጨረስ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሕገ-ወጥ ደላሎችና ጉዳይ አስፈፃሚዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ለተለያዩ የውጭ ሀገራት ዜጎች እንዲሁም ለትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሕገ-ወጥ መንገድ የቱሪስት ቪዛ በማውጣትና በማሳደስ፣ የሃገር ውስጥ የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃዶችን በሕገ-ወጥ መንገድ ለውጭ ሃገራት ዜጎች በማውጣት እና በማሳደስ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ሃብት በማፍራት እንዲሁም በሌሎችም ሕገ-ወጥ ድርጊቶች የተጠረጠሩ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሠራተኞችና ከእነርሱ ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸዉ ግለሰቦች ላይ ምርመራ ተጣርቶ በድምሩ 60 ተጠርጣሪዎች ላይ 15 ተደራራቢ ክሶች የቀረቡ ሲሆን በሌሎች 6 መዝገቦች ላይም በተመሳሳይ ክስ መመስረቱን ገልፀዋል፡፡

ከዚሁ ክስ ጋር በተያያዘ ተከሳሾች በወንጀል ድርጊቱ ያፈሩትን ሀብት በተመለከተ ሰፊ የምርመራ ሥራ እየተሠራ የሚገኝና በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይም የወንጀል ምርመራ ሥራው እንደቀጠለ ሲሆን ቀሪ የወንጀል ምርመራው እንዳለቀም ተገቢው ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ከመሬት ጋር በተያያዘ መብት ሳይኖራቸው በተጭበረበረ መንገድ ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ምትክ ቦታና ካሳ በወሰዱና በሰጡ፣ የመሬት ጉዳይን እናስፈፅማለን በማለት ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ በተቀበሉና በሌሎች የመሬት ሙስና ጉዳዮች በድምሩ በ48 ተከሳሾች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል እንዲሁም በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ የቀረበባቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በባንኮች ላይ ከሚፈፀም ምዝበራና ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ሃሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ለረጅም ጊዜ ሳይንቀሳቀሱ የቆዩ የባንክ ሂሳቦችን በማንቀሳቀስ ያለደንበኞች እውቅናና ፈቃድ በሕይወት ከሌሉ፣ ውጪ ሀገር ከሚኖሩና ከሌሎችም ደንበኞች አካውንት ላይ ገንዘብ ወጪ አድርጎ በመውሰድ፣ የባንክ ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግና የኤቲኤም ተጠቃሚ ለመሆን ባልጠየቁበትና ፈቃዳቸውን ባልሰጡበት ሁኔታ እንደጠየቁ አስመስለው ተጠቃሚ በማድረግ በተጭበረበረ መንገድ ከደንበኞቹ ሂሳብ ላይ ገንዘብ ወጪ አድርገው በመውሰድና በሌሎችም ህገወጥ መንገዶች ከተለያዩ ባንኮች ከ68 ሚሊየን ብር በላይ በወሰዱ የባንክ ሰራተኞችና ሌሎች ግለሰቦች ላይ በ23 የተለያዩ መዛግብት ክስ የቀረበ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ተገቢውን ክፍያ ሳይከፍሉ እንደከፈሉ አስመስለው ሃሰተኛ የባንክ ደርሰኞችን አዘጋጅቶ ለኢትዮ-ቴሌኮም በማቅረብ ከኢትዮ-ቴሌኮም ላይ ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ በማጭበርበር ለግል ጥቅማቸው ባዋሉ ግለሰቦች ላይ ክስ ቀርቧል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በሀገራችን በስፋት ከሚፈፀሙ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ ከሆነው ሀሰተኛ መንግስትና የህዝባዊ ድርጅቶች ሰነዶችን ከማዘጋጀትና ከመገልገል ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ የመንግስትና የህዝባዊ ድርጅቶች ሰነዶችን በማዘጋጀት ለተለያዩ የመንግስት ተቋማትና ድርጅቶች በማቅረብ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ በወሰዱ ግለሰቦች ላይ በ12 መዝገቦች ክስ የቀረበ ሲሆን፣ እንደዚሁም በተሰጣቸው ኃላፊነት ህገ-ወጥ ድርጊት ለመፈፀም በማሰብ ከ3.2 ሚሊየን ብር በላይ ጉቦ በተቀበሉና ባቀባበሉ ግለሰቦች ላይ በ4 የተለያዩ መዝገቦች ክስ የቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተር ጀነራሉ ገለፃ ከውጪ በእርዳታ የተገኘና በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ተረጂዎች የተላከን የእርዳታ እህል ከመሸጥና ለግል ጥቅም ከማዋል ጋር በተያያዘ የምርመራና የዐቃቤ ህግ ቡድን ተዋቅሮ ድርጊቱ በተፈፀመባቸው ክልሎች የእርዳታ እህሉን ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የተባሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የወንጀል ምርመራ ስራ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በፌደራል ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚፈፀሙ የሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘም በተወሰኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ምርመራ የተጣራና የወንጀል ክስም የቀረበ ሲሆን በቀጣይም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከግዢና የውስጥ ገቢ ማመንጫ ስራዎች ጋር በተያያዘ የተፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን ከፌደራል ዋና ኦዲተር እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የህግ ማስከበር ስራው የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 6 ወር ውስጥ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ከነበሩ ጉዳዮች መካከል የልማት ተነሺ ሳይሆኑ እንደሆኑ በማስመሰል በተጭበረበረ መንገድ ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ በወሰዱና እንዲከፈል ባደረጉ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ በ19 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለው እስከ 19 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት እንደተወሰነባቸው መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመጨረሻም በቀጣይ ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት የፀረ-ሙስና የህግ ማስከበር ስራውን በማጠናከር ከፍተኛ ምዝበራ የተፈፀመባቸው፣ በሀገር ፀጥታና ደህንነት ላይ አደጋ የሚያስከትሉና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በተገልጋይ ህብረተሰቡ ላይ የሚፈፀሙ በመሬት አስተዳደር፣ ፍትህና ፀጥታ ዘርፍ፣ የመንግስት ገቢና ግዢ ስርዓት እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ላይ ትኩረት በማድረግ የህግ ማስከበር ስራዎች እንደሚሰሩ ዳይሬክተር ጀኔራሉ አክለው ገልጸዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በመዲናዋ በሙስና መከላከል ሥራ ከ876 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 4/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ በሙስና መከላከል ሥራ ከ876 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት ማዳን መቻሉን የከተማዋ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አሰፋ ቶላ እንዳሉት፥ ባለፉት ስድስት ወራት ሙስናን ለመከላከል የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ሌሎች ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሙስና በስፋት የሚስተዋልባቸው ዘርፎችን በመለየት የመከላከል ሥራ ላይ በትኩረት መሰራቱን ነው የገለጹት፡፡

በዚህም በመደበኛ ሙስና መከላከል 534 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና በአስቸኳይ ሙስና መከላከል 342 ነጥብ 4 ሚሊየን በድምሩ 876 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት ማዳን መቻሉን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በአይነት 171 ጠቅላላ ንብረት እና ከ4 ሺህ 685 ካሬ ሜትር በላይ መሬት ማዳን መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ከሙስና ወንጀሉ ጋር በተያያዘም 136 ሰዎች ተጠያቂ መደረጋቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋ፡፡

በተጠቀሰው ጊዜ 792 ጥቆማ መቅረቡን ጠቁመው፥ ከእነዚህ ውስጥ የተጠና 592 እና አግባብነት የሌላቸው 21 ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ደግሞ በሒደት ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በመንግስት ተቋማት፣ በልማት ድርጅቶች እና ህዝባዊ ተቋማት ያጋጠመዎትን ሙስና እና ብልሹ አሰራር በመጠቆም የዜግነት ግዴታውን ይወጡ!

**

፨ የመንግስት አገልግሎት ለማግኘት ፈልገው ወደ ተቋም ሲሄዱ ጉቦ ወይም የእጅ መንሻ ከተጠየቁ መብቴን በገንዘብ አልገዘም ብለው ባሉበት ቦታ ሆነው ጥቆማ ለኮሚሽኑ በማቅረብ መብትዎትን ያስከብሩ!

፨ እርስዎና ሌላው ተገልጋይ የመንግስት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋም ሄደው እርስዎ ለአገልግሎቱ ትክክለኛ መረጃ አቅርበው እያሉ ትክክለኛ መረጃ ላለቀረበው ተገልጋይ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ካወቁ ለኮሚሽኑ የታሰበው የሙስና ወንጀል ወደ ድርጊት ከመለወጡ በፊት ባሉበት ቦታ ሆነው ጥቆማ በማቅረብ ያስቁሙ!

ስለሆነም የሙስና እና ብልሹ አሰራር ድርጊቶች ካጋጠመዎት👇

በኮሚሽኑ ሀገራዊ የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
በኮሚሽኑ የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
በኮሚሽኑ ስልክ ቁጥር፦ 09 35 94 75 33 ወይም ካዛንቺስ ከልማት ባንክ ጉን በሚገኘው የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 2ኛ ወለል/ፎቅ በአካል ተገኝተው ጥቆማ ማቅረብ ይችላሉ።

ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ፣ መብትዎትን ያስከብሩ!
አሰራሮችን ማዘመን የሙስና ተጋላጭነትን ይቀንሳል!

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ማንኛውንም ጉዳይ አስፈጽማለሁ በማለት ህብረተሰቡን በማጭበርበር ገንዘብ ሲቀበል የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ)በወላይታ ሶዶ ከተማ ማንኛውንም ጉዳይ አስፈጽማለሁ በማለት ህብረተሰቡን በማጭበርበር ገንዘብ ሲቀበል የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።


በፋና ወምባ ቀበሌ አሰተዳደር ማዘጋጃ ቤት የቤቶች ልማት ዘርፍ ባለሙያ አቶ ሄኖክ ቴጋ ማንኛውንም ጉዳይ አስፈጽማለሁ በማለት ህብረተሰቡን በማጭበርበር ገንዘብ ሲቀበል በቁጥጥር ሥር መዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።

በህግ ቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ የማዘጋጃ ቤቱ ስራ አስኪያጅ ጓደኛዬ ነው፥ ጉዳያችሁን እኔ አስፈጽማለሁ በማለት ህብረተሰቡን ሲያጭበረብርና ገንዘብ ሲቀበል እንደነበረ ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቡ በተለያዩ ጊዜያት ከባለጉዳዮች የቀበሌ ቤት እኔ እሰጣለሁ፣ የትኛውንም ሥራዎችን እኔ አስፈጽማለሁ፣ የማዘጋጃ ቤቱ ስራ አስኪያጅ ጓደኛዬ ነው በማለት ገንዘብ ሲቀበል እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፥ ግለሰቡ የተለመደ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል በልዩ ትኩረት እየሰራ በመሆኑ ማንኛውም ባለጉዳይ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋማት ሲሄድ እጅ መንሻ፣ ጉቦ እና ያልተገባ ጥቅም የሚጠይቁ ግለሰቦች ሲያጋጥም ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርባል።

ስለሆነም በከተማው ፖሊስ የስልክ መስመር 04655510146 በመደወል ሙሰኞችንና መሰል ድርጊት ፈፃሚዎችን በማንኛውንም ሰዓት ጥቆማ እንዲሰጡ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ማሳሰቡን ከወላይታ ሶዶ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሥነምግባራዊ አመራር (ክፍል ሁለት)

****************

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ በበይነመረብ አማካኝነት የሚያቀርበው የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ክህሎት ሥልጠና እና ግንዛቤ ማጎልበቻ ፕሮግራም የጀመረ ሲሆን፣ በቀጣይም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችና ክፍሎች የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሙስና ወንጀል የተጠረጠረ የፍርድ ቤት ዳኛ በቁጥጥር ስር ውሎ ፍርድ ቤት ቀረበ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 6/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሙስና የወንጀል ድርጊት በመፈጸም ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ዳኛ ፍርድ ቤት ቀረበ።

ተጠርጣሪው የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆነው ተስፋዬ ደረጄ በወንጀል የተከሰሰ ግለሰብን ነጻ አደርግሃለው በማለት በሙስና ገንዘብ ተቀብሏል ተብሎ ተጠርጥሯል።

ተጠርጣሪው አንድን ግለሰብ ከተመሰረተበት የወንጀል ክስ ነጻ አስወጣለው በማለት የግለሰቡን መዝገብ የሚመለከቱ ሁለት ዳኞች አብረውት እንደተማሩና እንደሚያውቃቸው እንዲሁም አንደኛውን ዳኛ ደግሞ የስራ ባልደረባዬ ያውቃቸዋል ብሎ በመግለጽ በማግባባት 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በመጠየቅና 400 ሺህ ብር ሙስና ተቀብሏል በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ተጠርጣሪውን ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

ሆኖም የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባሉበት ተደራራቢ የመዝገቦች ምክንያት በይደር ለመመልከት ለነገ መቀጠሩን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአስቼኳይ ሙስና መከላከል ሥራ ከ2.7 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ገለፀ

*

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 6/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ውይይት አካሄዷል።

በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት በዋናነት በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል፣ የሙስና መከላከል ጥናት እንዲሁም በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዙሪያ የተሰሩ የእቅድ አፈፃፀም ተግባራት በሪፖርቱ ቀርበዋል።

በሪፖርቱ ለ45,238 የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱ፣ ከሙስና መከላከል ጋር በተያያዘ በአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ፣ በክልሉ እንቨስትመንት እንቅስቃሴ ላይ በመሬት አሰጣጥ ዙሪያ እና በአዳጋ መከላከልና ዝግጁነት ለተፈናቃይ ወገኖች በሚመጡ እርዳታዎች ላይ 3 የአሰራር ስራዓት ጥናት የተሰራ መሆኑ እንዲሁም 527 የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፣ 1,190 የሀብት ምዝገባ እድሳት እና ለ24 ተገልጋዮች የሀብት ምዝገባ ማቋረጥ ስራ መከናዎኑ ተመላክቷል።

ለኮሚሽኑ ባለፋት ስድስት ወራት 106 ጥቆማዎች ከህዝብ የቀረቡ ሲሆን፥ ስድስቱ ለምርመራ ለፓሊስ መላካቸው፤ እንዲሁም ሀምሳ አምስቱ በአስተዳደራዊ፣ 45 ጥቆማዋች በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ መፈታታቸው ተነግሯል።

በዚህም በአስቸኳይ ሙስና መከላከል በተሰራ ስራ 1,851 ካሜ የከተማ ቦታ፣ 2,710,548 ብር፣ 450 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እና 12 ላፕቶፖች የህዝብና የመንግስትን ሀብት ከብክነትና ከዘረፋ ማዳን መቻሉም ተገልጿል።

ኮሚሽኑ 20ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል አከባበርን ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ ተቋማት አመራሩና ሰራተኛው በተገኘበት በየቢሮው በፓናል ውይይቶች፣ በጥያቄና መልስ ውድድሮች፣ በአደባባይ ቢልቦርዶችን በመስቀል፣ ባነሮችን በመለጠፍና ህትመቶችን በማሰራጨት በድምቀት የተከበረ መሆኑና በብዓሉም 334,769 ተሳታፊ መገኘቱን በሪፖርቱ መቅረብ ችሏል።

በውይይት መድረኩ በተገኙ ተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተው በኮሚሽኑ አመራሮች ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን፥ በክልሉ የፀጥታ ችግር ምክንያት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ብዙ ያልተከናወኑ ተግባሮች መኖራቸውን አውስተው በቀጣይ ወራትም ያልተከናወኑ ተግባራትን በመለየት መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ መሰጠቱን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡