በሐሰተኛ ሰነድ የይዞታ ካርታ አውጥቶ ሸጧል የተባለው ተከሳሽ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ
******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሐሰተኛ ሰነድ 72 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ካርታ አውጥቶ በ5 ሚሊየን ብር ሸጧል የተባለው ተከሳሽ ተፈራ አበራ ተከስተ በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ወሰነ።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ ተደራራቢ ክሶችን አቅርቦ ነበር።
በዚህም ባቀረበው 1ኛ ክስ ላይ ተከሳሹ የሙስና ወንጀልን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 1፣ ንዑስ ቁጥር 2/ሀ እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ስሙን ቀይሮ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በመጠቀም በመስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኝ ጅምር ግንባታ ላይ የነበረ 72 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ሐሰተኛ ካርታ በማውጣት ሰናይት ሃይሌ ለተባለች ግለሰብ በ5 ሚሊየን ብር መሸጡን ጠቅሶ በክሱ ላይ አስፍሯል።
በ2ኛ ክስ ላይ ዐቃቤ ሕግ በህገወጥ መንገድ የተገኘ ንብረትን ወይም ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል አዋጅ ቁጥር 780 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በህገወጥ መንገድ ያገኘውን ገንዘብ ምንጩን መደበቅ ወንጀል ፈጽሟል በማለትም ክስ አቅርቦበታል።
በሌላ በኩል ዐቃቤ ሕግ በዚሁ ተከሳሽ ላይ በ3ኛ ክስ የሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 1፣ ንዑስ ቁጥር 2/ሀ እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በሐሰተኛ ሰነድ ካርታ የወጣለትን ይዞታ ለ3ኛ ሰው በተዘዋዋሪ ተሽጧል የሚል ክስ አቅርቦበት የነበረ ቢሆንም ይህ ክስ ከአንደኛ ክስ ጋር ተጠቃሎ እንዲቀርብ በፍርድ ቤቱ በመታዘዙ ተጠቃሎ እንዲታይ ተደርጓል።
ተከሳሹ የክስ ዝርዝር ከደረሰው በኋላ ወንጀሉን አለመፈጸሙን ገልጾ የሰጠውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦበታል።
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ በተከሰሰበት ድንጋጌ እንዲከላከል በሰጠው ብይን ተከሳሹ 3 የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው ማስተባበል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል። ከዚህም በኋላ ተከሳሹ አምስት የቅጣት ማቅለያ አስተያየት አቅርቧል። በዐቃቤ ሕግ በኩል ግን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት አልቀረበም።
ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ ያቀረበውን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመያዝ ዛሬ በዋለው ችሎት ተከሳሹን በዕርከን 29 መሰረት በ10 አመት ጽኑ እስራትና በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ኮሚሽኑ በ25 የዘርፍ ተቋማት ውስጥ ከሚሰሩ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ስራ አስፈፃሚዎች እና ባለሙያዎች ጋር የግንዛቤ መፍጠሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ25 የዘርፍ ተቋማት ውስጥ ከሚሰሩ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ስራ አስፈፃሚዎች እና ባለሙያዎች ጋር የግንዛቤ መፍጠሪያ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
የውይይቱ መድረኩ ዋና ዓላማ በሙስና መከላከል ዋና ዋና ተግባራት ላይ በምን መልኩ መስራት እንደሚገባ ግንዛቤ ለመስጠት ታሳቢ ያደረገ ሲሆን፣ የሙስና መረጃ ቅበላና የሀብት ምዝገባ አያያዝ፤ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራዎች እና የሙስና መከላከል ስትራቴጂ አስፈላጊነት በሚሉ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሙስና መረጃ ቅበላና የሀብት ምዝገባ አያያዝ በተመለከተ በኮሚሽኑ የሙስና መረጃ አሥተዳደርና የሀብት ምዝገባ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፈርዳ ገመዳ ሀሳብ የሰጡ ሲሆን የሙስና ጥቆማ በሚደረግበት ወቅት ጠቋሚው አካልም ሆነ ተቋም አስፈላጊውን ጥንቃቄን ማድረግ እንደሚገባ እና በሀብት ምዝገባ ወቅትም የግለሰቦችን ሚስጥር መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በኮሚሽኑ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሸው በበኩላቸው አስቸኳይ ሙስና ማለት ሙስና ሊፍጸም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ሲታወቅ ድርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት እንዳይፈጸም ማቋረጥ ነው ብለዋል፡፡ ስልጣንን ያለ አግባብ ተጠቅሞ የሙስና ወንጀል እንዳይፈጸም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር የህዝብ እና የመንግስት ሃብት ከምዝበራ ማዳን እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡
የውይይት መድረኩ በሁሉም ዘርፎች በሙስና መከላከል ስትራቴጂ ዝግጅት ተሳትፎ ማድረግ ያላቸውን ሚና ለመለየት ከማስቻሉም በላይ በዘርፉ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ ለማዘጋጀት ይረዳቸዋል ያሉት በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ጥናት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድይራድ ሰይፍ ናቸው፡፡
በውይይቱ መድረኩ ለተሰጡ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ እና ም/ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው ተገኝተው ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ጉቦ የተቀበሉ የመሬት ሊዝ አስተዳደር ፅ/ቤት ሰራተኞች እጅ ከፍንጅ ተያዙ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 23/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጉዳይ ለመፈፀም 1 ሚሊየን 4 መቶ ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ ሁለት የመሬት ሊዝ አስተዳደር ፅ/ቤት ሰራተኞች እና ተባባሪያቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የቅንጅት ስራ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር መስፍን በላቸው እንደገለፁት በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር የቦታ ርክክብና ክትትል ቡድን መሪ እና የሊዝ ማስተላለፍ ባለሙያ ሲሆኑ፥ ሶስተኛዋ ተጠርጣሪ ደግሞ ለወንጀሉ ተባባሪ የሆነች የሊዝ ማስተላለፍ ባለሙያው እህት ነች፡፡
የግል ተበዳይ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በሊዝ የገዙትን ቦታ ለመረከብ ሲመላለሱ ከቆዩ በኋላ የግንባታ ማስጀመሪያ ፈቃድ እንዲራዘምላቸው ለመጠየቅ አገልግሎት ፈልገው ነበር ወደ ክፍለ ከተማው አስተዳደር የሄዱት፡፡
ይሁን እንጂ ተጠርጣሪዎቹ ተገቢውን አገልግሎት መስጠጥ ሲጠበቅባቸው ቀጠሮ በማብዛት ሲያመላልሷቸው እንደነበር እና ጉዳዩን ለመፈፀም ገንዘብ እንደተጠየቁ የግል ተበዳይ መግለፃቸውን ኮማንደር መስፍን አስረድተዋል፡፡
"በሊዝ የተገዛው ቦታ መንገድ ዳር በመሆኑ እኛ ለምንፈፅምልዎት ጉዳይ የሚከፍሉን ገንዘብ ይጨምራል" የሚል መደራደሪያ ሃሳብ በማቅረብ ተጠርጣሪዎቹ 3 ሚሊዮን ብር ጠይቀው እንደነበር እና በመጨረሻም ወደ 1 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ ብር ዝቅ እንደተደረገ ኮማንደር መስፍን አብራርተዋል፡፡
ከተጠየቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ሚሊዮን 2 መቶ ሺህ ብሩ የሊዝ ማስተላለፍ ባለሙያው በሆነው ተጠርጣሪ እህት የባንክ ሂሳብ ውስጥ እንዲገባ መደረጉን የጠቀሱት የምርመራ ሃላፊው፥ ከግል ተበዳይ በቀረበ አቤቱታ በአዲስ አበባ ፖሊስ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ክትትል 200 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የማህበራዊ የትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር(መተግበሪያ)፡- https://epfs.gov.et

በጅማ ከተማ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታን ላልተገባ ጥቅም በማዋል መንግስትን ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ አሳጥተዋል የተባሉ ተከሳሾች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በጅማ ከተማ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታን ላልተገባ ጥቅም በማዋል መንግስትን ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ አሳጥተዋል የተባሉ ተከሳሾች በ15 አመት ጽኑ እስራት እና በገንዘብ እንዲቀጡ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ወሰነ።
የቅጣት ውሳኔው የተላለፈባቸው ተከሳሾች የጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የቀድሞ ፕላንና መሬት አስተዳደር ኃላፊ ሼራብ አባሜጫ አባጎጃም እና የጅማ ከተማ የቀድሞ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አወል አባሜጫ አባቡሉ ናቸው።
የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተከሳሾቹን በቁጥጥር ስር አውሎ የተለያዩ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን ለኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ዐቃቤ ሕግ አስረክቧል።
ዐቃቤ ሕግም ተከሳሾቹን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ እና ለ አንቀጽ 407 ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል በማለት በመጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ተደራራቢ ክስ አቅርቦባቸዋል።
በክሱ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሾቹ በቁጥጥር ስር ያልዋለው በክስ መዝገቡ በ3ኛ ተራ ቁጥር ከተጠቀሰው የጅማ ከተማ የመሃንዲስ መሪ ከነበረው ሰዓዲ አቢዩ ነገኦ ከተባ ተከሳሽ ጋር በጥቅም በመመሳጠር 2ኛ ተከሳሽ በወላጅ እናቱ ስም እና ፊርማቸውን አስመስሎ በመጠቀም 10 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ያቀረበ በማስመሰል ማመልከቻ ማስገባቱ ተጠቅሷል።
በማመልከቻው መነሻነት 1ኛ ተከሳሽና 3ኛ ተከሳሽ በጋራ በመሆን አንድ ካሬ ሜትር በ1 ብር ከ50 ሳንቲም በሊዝ የተሰጠ አስመስለው ለ2ኛ ተከሳሽ በጊንጆው ጉድሉ ቀበሌ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታ እንዲወስድ ማድረጋቸው በክሱ ተገልጿል።
በተጨማሪም ለክሊኒክ ግንባታ በሚል በ3ኛ ተከሳሽ ፕላንና ካርታ አዘጋጅነት በ1ኛ ተከሳሽ አጽዳቂነት መስጠታቸው ተዘርዝሯል።
ባጠቃላይ ይዞታው በሊዝ ቢሸጥ ኖሮ ሊገኝ የሚችለውን ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማሳጣታቸው በክሱ ተጠቅሷል።
በዚህ መልኩ ፍርድ ቤት ቀርበው የቀረበባቸውን ክስ የተከታተሉት 1ኛና 2ኛ ተከሳሾች ወንጀሉን አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው በሰጡት የዕምነት ክህደት ቃል መነሻ ፍርድ ቤቱ በዐቃቤ ሕግ የቀረቡ የተለያዩ የምስክር ቃልና የሰነድ ማስረጃዎችን ተመልክቷል።
የቀረበባቸውን ማስረጃ እንዲከላከሉ ብይን የተሰጣቸው ተከሳሾቹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መስተባበል ባለመቻላቸው በተከሰሱበት ድንጋጌ የጥፋተኝነት ፍርድ መተላለፋን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ፍርድ ቤቱ በዐቃቤ ሕግ በኩል ተከሳሾቹ ወንጀሉን በጥቅም በመመሳጠር የፈጸሙት መሆኑ ተጠቅሶ የቀረበውን የቅጣት ማክበጃ እና የተከሳሾቹ የቤተሰብ አስተዳዳሪና የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለባቸው ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ ይዟል።
በዚህም ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸውን በ15 አመት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዢን ኃላፊ ም/ኮማንደር ገዛኸኝ አጉቾ ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ከሸገር ከተማና በስሩ ከሚገኙ የክ/ከተማ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በጥቅም ግጭት መለየትና የሀብት ምንጭ ትክክለኛነት ማጣራት ሥራ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ
********
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሸገር ከተማና በስሩ ከሚገኙ ከ12ቱ ክ/ከተማ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በጥቅም ግጭት መለየትና የሀብት ምንጭ ትክክለኛነት ማጣራት ሥራ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል፡፡
የውይይቱ መድረኩ ዓላማ የጥቅም ግጭት ፅንሰ ሃሳብ እና መሠረታዊ መንስኤዎችን በመረዳት ለጥቅም ግጭት ተጋላጭ በሆኑ ዘርፎችና አሰራሮች ላይ በማተኮር እንደ ክ/ከተማው ነባራዊ ሁኔታ የጥቅም ግጭት የመለየት ወይም የሀብት ምንጭ ትክክለኛነት የማጣራት ሥራን በተሻለ ጥራትና ግንዛቤ እንዲያከናውኑ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከመረጃ ሰጭ ተቋማት ጋር የተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ በዋናነት የጥቅም ግጭት ምንነት፣ አይነቶች፣ ገፅታዎች፣ ህጋዊ መነሻዎች፣ መሠረታዊ መንስኤዎች እና ለጥቅም ግጭት የሚያጋልጡ ሁኔታዎች እንዲሁም የጥቅም ግጭት እና ሙስና፣ ለጥቅም ግጭት ተጋላጭ የሆኑ ዘርፎችና አሰራሮች፣ የሚያስከትለው ጉዳት፣ የመከላከልና ማስተዳደር ስልቶች እንዲሁም የጥቅም ግጭት መከላከል (ሀብት ማጣራት) አስፈላጊነት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
በውይይቱ መድረኩ ለተሰጡ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጥቅም ግጭት መከላከል ዴስክ ኃላፊ አቶ ከተማ ኃይለስላሴ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ በቀጣይም ኮሚሽኑ በሚያከናውናቸው የሀብት ምንጭ ትክክለኛነት የማጣራት ስራዎች የከተማውና የክ/ከተማው ፅ/ቤት ኃላፊዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።