Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
የኮሚሽኑ አመራሮች እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ

*

(
የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 30/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮች እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች እንደገለፁት የአመራር ሥነምግባር እና ታማኝነት ማዕከል ለማቋቋም እቅድ ይዞ ተግባራን እያከናወነ መሆኑን ለኮሚሽኑ አመራሮች ገለፃ አድርገዋል፡፡

ፕሮግራሙ በዋናነት የአመራር ልማት ፕሮግራም የመሪዎችን የአመራር ክህሎትና አቅም በመገንባት በሙያቸው፣ በአመራር ሚናቸውና በአደረጃጀታቸው የላቀ ብቃት እንዲላበሱ የሚያስችል የአመራር ግንባታ ዓይነተኛ መሳሪያ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

ፕሮግራሙ የመሪዎችን አመለካከት ክህሎት እና የአመራር ዘይቤ በማያቋርጥ ሁኔታ በማሻሻል በሚመሩት ተቋም ወይም ድርጅት የተቀመጡ ግቦችን ከማሳካት ባሻገር ቀጣይነት ባለው መልኩ ብቁ የአመራር ትውልድ ለመፍጠር የሚያስችከል ስትራቴጂ መሆኑን ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የመጡ አመራሮች ገልፀዋል፡፡

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮች እንደገለፁት ፕሮግራሙ የአመራር የሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ላይም እንደ አንድ ፕሮግራሙ ትኩረት ያደረገ መሆኑን በማድነቅ፥ በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ጉዳዮች የሚያጠና ኮሚቴ ተደራጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የአ/አ ከተማ ከንቲባ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር የነበሩትና የፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር የነበሩት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

*****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 30/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር የነበሩት እና የፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር የነበሩት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የፖሊስን የጥርጣሬ መነሻ ምክንያትንና የተጠርጣሪዎችን የመከራከሪያ ነጥብን ተመልክቷል።

ተጠርጣሪዎቹ የአ/አ ከንቲባ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር የነበሩት ኤልቤቴል ሀብቴ እና የፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር የነበሩት ፍቅሩ ኦላናን ጨምሮ አምስት ናቸው።

ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የጥርጣሬ መነሻውን ያቀረበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ 1ኛ እና 2ኛ ተጠርጣሪዎች ያላቸውን የስራ ኃላፊነት በመጠቀም የካቲት ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ምንም ስራ የሌለውን የ1ኛ ተጠርጣሪ ወንድም ይስሀቅ ሀብቴ የተባለ ግለሰብ ትልቅ ባለኃብት እንደሆነና የተለያዩ እቃዎችን ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያመጣ የተለያዩ ግለሰቦችን እየጠቀመ እንደሆነ እና ከውጭ ሀገራት የሚያስመጣቸው እቃዎችን ደግሞ 1ኛ እና 2ኛ ተጠርጣሪዎች በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ባላቸው ስልጣን መሰረት ቁጥጥር እንደማይደረግና ከፍተኛ ትርፍ እንደሚያስገኝ በማስመሰል ተግባር ላይ ሚና እንደነበራቸው ጠቅሶ ፖሊስ በጥርጣሬ መነሻው ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አብራርቷል።

3ኛ እና 4ኛ ተጠርጣሪዎች ደግሞ ከግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆን በተለያዩ የንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎችን በማግኘት ከ1ኛ ተጠርጣሪ ወንድም ጋር በጋራ እንደሚሰሩና ትርፋማ እንደሚሆኑ በመግለጽና በተለይም 1ኛ እና 2ኛ ተጠርጣሪዎች በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ስልጣን ያላቸው መሆናቸውን በመግለጽ እንዲሁም እነዚሁ 1ኛ እና 2ኛ ተጠርጣሪዎች እስከ ላይኛው የስልጣን ዕርከን ድረስ ሰንሰለት ያላቸው መሆናቸውን ጠቁመው፤ የግል ተበዳዮቹን ስጋት አይግባችሁ በማለት ነጋዴዎቹን ያግባቡ መሆኑን ጠቅሶ መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።

በዚህ መልኩ ከ17 ግለሰቦች ዕቃ ማምጪያ በሚል 47 ሚሊየን 345 ሺህ ብር ከተቀበሉ በኋላ ከግል ተበዳዮች የሰበሰቡትን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን ጠቅሶ መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ የጥርጣሬ መነሻውን ገልጿል።

በተጨማሪም የግል ተበዳዮቹ በሂደት የተፈጸመው የወንጀል ተግባር መሆኑን ተረድተው ገንዘባችንን መልሱ በሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ደግሞ 1ኛ፣ 2ኛ እና 5ኛ ተጠርጣሪዎች የ1ኛ ተጠርጣሪ ወንድም በህግ እንዳይጠየቅ ከአካባቢው ከሰወሩት በኋላ ወደ ግል ተበዳዮች ስልክ በመደወል በትላልቅ ሆቴሎች ውስጥ ስብሰባ እየጠሩ ''አርፋችሁ ተቀመጡ በዚህ ጉዳይ ሁለተኛ ስለገንዘብ እንዳታነሱ፣ የተለያዩ እንቅስቃሴ ብታደርጉና ወደ ህግ ብትሄዱ የምታመጡት ነገር የለም እንዲሁም በቤተሰባችሁና በራሳችሁ ላይ ጉዳት ይደርሳል በማለት የከፍተኛ ባለስልጣናትን ስም በመጥራት ሲያስፈራሯቸው ነበር ሲል የጥርጣሬ መነሻውን ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አስረድቷል።

በዚህ መልኩ በከባድ ማታለልና ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ገልጿል።

የግል ተበዳዮችን ቃል መቀበሉንና የተወሰኑ የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰቡን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ ቀሪ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ከወንጀሉ ውስብስብነት አንጻር ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጾ፤ በወ/መ/ስ/ህ/ቁጥር 59/1 መሰረት የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ እንዲሰጠው መጠየቁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ምንም ወንጀል እንዳልፈጸሙ በመግለጽ ፖሊስ የጠየቀው የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮን በመቃወም ተከራክረዋል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የምርመራ መዝገቡ ጅምር መሆኑን ተከትሎ ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ እንደሚያስፈልገው በማመን የ14 ቀን የምርመራ ማጠቃለያ ጊዜ ለፖሊስ ፈቅዷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የኮሚሽኑ ሠራተኞች የገና በዓልን ምክኒያት በማድረግ ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ አደረጉ

*****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 30/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች የገና በዓልን ምክኒያት በማድረግ ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ አድርገዋል።

የኮሚሽኑ ሠራተኞች የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድረስ በመሄድ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፥ የገና በዓልን ምክኒያት በማድረግ የንፅህና መጠበቂያ እና ለምግብነት የሚውል ዱቄት እገዛ አድርገዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የፖሊስ አባሉ ወደ ባንክ አካወንታቸው በስህተት የገባን 45 ሺህ 200 ብር ተመላሽ አደረጉ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን የጊምቢቹ ከተማ ፖሊስ ባልደረባ ዋና ሳጂን መስፍን አለሙ ወደ ባንክ አካውንታቸው በስህተት የገባን 45 ሺህ 200 ብር ተመላሽ አደረጉ።

ገንዘቡ የልፋታቸው ዉጤት እንዳልሆነ የተረዱት ዋና ሳጅን መስፍን ወደ ጊምቢቹ ከተማ አቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ ሄደዉ በማመልከት ለባለቤቱ እንዲመለስ ማድረጋቸው ከከተማው አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በኮሚሽኑ የሚዘጋጀው የታህሳስ ወር 18ኛ ዕትም ዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ
****************
የዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ ሙሉ መረጃን ለማግኘት ሊንኩን ያስፈጥሩ...https://drive.google.com/file/d/1-mtsLkstyITV-OW_-rjCgpL9BhY1NE3R/view?usp=sharing
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ ከግለሰቦች ገንዘብ የተቀበለችው ተከሳሽ

****************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለፀ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀሰተኛ ሰነድ በሚያዘጋጁ ግለሰቦች ላይ ባደረገው ክትትል ልዩ ልዩ ሀሰተኛ ሠነዶችንና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን ቁሳቁሶች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ፖሊስ በወረዳ 3 አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሀሰተኛ ሰነድ በሚዘጋጅበት መኖሪያ ቤት ውስጥ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ 13 ሀሰተኛ የመኪና ሊብሬ፣ 10 ሀሰተኛ የቤት ካርታ፣ 2 ሀሰተኛ የጋብቻ ሰርተፍኬት፣ 18 የእጅ በእጅ የሽያጭ ደረሰኞች እና 6 ሀሰተኛ የባንክ ቤት ደረሰኞች ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ የዲግሪ፣ የዲፕሎማ እና የስምንተኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ሀሰተኛ የስራ ልምድ እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ሀሰተኛ አርማዎች (ሎጎ) መገኘታቸውን የጌጃ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ኮማንደር በልሁ ክፍሌ ገልፀዋል።

ሀሰተኛ ሰነድ በሀገር ላይ የሚስከትለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳት በመረዳት ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አበርክቶ ሊወጣ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ማስተላለፉን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።