Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ጉቦ የተቀበሉ የመሬት ሊዝ አስተዳደር ፅ/ቤት ሰራተኞች እጅ ከፍንጅ ተያዙ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጉዳይ ለመፈፀም 1 ሚሊየን 4 መቶ ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ ሁለት የመሬት ሊዝ አስተዳደር ፅ/ቤት ሰራተኞች እና ተባባሪያቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የቅንጅት ስራ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር መስፍን በላቸው እንደገለፁት በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር የቦታ ርክክብና ክትትል ቡድን መሪ እና የሊዝ ማስተላለፍ ባለሙያ ሲሆኑ፥ ሶስተኛዋ ተጠርጣሪ ደግሞ ለወንጀሉ ተባባሪ የሆነች የሊዝ ማስተላለፍ ባለሙያው እህት ነች፡፡

የግል ተበዳይ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በሊዝ የገዙትን ቦታ ለመረከብ ሲመላለሱ ከቆዩ በኋላ የግንባታ ማስጀመሪያ ፈቃድ እንዲራዘምላቸው ለመጠየቅ አገልግሎት ፈልገው ነበር ወደ ክፍለ ከተማው አስተዳደር የሄዱት፡፡

ይሁን እንጂ ተጠርጣሪዎቹ ተገቢውን አገልግሎት መስጠጥ ሲጠበቅባቸው ቀጠሮ በማብዛት ሲያመላልሷቸው እንደነበር እና ጉዳዩን ለመፈፀም ገንዘብ እንደተጠየቁ የግል ተበዳይ መግለፃቸውን ኮማንደር መስፍን አስረድተዋል፡፡

"በሊዝ የተገዛው ቦታ መንገድ ዳር በመሆኑ እኛ ለምንፈፅምልዎት ጉዳይ የሚከፍሉን ገንዘብ ይጨምራል" የሚል መደራደሪያ ሃሳብ በማቅረብ ተጠርጣሪዎቹ 3 ሚሊዮን ብር ጠይቀው እንደነበር እና በመጨረሻም ወደ 1 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ ብር ዝቅ እንደተደረገ ኮማንደር መስፍን አብራርተዋል፡፡

ከተጠየቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ሚሊዮን 2 መቶ ሺህ ብሩ የሊዝ ማስተላለፍ ባለሙያው በሆነው ተጠርጣሪ እህት የባንክ ሂሳብ ውስጥ እንዲገባ መደረጉን የጠቀሱት የምርመራ ሃላፊው፥ ከግል ተበዳይ በቀረበ አቤቱታ በአዲስ አበባ ፖሊስ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ክትትል 200 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የማህበራዊ የትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር(መተግበሪያ)፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በጅማ ከተማ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታን ላልተገባ ጥቅም በማዋል መንግስትን ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ አሳጥተዋል የተባሉ ተከሳሾች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በጅማ ከተማ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታን ላልተገባ ጥቅም በማዋል መንግስትን ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ አሳጥተዋል የተባሉ ተከሳሾች በ15 አመት ጽኑ እስራት እና በገንዘብ እንዲቀጡ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ወሰነ።

የቅጣት ውሳኔው የተላለፈባቸው ተከሳሾች የጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የቀድሞ ፕላንና መሬት አስተዳደር ኃላፊ ሼራብ አባሜጫ አባጎጃም እና የጅማ ከተማ የቀድሞ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አወል አባሜጫ አባቡሉ ናቸው።

የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተከሳሾቹን በቁጥጥር ስር አውሎ የተለያዩ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን ለኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ዐቃቤ ሕግ አስረክቧል።

ዐቃቤ ሕግም ተከሳሾቹን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ እና ለ አንቀጽ 407 ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል በማለት በመጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ተደራራቢ ክስ አቅርቦባቸዋል።

በክሱ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሾቹ በቁጥጥር ስር ያልዋለው በክስ መዝገቡ በ3ኛ ተራ ቁጥር ከተጠቀሰው የጅማ ከተማ የመሃንዲስ መሪ ከነበረው ሰዓዲ አቢዩ ነገኦ ከተባ ተከሳሽ ጋር በጥቅም በመመሳጠር 2ኛ ተከሳሽ በወላጅ እናቱ ስም እና ፊርማቸውን አስመስሎ በመጠቀም 10 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ያቀረበ በማስመሰል ማመልከቻ ማስገባቱ ተጠቅሷል።

በማመልከቻው መነሻነት 1ኛ ተከሳሽና 3ኛ ተከሳሽ በጋራ በመሆን አንድ ካሬ ሜትር በ1 ብር ከ50 ሳንቲም በሊዝ የተሰጠ አስመስለው ለ2ኛ ተከሳሽ በጊንጆው ጉድሉ ቀበሌ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታ እንዲወስድ ማድረጋቸው በክሱ ተገልጿል።

በተጨማሪም ለክሊኒክ ግንባታ በሚል በ3ኛ ተከሳሽ ፕላንና ካርታ አዘጋጅነት በ1ኛ ተከሳሽ አጽዳቂነት መስጠታቸው ተዘርዝሯል።

ባጠቃላይ ይዞታው በሊዝ ቢሸጥ ኖሮ ሊገኝ የሚችለውን ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማሳጣታቸው በክሱ ተጠቅሷል።

በዚህ መልኩ ፍርድ ቤት ቀርበው የቀረበባቸውን ክስ የተከታተሉት 1ኛና 2ኛ ተከሳሾች ወንጀሉን አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው በሰጡት የዕምነት ክህደት ቃል መነሻ ፍርድ ቤቱ በዐቃቤ ሕግ የቀረቡ የተለያዩ የምስክር ቃልና የሰነድ ማስረጃዎችን ተመልክቷል።

የቀረበባቸውን ማስረጃ እንዲከላከሉ ብይን የተሰጣቸው ተከሳሾቹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መስተባበል ባለመቻላቸው በተከሰሱበት ድንጋጌ የጥፋተኝነት ፍርድ መተላለፋን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ በዐቃቤ ሕግ በኩል ተከሳሾቹ ወንጀሉን በጥቅም በመመሳጠር የፈጸሙት መሆኑ ተጠቅሶ የቀረበውን የቅጣት ማክበጃ እና የተከሳሾቹ የቤተሰብ አስተዳዳሪና የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለባቸው ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ ይዟል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸውን በ15 አመት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዢን ኃላፊ ም/ኮማንደር ገዛኸኝ አጉቾ ገልጸዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር(መተግበሪያ)፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽኑ ከሸገር ከተማና በስሩ ከሚገኙ የክ/ከተማ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በጥቅም ግጭት መለየትና የሀብት ምንጭ ትክክለኛነት ማጣራት ሥራ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ

********

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሸገር ከተማና በስሩ ከሚገኙ ከ12ቱ ክ/ከተማ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በጥቅም ግጭት መለየትና የሀብት ምንጭ ትክክለኛነት ማጣራት ሥራ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል፡፡

የውይይቱ መድረኩ ዓላማ የጥቅም ግጭት ፅንሰ ሃሳብ እና መሠረታዊ መንስኤዎችን በመረዳት ለጥቅም ግጭት ተጋላጭ በሆኑ ዘርፎችና አሰራሮች ላይ በማተኮር እንደ ክ/ከተማው ነባራዊ ሁኔታ የጥቅም ግጭት የመለየት ወይም የሀብት ምንጭ ትክክለኛነት የማጣራት ሥራን በተሻለ ጥራትና ግንዛቤ እንዲያከናውኑ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከመረጃ ሰጭ ተቋማት ጋር የተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ በዋናነት የጥቅም ግጭት ምንነት፣ አይነቶች፣ ገፅታዎች፣ ህጋዊ መነሻዎች፣ መሠረታዊ መንስኤዎች እና ለጥቅም ግጭት የሚያጋልጡ ሁኔታዎች እንዲሁም የጥቅም ግጭት እና ሙስና፣ ለጥቅም ግጭት ተጋላጭ የሆኑ ዘርፎችና አሰራሮች፣ የሚያስከትለው ጉዳት፣ የመከላከልና ማስተዳደር ስልቶች እንዲሁም የጥቅም ግጭት መከላከል (ሀብት ማጣራት) አስፈላጊነት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

በውይይቱ መድረኩ ለተሰጡ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጥቅም ግጭት መከላከል ዴስክ ኃላፊ አቶ ከተማ ኃይለስላሴ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ በቀጣይም ኮሚሽኑ በሚያከናውናቸው የሀብት ምንጭ ትክክለኛነት የማጣራት ስራዎች የከተማውና የክ/ከተማው ፅ/ቤት ኃላፊዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የሀገራችንን ሠላም ለማስጠበቅና ቀጣይነት ያለው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በጋራ መታገል ያስፈልጋል!

*****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ የማንነት ሰነድ በመጠቀም በህገወጥ መልኩ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎች ከጥር አንድ ጀምሮ ወደህጋዊ መስመር እንዲገቡ የጊዜ ገደብ ተሰጠ

************


(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 25/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀሰተኛ የማንነት ሰነድ በመጠቀም በህገወጥ መልኩ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎች ከጥር አንድ እስከ ጥር 30 2016 ዓ.ም ድረስ ወደህጋዊ መስመር እንዲገቡ የጊዜ ገደብ መሠጠቱን የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት አስታወቀ።

ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ የሚኖሩና በህጋዊ መስመር ያልገቡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች መኖራቸውንም ገልጿል።

ሀሰተኛ የማንነት ሰነድ በመጠቀም በሕገወጥ መልኩ በኢትዮጵያ የሚኖሩና የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸው አካላት ወደህጋዊ መስመር የማስገባት ስራን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ተሰጥቷል።

የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ፓስፖርት፣ ሀሰተኛ ቪዛ እና ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየኑሩ ይገኛል።

በተደረገው የማጣራት ስራ ከ18 ሺህ በላይ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ከ1ሺህ 500 በላይ ሀሰተኛ ቪዛ እና ከአንድ ሺህ 800 በላይ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያን ያሰሩ ዜጎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መገኘታቸውን አስታውቀዋል።

እነዚህንና ሌሎች ህገወጥ ሰነድ ያለቸው ዜጎች ከጥር አንድ ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ወደ ተቋሙ በመምጣት ህጋዊ ሰነድ እንዲዘጋጅላቸው የማያደርጉ ከሆነ እርምጃ ይወሳዳል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

በሕገወጥ መልኩ በኢትዮጵያ የሚኖሩ እና የሌላ ሀገር ዜግነት ባላቸው አካላት ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ህጋዊ ሰነድ እንዲዘጋጅላቸው ካለደረጉ መንግስት እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የሙስና እና ታክስ ነክ ወንጀሎችን ለመከላከል ቅንጅታዊ አሰራር ማጎልበት እንደሚገባ ተገለፀ

********

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 25/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፍትህ ቢሮ በመሰረታዊ ሕጎች ዙሪያ በየደረጃው ላሉ መዋቅሮችና መርማሪ ፖሊሶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር በሚዛን ከተማ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊና የወንጀል እና ፍታብሄር ጉዳዮች ዘርፍ ሃላፊ አቶ ታመነ ታደሰ የሙስና እና ታክስ ነክ ወንጀሎች በሃገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ላይ የሚፈፀሙ ችግሮች በመሆናቸው ለመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤ መሆናቸዉን ገልፀዋል።

እነዚህ ወንጀሎች ካላቸዉ ረቂቅ እና ዉስብስብ ባህርይ አንፃር ለምርመራ አዳጋች መሆናቸዉን የገለፁት ኃላፊዉ፥ ወንጀሎቹን መከላከል የሕዝብ እና የመንግስት ሃብትን ከምዝበራ ለመታደግ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይም በተቋም ደረጃ የዓቃብያነ-ህግ እና የፖሊስ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር የሙስ እና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎችን ለመከላከል አይነተኛ ሚና እንዳላቸዉም ነዉ አቶ ታመነ የገለፁት።

በተቋሙ የታክስና ኢኮኖሚ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር አቶ ውብሸት ጀመረ በስልጠናዉ ወቅት እንደገለፁት የሙስና እና ታክስ ነክ ወንጀሎች በመንግስት የልማት ድርጅቶችና ኢኮኖሚ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች መሆናቸዉን ገልፀዉ፥ እነዚህን ወንጀሎች በመከላከል የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከግለሰብ ጀምሮ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸዉን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ሙሰኞችን ለህግ አቅርቦ ከማስቀጣት ባለፈ የተመዘበረዉን ሃብት ከማስመለስ አንፃር የክልሉ ፍትህ ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የጀመሩትን ህግ የማስከበር ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለፁት ደግሞ በክልሉ ፍትህ ቢሮ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር አቶ ይንገስ ታደለ ናቸዉ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፍትህ ቢሮ በመሰረታዊ ሕጎች እና በሥነ-ሥርአት ህጎች ዙሪያ በየደረጃው ላሉ መዋቅሮችና በክልሉ ለሚገኙ መርማሪ ፖሊሶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መርሃ ግብርን በሚዛን አማን ከተማ አካሂደዋል።

ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናዉ ወቅታዊና በተለይ ከጥቆማ ጀምሮ በምርመራ ሂደት ዉስጥ የሚፈፀሙ ክፍተቶችን የሚፈታ መሆኑን መናገራቸውን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡