Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
ኤጀንሲው አገልግሎት በመስጠት ሂደት ላይ ያልተገባ ጥቅም የሚያገኙ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን እየሰራ ነው

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አገልግሎት በመስጠት ሂደት ላይ ያልተገባ ጥቅም የሚያገኙ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን እየሰራ መሆኑን ገለፀ።
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በስድስት ወራት ውስጥ በህገወጥነትና ተጠያቂነት ላይ በተሰሩ ስራዎች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ እንደለፁት፤ ኤጀንሲው ከሌብነት የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ነው።

በ6 ወራት ውስጥ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በኦዲት ግኝት ላይ ክትትሎች ተደርገዋል። በዚህም የአገልግሎት ኦዲትን በተመለከተ በጠቅላላው 63 ሰዎች ተጠያቂ ሲሆኑ 12 በወንጀል እና 41 በዲሲፕሊን ተጠያቂ ናቸው። ቀሪ 10 የጽ/ቤት አመራሮች ስራን በአግባቡ ባለመምራት ተጠያቂ የሚሆኑ መሆናየውን ገልፀዋል።

እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ 47 ባለሙያዎች ተጠያቂ የተደረጉ ሲሆን ከዚህም 34 በከባድ እና ቀላል ዲሲፕሊን እንዲሁም 9 ባለሙያዎች በወንጀል ተከሰዋል ብለዋል።

በተጨማሪም 36 ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው የተገኙ ተገልጋዮች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገ መሆኑን አስታውቀው፤ 4ቱ በወረዳ ጽ/ቤት፣ 34ቱ በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት መሆናቸውን ገልፀዋል። ከዚህም ውስጥ 3ቱ ፍርድ መሰጠታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ለግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ሥነምግባራዊ አመራር ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራር ጽንሰ ሀሳብ እና መገለጫ ባህርያት እንዲሁም ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥልጠና ዴስክ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና በነገው ዕለትም እንደሚቀጥል ከግብርና ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በመልካም ሥነምግባር አርዓያ የሆነ፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የሚጸየፍ ትውልድ በመፍጠር ረገድ የመምህራን ሚና የጎላ ነው!

***************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ማረሚያ ቤት በሚገኝ ግለሰብ ስም ሐሰተኛ ሊብሬና ከዕግድ ነጻ ሰነዶችን በመጠቀም ገንዘብ ተበድረዋል በተባሉ ግለሰቦች የክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ማረሚያ ቤት በሚገኝ ግለሰብ ስም ሀሰተኛ የቪ8 ተሽከርካሪ ሊብሬና ከዕግድ ነጻ የሚሉ ሰነዶችን በመጠቀም ገንዘብ ተበድረዋል ተብለው በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ።

ተጠርጣሪዎቹ ወ/ሮ ራኬብ መንግስቱ እና ወ/ሮ ቤተልየም መንግስቱ በማረሚያ ቤት በሚገኝ ሱራፌል በቀለ በሚባል ግለሰብ ስም ከአ/አ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የተሰጠ በማስመሰል የቪ8 ተሽከርካሪ ማረጋገጫ ሊብሬና ከዕግድ ነጻ የሚል ሀሰተኛ ማስረጃዎችን በመጠቀም ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ ከተባለ ህዝባዊ ድርጅት እያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን 76 ሺህ 74 ብር ገንዘብ ተበድረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ናቸው።

የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ተጠርጣሪዎች ላይ ሲያከናውን የቆየውን የምርመራ ስራ አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ገልጿል።

ዛሬ መዝገቡን እንደተረከበ የገለጸው የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ደግሞ መዝገቡን ተመልክቶ ለመወሰን እንዲያስችለው በወ/መ/ስ/ህ/ቁ 109/1 መሰረት የ15 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ ጠይቋል።

በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ በወንጀል ድርጊቱ የተገኘው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሶ ተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ የሚመሰርት ከሆነ ከ10 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ ድንጋጌ እንደሚሆን በመጠቆም ይህም ድንጋጌ ዋስትና የሚያስከለክል በመሆኑ ክስ እስኪመሰርት ተጠርጣሪዎቹ በእስር ይቆዩ የሚል ጥያቄ አንስቷል።

በተጠርጣሪ ጠበቃ በኩል ደግሞ የዐቃቤ ሕግ የክስ መመስረቻ ጊዜ ጥያቄን በመቃወም ተከራክሯል።

ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ድንጋጌ ዋስትና ሊያስከስስ ይችላል በሚል ምክንያት ብቻ የተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት ሊገደብ አይገባም የሚል የመከራከሪያ ነጥብ መነሳቱን ጠቅሶ ኤፍቢሲ ዘግቧል።

የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ ለመወሰን ጊዜ እንደሚያስፈልግ በማመን ዐቃቤ ሕግ የጠየቀውን የክስ መመስረቻ ጊዜ በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጥሯል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በመልካም ሥነምግባር የታነጸ፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በፅናት መታገል የሚችል ዜጋ ለማፍራት የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ ነው!

*********************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ ሰነዶችና የተቋማት ማህተም ሲያዘጋጅ በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ በ10 ዓመት እስራትና በገንዘብ ተቀጣ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 3/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችንና የተቋማትን ማህተም ሲያዘጋጅ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሎ ክስ የቀረበበት ግለሰብ በ10 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ወሰነ።

የቅጣት ውሳኔ የተወሰነበት ግሩም ክፈተው ገ/ህይወት በጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም “በአዲስ አበባ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 በቤት ቁጥር አዲስ በሆነ ህንጻ ላይ በተከራየው ክፍል ውስጥ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችንና የተቋማት ማህተሞችን እየቀረፀ ሲያዘጋጅ እንደነበር ተጠቅሶ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና የሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 (1) ሀ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፏል” በማለት ሀሰተኛ ሰነዶችን ማዘጋጀት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

ይህ ክስ ከቀረበበት በኋላ ተከሳሹ የሰጠውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ በተከሰሰበት ድንጋጌ እንዲከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሹ በተገቢው የዐቃቤ ሕግ መከራከሪያ ማስረጃን ያላስተባበለ በመሆኑ እንዲከላከል በተባለበት ድንጋጌ የጥፋተኝነት ፍርድ መሰጠቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ዐቃቤ ሕግ ላቀረበው የቅጣት ማክበጃ አስተያየት ፍርድ ቤቱ በመካከለኛ ደረጃ እንዲያዝ አድርጓል።

ተከሳሹ ለህዳሴ ግድብ የፈጸመውን የቦንድ ግዢ፣ የደም ልገሳ ያደረገውን ተሳትፎ ጠቅሶ ባቀረበው የቅጣት ማቅለያ አስተያየትን በሚመለከት ደግሞ ፍርድ ቤቱ የተለዩ በበጎ ፍቃድ የሰጠው የማህበራዊ ተሳትፎን በወንጀል ህግ አንቀጽ 86 መሰረት እንደ አንድ ማቅለያ በመያዝ እንዲሁም የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለውና የዘወትር ፀባዩ መልካም እንደነበር በወንጀል ህግ አንቀጽ 82 (1) ሀ መሰረት እንደ አንድ ማቅለያ ይዞለታል።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን በመካከለኛ ደረጃ በ10 አመት ጽኑ እስራትና በ6 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት በሙስና ወንጀል የተከሰሱ 175 ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ መሰጠቱ ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 3/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በፌደራል ደረጃ በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ ቤት ከቀረቡ ተከሳሾች መካከል 175 የሚሆኑት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት እንደተወሰነባቸው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ዘላለም ፈቃዱ ገለፁ፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ የሙስና ወንጀሎችን የፈፀሙ ተከሳሾች በ191 መዝገቦች ክስ ተመስርቶባቸው፣ አጠቃላይ በክርክር ላይ ከነበሩ 489 መዛግብት መካከልም በ100 መዝገቦች የተከሰሱ 175 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለው እስከ 19 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደተወሰነባቸው ዳይሬክተር ጀኔራሉ ገልፀዋል፡፡

በተለይም ከአገልገሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚፈፀም ጉቦና የማይገባ ጥቅም መቀበል፣ በመንግስት አሰራር ላይ የሚፈፀም በሥልጣን አላግባብ መገልገል፣ ከመሬት እና ካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የሚፈፀም ሙስና፣ ሃሰተኛ መንግስታዊ ሰነዶችን ከማዘጋጀትና ከመጠቀም እንዲሁም ከባንክ ደንበኞች እውቅና ውጪ በሃሰተኛ ሰነዶችና በሞባይል ባንኪንግ የባንክ ሒሳብን በማንቀሳቀስ ከሚፈፀም ምዝበራ ጋር በተያያዘ በርካታ የሕግ ማስከበር ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

ዳይሬክተር ጀኔራሉ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ከፓስፖርትና ሌሎች አገልግሎቶች አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ሲፈፀም በነበረ ስር የሰደደ የሙስና ወንጀል ላይ በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ብቻ ማግኘት የሚገባቸውን የኢትዮጵያ ፓስፖርት በሺዎች የሚገመት ዶላርና የኢትዮጵያ ብር በመቀበል ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ፓስፖርት በመስጠት፣ ከእያንዳንዱ አገልግሎት ፈላጊ ከ10 ሺ ብር እስከ 300 ሺ ብር በማስከፈል ጉዳያቸውን በሕገ-ወጥ መንገድ በመጨረስ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሕገ-ወጥ ደላሎችና ጉዳይ አስፈፃሚዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ለተለያዩ የውጭ ሀገራት ዜጎች እንዲሁም ለትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሕገ-ወጥ መንገድ የቱሪስት ቪዛ በማውጣትና በማሳደስ፣ የሃገር ውስጥ የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃዶችን በሕገ-ወጥ መንገድ ለውጭ ሃገራት ዜጎች በማውጣት እና በማሳደስ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ሃብት በማፍራት እንዲሁም በሌሎችም ሕገ-ወጥ ድርጊቶች የተጠረጠሩ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሠራተኞችና ከእነርሱ ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸዉ ግለሰቦች ላይ ምርመራ ተጣርቶ በድምሩ 60 ተጠርጣሪዎች ላይ 15 ተደራራቢ ክሶች የቀረቡ ሲሆን በሌሎች 6 መዝገቦች ላይም በተመሳሳይ ክስ መመስረቱን ገልፀዋል፡፡

ከዚሁ ክስ ጋር በተያያዘ ተከሳሾች በወንጀል ድርጊቱ ያፈሩትን ሀብት በተመለከተ ሰፊ የምርመራ ሥራ እየተሠራ የሚገኝና በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይም የወንጀል ምርመራ ሥራው እንደቀጠለ ሲሆን ቀሪ የወንጀል ምርመራው እንዳለቀም ተገቢው ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ከመሬት ጋር በተያያዘ መብት ሳይኖራቸው በተጭበረበረ መንገድ ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ምትክ ቦታና ካሳ በወሰዱና በሰጡ፣ የመሬት ጉዳይን እናስፈፅማለን በማለት ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ በተቀበሉና በሌሎች የመሬት ሙስና ጉዳዮች በድምሩ በ48 ተከሳሾች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል እንዲሁም በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ የቀረበባቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በባንኮች ላይ ከሚፈፀም ምዝበራና ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ሃሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ለረጅም ጊዜ ሳይንቀሳቀሱ የቆዩ የባንክ ሂሳቦችን በማንቀሳቀስ ያለደንበኞች እውቅናና ፈቃድ በሕይወት ከሌሉ፣ ውጪ ሀገር ከሚኖሩና ከሌሎችም ደንበኞች አካውንት ላይ ገንዘብ ወጪ አድርጎ በመውሰድ፣ የባንክ ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግና የኤቲኤም ተጠቃሚ ለመሆን ባልጠየቁበትና ፈቃዳቸውን ባልሰጡበት ሁኔታ እንደጠየቁ አስመስለው ተጠቃሚ በማድረግ በተጭበረበረ መንገድ ከደንበኞቹ ሂሳብ ላይ ገንዘብ ወጪ አድርገው በመውሰድና በሌሎችም ህገወጥ መንገዶች ከተለያዩ ባንኮች ከ68 ሚሊየን ብር በላይ በወሰዱ የባንክ ሰራተኞችና ሌሎች ግለሰቦች ላይ በ23 የተለያዩ መዛግብት ክስ የቀረበ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ተገቢውን ክፍያ ሳይከፍሉ እንደከፈሉ አስመስለው ሃሰተኛ የባንክ ደርሰኞችን አዘጋጅቶ ለኢትዮ-ቴሌኮም በማቅረብ ከኢትዮ-ቴሌኮም ላይ ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ በማጭበርበር ለግል ጥቅማቸው ባዋሉ ግለሰቦች ላይ ክስ ቀርቧል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በሀገራችን በስፋት ከሚፈፀሙ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ ከሆነው ሀሰተኛ መንግስትና የህዝባዊ ድርጅቶች ሰነዶችን ከማዘጋጀትና ከመገልገል ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ የመንግስትና የህዝባዊ ድርጅቶች ሰነዶችን በማዘጋጀት ለተለያዩ የመንግስት ተቋማትና ድርጅቶች በማቅረብ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ በወሰዱ ግለሰቦች ላይ በ12 መዝገቦች ክስ የቀረበ ሲሆን፣ እንደዚሁም በተሰጣቸው ኃላፊነት ህገ-ወጥ ድርጊት ለመፈፀም በማሰብ ከ3.2 ሚሊየን ብር በላይ ጉቦ በተቀበሉና ባቀባበሉ ግለሰቦች ላይ በ4 የተለያዩ መዝገቦች ክስ የቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተር ጀነራሉ ገለፃ ከውጪ በእርዳታ የተገኘና በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ተረጂዎች የተላከን የእርዳታ እህል ከመሸጥና ለግል ጥቅም ከማዋል ጋር በተያያዘ የምርመራና የዐቃቤ ህግ ቡድን ተዋቅሮ ድርጊቱ በተፈፀመባቸው ክልሎች የእርዳታ እህሉን ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የተባሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የወንጀል ምርመራ ስራ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በፌደራል ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚፈፀሙ የሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘም በተወሰኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ምርመራ የተጣራና የወንጀል ክስም የቀረበ ሲሆን በቀጣይም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከግዢና የውስጥ ገቢ ማመንጫ ስራዎች ጋር በተያያዘ የተፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን ከፌደራል ዋና ኦዲተር እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የህግ ማስከበር ስራው የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 6 ወር ውስጥ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ከነበሩ ጉዳዮች መካከል የልማት ተነሺ ሳይሆኑ እንደሆኑ በማስመሰል በተጭበረበረ መንገድ ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ በወሰዱና እንዲከፈል ባደረጉ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ በ19 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለው እስከ 19 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት እንደተወሰነባቸው መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመጨረሻም በቀጣይ ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት የፀረ-ሙስና የህግ ማስከበር ስራውን በማጠናከር ከፍተኛ ምዝበራ የተፈፀመባቸው፣ በሀገር ፀጥታና ደህንነት ላይ አደጋ የሚያስከትሉና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በተገልጋይ ህብረተሰቡ ላይ የሚፈፀሙ በመሬት አስተዳደር፣ ፍትህና ፀጥታ ዘርፍ፣ የመንግስት ገቢና ግዢ ስርዓት እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ላይ ትኩረት በማድረግ የህግ ማስከበር ስራዎች እንደሚሰሩ ዳይሬክተር ጀኔራሉ አክለው ገልጸዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡