Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
የኮሚሽኑ ሠራተኞች የገና በዓልን ምክኒያት በማድረግ ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ አደረጉ

*****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 30/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች የገና በዓልን ምክኒያት በማድረግ ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ አድርገዋል።

የኮሚሽኑ ሠራተኞች የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድረስ በመሄድ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፥ የገና በዓልን ምክኒያት በማድረግ የንፅህና መጠበቂያ እና ለምግብነት የሚውል ዱቄት እገዛ አድርገዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የፖሊስ አባሉ ወደ ባንክ አካወንታቸው በስህተት የገባን 45 ሺህ 200 ብር ተመላሽ አደረጉ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን የጊምቢቹ ከተማ ፖሊስ ባልደረባ ዋና ሳጂን መስፍን አለሙ ወደ ባንክ አካውንታቸው በስህተት የገባን 45 ሺህ 200 ብር ተመላሽ አደረጉ።

ገንዘቡ የልፋታቸው ዉጤት እንዳልሆነ የተረዱት ዋና ሳጅን መስፍን ወደ ጊምቢቹ ከተማ አቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ ሄደዉ በማመልከት ለባለቤቱ እንዲመለስ ማድረጋቸው ከከተማው አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በኮሚሽኑ የሚዘጋጀው የታህሳስ ወር 18ኛ ዕትም ዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ
****************
የዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ ሙሉ መረጃን ለማግኘት ሊንኩን ያስፈጥሩ...https://drive.google.com/file/d/1-mtsLkstyITV-OW_-rjCgpL9BhY1NE3R/view?usp=sharing
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ ከግለሰቦች ገንዘብ የተቀበለችው ተከሳሽ

****************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለፀ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀሰተኛ ሰነድ በሚያዘጋጁ ግለሰቦች ላይ ባደረገው ክትትል ልዩ ልዩ ሀሰተኛ ሠነዶችንና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን ቁሳቁሶች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ፖሊስ በወረዳ 3 አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሀሰተኛ ሰነድ በሚዘጋጅበት መኖሪያ ቤት ውስጥ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ 13 ሀሰተኛ የመኪና ሊብሬ፣ 10 ሀሰተኛ የቤት ካርታ፣ 2 ሀሰተኛ የጋብቻ ሰርተፍኬት፣ 18 የእጅ በእጅ የሽያጭ ደረሰኞች እና 6 ሀሰተኛ የባንክ ቤት ደረሰኞች ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ የዲግሪ፣ የዲፕሎማ እና የስምንተኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ሀሰተኛ የስራ ልምድ እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ሀሰተኛ አርማዎች (ሎጎ) መገኘታቸውን የጌጃ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ኮማንደር በልሁ ክፍሌ ገልፀዋል።

ሀሰተኛ ሰነድ በሀገር ላይ የሚስከትለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳት በመረዳት ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አበርክቶ ሊወጣ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ማስተላለፉን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኤጀንሲው አገልግሎት በመስጠት ሂደት ላይ ያልተገባ ጥቅም የሚያገኙ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን እየሰራ ነው

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አገልግሎት በመስጠት ሂደት ላይ ያልተገባ ጥቅም የሚያገኙ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን እየሰራ መሆኑን ገለፀ።
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በስድስት ወራት ውስጥ በህገወጥነትና ተጠያቂነት ላይ በተሰሩ ስራዎች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ እንደለፁት፤ ኤጀንሲው ከሌብነት የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ነው።

በ6 ወራት ውስጥ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በኦዲት ግኝት ላይ ክትትሎች ተደርገዋል። በዚህም የአገልግሎት ኦዲትን በተመለከተ በጠቅላላው 63 ሰዎች ተጠያቂ ሲሆኑ 12 በወንጀል እና 41 በዲሲፕሊን ተጠያቂ ናቸው። ቀሪ 10 የጽ/ቤት አመራሮች ስራን በአግባቡ ባለመምራት ተጠያቂ የሚሆኑ መሆናየውን ገልፀዋል።

እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ 47 ባለሙያዎች ተጠያቂ የተደረጉ ሲሆን ከዚህም 34 በከባድ እና ቀላል ዲሲፕሊን እንዲሁም 9 ባለሙያዎች በወንጀል ተከሰዋል ብለዋል።

በተጨማሪም 36 ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው የተገኙ ተገልጋዮች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገ መሆኑን አስታውቀው፤ 4ቱ በወረዳ ጽ/ቤት፣ 34ቱ በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት መሆናቸውን ገልፀዋል። ከዚህም ውስጥ 3ቱ ፍርድ መሰጠታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡