Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጥቅም ግጭት (Conflict of interest) ምንነት

******************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር ለመላክ ከግለሰቦች ገንዘብ የተቀበለችው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣች

******************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 22/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዐቃቤ ሕግ በህገ-ወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ አገር ለመላክ ገንዘብ ከግለሰቦች ተቀብለሻል ባላት ግለሰብ ላይ ክስ መስርቶባት ክርክሩ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

ተከሳሽ ደመቀች ማጉጄ አቤቱ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 27/1/ እና በሰው የመነገድና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀጽ 11/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በዐቃቤ ሕግ ስድስት ክስ ቀርቦባታል፡፡

ተከሳሽ ወደ ውጭ አገር ሰውን ለስራ ለመላክ ፍቃድ ሳይኖራት ቀኑ በውል ተለይቶ ባልታወቀ ከሀምሌ ወር 2013 እስከ መስከረም ወር 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የተለያዩ 6 ተበዳዮችን ወደ ጆርዳን አገር ልኬ ስራ አስቀጥራችኋለሁ፣ ለዝግጅቱ እንደዚሁም ለህክምና ምርመራ ብር ትከፍላላችሁ በማለት ፓስፖርት እና ፎቶግራፍ በመቀበል፣ ከ1ኛ ተበዳይ 29 ሺህ 500 ብር፣ ከ2ኛ ተበዳይ 32 ሺህ 500 ብር፣ ከ3ኛ ተበዳይ 33 ሺህ 500 ብር፣ ከ4ኛ ተበዳይ 39 ሺህ ብር፣ ከ5ኛ ተበዳይ 25 ሺህ ብር፣ ከ6ኛ ተበዳይ 23 ሺህ ብር ተቀብላለች፡፡

ቀጥሎም ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት ጆርዳን አገር ስለምትሄዱ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቀድማችሁ መድረስ አለባችሁ ብላ በመንገር እና ከሌሎች የግል ተበዳዮች ጋር ታክሲ በማሳፈር ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ሲሆን ቦሌ አየር ማረፊያ ካደረሰቻቸው በኋላ ግብረ-አበሯ የሆነውና ለጊዜው በቁጥጥር ስር ያልዋለ ግለሰብ የበረራ ትኬት ይዞ እየመጣ ነው በሚል ሲጠብቁ ሳይመጣ ቀርቶ የበረራ ሰዓት አልፎ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት ሲሆን ነገ ትሄዳላችሁ አሁን አልጋ ይዘን ታድራላችሁ በማለት እየተመለሱ እያለ በጸጥታ አካላት የተያዙ በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመችው በህገ-ወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ አገር መላክ ሙከራ ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ተከሳሽ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት ቀርባ የተከሰሰችበት ክስ በችሎት ተነቦላት ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለቷ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንድትከላከል ብይን ተሰጥቶ ተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮችን አቅርባ ያሰማች ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበባትን ክስ መከላከል ባለመቻሏ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሿ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠትና የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ30 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ እንዲሁም ከህዝባዊ መብቶቿ ለ5 ዓመት ታግዳ እንድትቆይ ሲል መወሰኑን ፍትህ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገፁ መረጃውን አጋርቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር(መተግበሪያ)፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትና መገልገል የሚያስከትለው ተጠያቂነት

******************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር(መተግበሪያ)፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በክልሉ የተጀመረው የሀሰተኛ ትምህርት መረጃ ማጥራት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - አቶ አስራት አዳሮ

******************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 22/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተጀመረው የሀሰተኛ ትምህርት መረጃ ማጥራት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አስራት አዳሮ ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

ቢሮው ቀልጣፋ፣ ፈጣንና ተገልጋይን የሚያረካ የመንግሥት አግልግሎት ለዜጎች ለማቅረብ የሚያስችል የለውጥ አሰራሮች ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ከክልሉ ስድስቱም ዞኖች ለተወጣጡ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ለቀጣይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

ክልሉ ከተደራጀ ወዲህ የመንግሥት አግልግሎት አሰጣጥን ለተገልጋዮች ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ መጠነ ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹት የቢሮ ኃላፊ አቶ አስራት አዳሮ፤
ከነዚህም ውስጥ በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ መነሻ የመዋቅር ማጣጣምና መልሶ ማደራጀት ስራ አንዱ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም ወጪዎችን በመቀነስ የመንግሥት የአግልግሎት አሰጣጥን ዘመናዊና ቀልጣፋ የማድረግ ተግባር ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተናግረዋል።

በቢሮክራሲ የተተበተበውን የአግልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን ተቋማዊ የመፈጸም አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ የገለጹት አቶ አስራት፤ በክልሉ የተጀመረው የሀሰተኛ ትምህርት መረጃ ማጥራት ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ስልጠናው በሰው ሀብት አደረጃጀት ተግባራት፣ በኢንስፔክሽን ጥናት ሰነድ ትግበራ፣ የሰው ሀብት መረጃ አያያዝ፣ በተቋም ተኮር የለውጥ ትግበራ እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፈታት ላይ የሚያተኩር መሆኑን ከወጣው መርሀግብር መገንዘብ መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር(መተግበሪያ)፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በንግዱ ዘርፍ የሚስተዋለውን የሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭነት ለማስቀረት በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገለፀ

******************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 22/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በሥነምግባር፣ በሙያ ሥነምግባር እና በንግድ ሙያ ላይ የብልሹ አሰራር ተጋላጭነት ዙሪያ ስልጠና መስጠቱ ተገለፀ፡፡

የንግድ ቢሮ የከተማዋን ፋይናንስ የሚያንቀሳቅስና ትልቅ ተልዕኮ የያዘ ተቋም በመሆኑ ከሙስና እና ከብልሹ አሰራር እንዲሁም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆኑ ተቋማትን በጥናት በመለየትና ዘርፍ ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት በሥነምግባር ግንባታ እና በሙስና መከላከል ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ አቶ ጀንበሩ ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው የንግድ ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰልጣኞች በቆይታቸው ስለ ሥነምግባር፣ የሥነምግባር መርሆች፣ የሙስና ምንነት፣ ሙስና የሚያስከትለው ጉዳት እና የሙስና ተጋላጭነት መንስኤዎች እንዲሁም በቀጣይ መደረግ ስላለባቸው ጉዳዮች ላይ ስልጠና እንደሚወስዱ ዳይሬክተሩ መጠቆማቸውን ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገፁ መረጃውን አጋርቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር(መተግበሪያ)፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የነቃ ተሳትፎ ያስፈልጋል!