Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
1 ሚሊየን ብር ጉቦ ሲቀበል ተገኝቷል የተባለው የጉሙሩክ አስተላላፊ ተከሰሰ

**

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) 1 ሚሊየን ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል በተባለው የጉምሩክ ትራንዚስተር (አስተላላፊ) ላይ የሙስና ወንጀል ክሥ ተመሰረተ።

ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን፥ ተከሳሹ የጉምሩክ ትራንዚስተር (አስተላላፊ) ግዑሽ አዳነ አበራ እንደሚባልም ተመላክቷል፡፡

የፍትኅ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬቶሬት ዐቃቢ-ሕግ ተከሳሹን የሙስና ወንጀል አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 27 ሥር የተደነገገውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት በተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦበታል።

በዚህም ባቀረበበት የሙስና ወንጀል ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ በሚሰራው የጉምሩክ አስተላላፊነት ስራ መሰረት ከቀረጥ ነጻ ለኢንቨስትመንት የገባን “ቶዮታ ሀይሉክስ” ተሽከርካሪ ÷ ነብዩ ቡሽራ ጅማ ከተባለ የግል ተበዳይና 1ኛ የዓቃቢ ሕግ ምስክር ከሆነው ግለሰብ ጋር በመሆን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ለመፈፀም በመስማማት የግል ተበዳይን የሰባት ዓመት የመኪናውን ቀረጥ እና ታክስ 1ሚሊየን 511 ሺህ 356 ከ66 ሣንቲም እንዲከፍሉና ተሸከርካሪውን በአካል እንዲያቀርቡ መናገሩን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ዝርዝር ላይ አስፍሯል።

ከዚህም በኃላ የግል ተበዳይ በኅዳር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ልዩ ቦታው ሳሪስ አቦ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ሲቀርቡ ተከሳሹ ተሽከርካሪው ለጥያቄ እንደሚፈለግ እና መሿለኪያ ኃይሌ ይርጋ ሕንጻ ላይ በሚገኘው የጉምሩክ ዋና መሥሪያ ቤት መጠየቅ እንዳለባቸው መግለጹም ተጠቅሶ በክሱ ዝርዝር ተካቷል።

በዚህ መልኩ ተሽከርካሪው እንዲለቀቅ ከጉምሩክ ኮሚሽን ኃላፊዎች ጋር እንደሚያደራድራቸው ለግል ተበዳይ በመንገር እና መኪናውን ለመልቀቅ የግል ተበዳይ 1 ሚሊየን ብር እንዲከፍሉ ኃላፊዎች መግለፃቸውን በማሳወቅ በኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 7 ሠዓት ከ30 አካባቢ ቦሌ መድሃኒያለም አከባቢ ልዩ ቦታው ኦኬዥን ካፌ ውስጥ ከግል ተበዳይ ጋር በመገናኘት 1 ሚሊየን ብር በአቢሲኒያ ባንክ የተጻፈ ቼክ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በክሱ ተጠቅሶ ዐቃቢህግ የማቀባበል የሙስና ወንጀልክስ አቅርቦበታል።

ዐቃቤ ሕግ ከክስ ዝርዝሩ ጋር የሰውና የሠነድ ማስረጃ አያይዞ ማቅረቡን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ተከሳሹ ችሎት ቀርቦ ክሱ እንዲደርሰው ከተደረገ በኋላ የክስ ዝርዝሩ በችሎት በንባብ ተሰምቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
መልካም ሥነ-ምግባር ለውጤታማ የገቢ አሰባሰብ አይነተኛ ሚና እንዳለው ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በገቢዎች ሚኒስቴር የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራር እና የሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለተውጣጡ አመራሮች እና ሰራተኞች በሥነ-ምግባር ላይ እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያግዝ ስልጠና በቢሾፍቱ ከተማ እየተሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው ባለፉት አምስት ወራት የተሰሩ ስራዎችን በመገምገምና የተሻለ አፈፃጸም ካስመዘገቡ ቅርንጫፎች ልምድ ለመለዋወጥ፣ ብሎም ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የተጠኑ ጥናቶችን በጋራ በመወያየት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን መፍታት ያለመ መሆኑን በሚኒስቴሩ የተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራር እና የሥነ-ምግባር ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ደስታ ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ሰነድ አቅርበው ያወያዩት እና በተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚታዩ ክፍተቶችን የአሰራር ስርዓት ጥናት በማድረግ መዝጋት ያስፈልጋል ያሉት በሚኒስቴሩ የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር አንድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራር ቡድን አስተባባሪ አቶ አማረ አለነ ሲሆኑ፥ ሰልጣኞች ጥፋት አጥፍቶ የተገኘ ሰራተኛን እንዴት መመርመር እንዳለባቸውና በጥፋቱ ልክ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ እንዳለባቸው ተጨማሪ ግንዛቤ እንዲያገኙ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን መግለፃቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመልክታል፡፡

ሰልጣኞች በበኩላቸው ሰራተኞች ሥነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉና ከብልሹ አሰራር ራሳቸውን እንዲቆጥቡ ይህን መሰል ግንዛቤን የሚያጎለብት ስልጠና መሰጠቱ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው፥ ሚኒስቴሩ ለብልሹ አሰራር ምክንያት የሚሆኑ የአሰራር ክፍተቶችን ቀድሞ እየለየ በጥናት የተደገፈ ስራ ሊሰራ እንደሚገባም አሳስብዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽኑ በማሕበር ለተደራጁ አካላት የሚደረገው የመሬት አሰጣጥ ግልፅና ተጠያቂነት ባለው አኳኋን መፈፀም እንዳለበት አስታወቀ

******************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤሻንጉል ጉምዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በማሕበር ለተደራጁ አካላት የሚደረገው የመሬት አሰጣጥ ግልፅና ተጠያቂነት ባለው አኳኋን መፈፀም እንዳለበት አስታወቀ፡፡

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽር አቶ መንግስቱ ላሎ በዘርፉ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችን ለመዝጋትም ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር መዘርጋት፣ ደንብና መመሪያዎችን አክብሮና ጠብቆ መስራት ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመዝጋትም ኮሚሽኑ ረዘም ያለ ጊዜ በመውስድ በአሶሳ ከተማ አስተተዳር መሬት ልማት ማኔጅመንት የከተማ ቦታ አሰጣጥ ላይ ባደረገው የአሰራር ስርዓት ጥናት ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ 10 ግኝቶችን የጠቆመ ሲሆን፣ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ምክረ ሐሳቦችንም አመላክቷል፡፡

ጥናቱን ያቀረቡት በኮሚሽኑ የአሰራር ጥናት ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ፍቃዱ ሰብስቤ በዋናነት የመረጃ አያያዝና ልውውጥ ክፍተቶች አገልግሎቶች እንዲጓተቱና ዘርፉ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ እንዲሆን መደረጉንአስረድተዋል፡፡

ችግሮችን ለመፍታትም አሰራሮችን በማዘመንና ከሰው ንክኪ በጸዳ መልኩ በቴክኖሎጅ መፈፀም፣ ስራውን በባለቤትነትና በተጠያቂነት መስራት የሚያስችሉ እንደ መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ አሰራሮችን መዘርጋትና ለውጤታማነት መጠቀም እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ በጥናቱ የተለዩ ምክረ ሃሳቦችንም መተግበር የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል፡፡

በጥናት ግኝቱ ውይይት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱልከሪም አብዱራሂም ጨምሮ የከተማ አስተዳድሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገፁ መረጃውን አጋርቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሙስና በሁሉም ዘርፎች የሚያስከትለውን ጉዳት በመረዳት በህብረት መታገል ይኖርብናል!

*************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀሰተኛ የታክስ ደረሰኞችን በማዘጋጀትና መገልገል እንዲሁም ያለፍቃድ መነገድ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ150 ሺህ ብር እንዲቀጣ ውሳኔ ተላለፈበት

************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገት ሊያደናቅፉ የሚችሉ ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን በንቃት መከላከል ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር ነው - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገት ሊያደናቅፉ የሚችሉ ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን በንቃት መከላከል ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር ነው ሲል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ በክልሉ ለሚገኙ የዞን፣ የከተማና የወረዳ የሥነ-ምግባር መከታተያ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ እየሰጠ ይገኛል፡፡

የፀረ-ሙስና ትግሉ ከተጀመረ ዘመናትን ያስቆጠረ ቢሆንም በሀገሪቱ ዕድገትና ብልፅግና ላይ እስከአሁን እያሳደረ ያለው ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል፡፡

ይህን ተከትሎ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራውን ጨምሮ በሙሰኞች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ጠንካራ ሊሆን እንደሚገባም ይነገራል፡፡

በክልሉ ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ላይ እንቅፋት ሊፈጥር የሚችለውን የሙስና እና ብልሹ አሰራርን ፈር ለማሲያዝ የታሰበለት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሚጀመርበት ወቅት የክልሉ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሶፊኒያስ ደስታ ኮሚሽኑ በክልሉ በሁሉም ዘርፎች የሚስተዋሉ የሥነ-ምግባር እና ብልሹ አሰራሮችን ለመጋፈጥ በሚያስችል ቁመና ላይ እንዳለም አስታውቀዋል፡፡

በይበልጥ ከመሬት ወረራና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ከዚህ ቀደም የነበረው ብልሹ አሰራር ክልሉን እየተፈታተነው ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፥ ይህንን ተከትሎ ቀድሞ የመከላከልና ብልሹ አሰራሩ ተፈጥሮ ሲገኝ የማጣራትና የህግ እርምጃ የሚወሰድበትን ሂደት መጀመሩንም አስታውቀዋል፡፡

ኮሚሽኑ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ በኋላ አስር የተለያዩ ጥቆማዎች የደረሱት ሲሆን፥ በእነዚህም ላይ የማጣራት ሥራ እየተሰራባቸው ስለመሆኑ የጠቆሙት ኮሚሽነር ሶፍኒያስ የማጣራት ሥራው ሲጠናቀቅም ጥፋተኞች ላይ የማያዳግም እርምጃም እንደሚወሰድባቸውም ተናግረዋል፡፡

የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ሊያደናቀፉ የሚችሉ ብልሹ አሰራሮችን በንቃት መከላከል ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር ነውም ብለዋል፡፡

በስልጠናው ላይ ተሳታፊዎች በበኩላቸው አዲስ የተሻሻለው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሙስና እና ብልሹ አሰራር ትግልን የበለጠ የሚያጠናክርና ለዘርፉ ባለሙያዎች አቅም እንደሚሆናቸውም ተናግረዋል፡፡

በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተሰጠ ያለው ሥልጠና ብልሹ አሰራሮችንና በይበልጥ ከግዥ ጋር ተያያዥነት ያሉ ሌብነቶች ከመከሰታቸው አስቀድሞ ለማክሰም የሚረዳ አቅም እንደሚፈጥርላቸው የተናገሩት ሠልጣኞቹ ክልሉም ሆነ አከባቢያቸው ከሚሰሩ የልማት ተግባራት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ እንደሚያግዙም ተናግረዋል፡፡

ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭነት ሥጋት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚሰጠው ሥልጠና የዞን፣ የከተማና የወረዳ የሥነ-ምግባር መከታተያ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሲሆኑ ስልጠናውም ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡