ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመጠቀም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅጥር ፈጽመዋል የተባሉ በእስራት ተቀጡ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀሰተኛ የሆነ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ በመጠቀም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምቦ ዲስትሪክት የስራ ቅጥር ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች በእስራት እንዲቀጡ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ወሰነ።
ተከሳሾቹ ወንጀሉን መፈጸማቸውን አምነው ለችሎቱ ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ማስረጃ መስማት ሳያስፈልገው በተከሳሾቹ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፏል።
የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ስር የተመላከተውን ድንጋጌን ተከሳሾቹ ተላልፈዋል በማለት ሀሰተኛ መንግስታዊ ወይም ህዝባዊ ሰነዶችን አዘጋጅቶ መጠቀም የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸው ነበር።
ክሱ የቀረበባቸው ተከሳሾች በአጠቃላይ 12 ሲሆኑ፤ ከነዚህ መካከል ባጂጌ ከበደ፣ ግርማዬ ደገፉና በሬዳ ነበራ ይገኙበታል።
የቀረበው ክስ ላይ እንደሚያመላክተው ተከሳሾቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምቦ ዲስትሪክት በወጣ የስራ ማስታወቂያ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ የስራ ቅጥር ውል ስምምነት መፈጸማቸው በክሱ ተጠቅሷል።
ከተከሳሾቹ መካከል 10ሩ የቅጥር ውል ከፈጸሙ በኋላ ለ10 ወራት በየደረጃው በተለያዩ መጠን ወርኃዊ ደመወዝ መውሰዳቸውን ዐቃቤ ሕግ በክሱ አመላክቷል።
ቀሪዎቹ ማለትም ሁለት ተከሳሾች ደግሞ የስራ ቅጥር ውል ስምምነት ከፈጸሙ በኋላ የማስረጃ ማጣራት ስራ ሲጀመር መሰወራቸው ዐቃቤ ሕግ በክሱ አመልክቷል።
በዚህም መልኩ ዐቃቤ ሕግ ሀሰተኛ መንግስታዊ ወይም ህዝባዊ ሰነዶችን አዘጋጅቶ መጠቀም የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ የቀረበው ክስ ዝርዝር ለተከሳሾቹ እንዲደርስ በማድረግ የክስ ዝርዝሩ በችሎት በንባብ አሰምቶ ነበር።
ዐቃቤ ሕግ ከክሱ ጋር ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አያይዞ አቅርቧል።
የዋስትና መብታቸው ታግዶ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ብይን የተሰጠባቸው ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ተከታትለዋል።
በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸው የክስ ዝርዝር እንዲሻሻልላቸው ተከሳሾች የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ቢያቀርቡም፤ ዐቃቤ ሕግ ክሱ ግልጽ መሆኑን ጠቅሶ ሊሻሻል አይገባም የሚል መልስ በጽሁፍ አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ የክስ መቃወሚያ ጥያቄው ክሱ እንዲሻሻል የሚያስችል የህግ መሰረት የለውም በማለት ውድቅ አድርጓታል።
ከዚህም በኋላ ተከሳሾቹን የዕምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደርጎ ተከሳሾቹ የወንጀል ተግባሩን መፈጸማቸውን አምነው ለችሎቱ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
በዚህም ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ምስክር መስማት ሳያስፈልገው በተከሳሾቹ ላይ በተከሰሱበት ድንጋጌ የጥፋተኝነት ፍርድ ማስተላለፉን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ተከሳሾቹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት በማመናቸው፣ የቀደመ የወንጀል ሪከርድ አለመኖሩንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን በቅጣት ማቅለያ ታሳቢ በማድረግ ፍርድ ቤቱ እያንዳንዳቸውን በ1 አመት ከ 8 ወራት እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ኮሚሽኑ ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብ እና የመንግስትን ሀብት ከብክነት ማዳን መቻሉን አስታወቀ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብ እና የመንግስትን ሀብት ከብክነት ማዳን መቻሉን አስታወቀ።
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መንግስቱ ላሎ እንደገለፁት ኮሚሽኑ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ በአዋጅ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ጠቁመው፥ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በጥናትና ምርምር የተለዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ለ165 ሺህ ተሳታፊዎች ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡
በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማነታቸውን ከማረጋገጥ ረገድም 17 ያህል ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ስራዎችን በማካሄድ 190 ያህል ምክረ ሀሳቦችን ለየተቋማት መስጠት መቻሉን ነው ኮሚሽነሩ ያብራሩት፡፡
በክልሉ የ33 ሺህ 856 አመራሮች የሀብት ምዝገባ ስራ መሰራቱን ገልፀው፥ የመጀመሪያ 25 አስመዝጋቢ አመራሮች ላይ በተካሄደው የሀብት ማጣራት ስራም 7 መኖሪያ ቤቶችን፣ 4 የድርጅት ቤቶችን እንዲሁም በባንክ አካውንት ወደ 682 ሺህ 775 ብር ማሳገድ መቻሉን ነው ያስታወቁት፡፡
ኮሚሽነር መንግስቱ አክለውም በሶስት ተከታታይ ዓመታት 919 ጥቆማዎችን እና አቤቱታዎችን በመቀበል 65 ሚሊዮን 519 ሺህ 490 ብር የህዝብ እና የመንግስት ሀብት ከብክነት ከማዳን ባሻገር 99 ሺህ ካሬ የከተማ ቦታን ማሳገድ ተችሏል ብለዋል፡፡
ተቋማት ወጥና ግልጽ የሆነ አሰራሮች ከመዘርጋት ረገድ ውስንነት መኖሩ፣ የህዝቡ ግንዛቤ እና ተሳትፎ በሚፈለግ ደረጃ አለመሆኑ፣ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ጠንከር ያለ ውሳኔ አለመሰጠቱ ለዘርፉ ስራ ውጤታማነት ማነቆ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ መናገራቸውን ቤንሻጉል ጉምዝ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ኮሚሽኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ከወትሮው በበለጠ ሁኔታ ለመዋጋት የሚያስችል ቅንጅታዊ አሰራሮችን ከተቋማት ጋር ፈጥረው እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ ይህንኑን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

1 ሚሊየን ብር ጉቦ ሲቀበል ተገኝቷል የተባለው የጉሙሩክ አስተላላፊ ተከሰሰ
**
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) 1 ሚሊየን ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል በተባለው የጉምሩክ ትራንዚስተር (አስተላላፊ) ላይ የሙስና ወንጀል ክሥ ተመሰረተ።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን፥ ተከሳሹ የጉምሩክ ትራንዚስተር (አስተላላፊ) ግዑሽ አዳነ አበራ እንደሚባልም ተመላክቷል፡፡
የፍትኅ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬቶሬት ዐቃቢ-ሕግ ተከሳሹን የሙስና ወንጀል አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 27 ሥር የተደነገገውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት በተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦበታል።
በዚህም ባቀረበበት የሙስና ወንጀል ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ በሚሰራው የጉምሩክ አስተላላፊነት ስራ መሰረት ከቀረጥ ነጻ ለኢንቨስትመንት የገባን “ቶዮታ ሀይሉክስ” ተሽከርካሪ ÷ ነብዩ ቡሽራ ጅማ ከተባለ የግል ተበዳይና 1ኛ የዓቃቢ ሕግ ምስክር ከሆነው ግለሰብ ጋር በመሆን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ለመፈፀም በመስማማት የግል ተበዳይን የሰባት ዓመት የመኪናውን ቀረጥ እና ታክስ 1ሚሊየን 511 ሺህ 356 ከ66 ሣንቲም እንዲከፍሉና ተሸከርካሪውን በአካል እንዲያቀርቡ መናገሩን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ዝርዝር ላይ አስፍሯል።
ከዚህም በኃላ የግል ተበዳይ በኅዳር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ልዩ ቦታው ሳሪስ አቦ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ሲቀርቡ ተከሳሹ ተሽከርካሪው ለጥያቄ እንደሚፈለግ እና መሿለኪያ ኃይሌ ይርጋ ሕንጻ ላይ በሚገኘው የጉምሩክ ዋና መሥሪያ ቤት መጠየቅ እንዳለባቸው መግለጹም ተጠቅሶ በክሱ ዝርዝር ተካቷል።
በዚህ መልኩ ተሽከርካሪው እንዲለቀቅ ከጉምሩክ ኮሚሽን ኃላፊዎች ጋር እንደሚያደራድራቸው ለግል ተበዳይ በመንገር እና መኪናውን ለመልቀቅ የግል ተበዳይ 1 ሚሊየን ብር እንዲከፍሉ ኃላፊዎች መግለፃቸውን በማሳወቅ በኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 7 ሠዓት ከ30 አካባቢ ቦሌ መድሃኒያለም አከባቢ ልዩ ቦታው ኦኬዥን ካፌ ውስጥ ከግል ተበዳይ ጋር በመገናኘት 1 ሚሊየን ብር በአቢሲኒያ ባንክ የተጻፈ ቼክ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በክሱ ተጠቅሶ ዐቃቢህግ የማቀባበል የሙስና ወንጀልክስ አቅርቦበታል።
ዐቃቤ ሕግ ከክስ ዝርዝሩ ጋር የሰውና የሠነድ ማስረጃ አያይዞ ማቅረቡን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ተከሳሹ ችሎት ቀርቦ ክሱ እንዲደርሰው ከተደረገ በኋላ የክስ ዝርዝሩ በችሎት በንባብ ተሰምቷል።

መልካም ሥነ-ምግባር ለውጤታማ የገቢ አሰባሰብ አይነተኛ ሚና እንዳለው ተገለፀ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በገቢዎች ሚኒስቴር የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራር እና የሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለተውጣጡ አመራሮች እና ሰራተኞች በሥነ-ምግባር ላይ እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያግዝ ስልጠና በቢሾፍቱ ከተማ እየተሰጠ ነው፡፡
ስልጠናው ባለፉት አምስት ወራት የተሰሩ ስራዎችን በመገምገምና የተሻለ አፈፃጸም ካስመዘገቡ ቅርንጫፎች ልምድ ለመለዋወጥ፣ ብሎም ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የተጠኑ ጥናቶችን በጋራ በመወያየት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን መፍታት ያለመ መሆኑን በሚኒስቴሩ የተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራር እና የሥነ-ምግባር ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ደስታ ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ሰነድ አቅርበው ያወያዩት እና በተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚታዩ ክፍተቶችን የአሰራር ስርዓት ጥናት በማድረግ መዝጋት ያስፈልጋል ያሉት በሚኒስቴሩ የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር አንድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራር ቡድን አስተባባሪ አቶ አማረ አለነ ሲሆኑ፥ ሰልጣኞች ጥፋት አጥፍቶ የተገኘ ሰራተኛን እንዴት መመርመር እንዳለባቸውና በጥፋቱ ልክ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ እንዳለባቸው ተጨማሪ ግንዛቤ እንዲያገኙ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን መግለፃቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመልክታል፡፡
ሰልጣኞች በበኩላቸው ሰራተኞች ሥነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉና ከብልሹ አሰራር ራሳቸውን እንዲቆጥቡ ይህን መሰል ግንዛቤን የሚያጎለብት ስልጠና መሰጠቱ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው፥ ሚኒስቴሩ ለብልሹ አሰራር ምክንያት የሚሆኑ የአሰራር ክፍተቶችን ቀድሞ እየለየ በጥናት የተደገፈ ስራ ሊሰራ እንደሚገባም አሳስብዋል፡፡

ኮሚሽኑ በማሕበር ለተደራጁ አካላት የሚደረገው የመሬት አሰጣጥ ግልፅና ተጠያቂነት ባለው አኳኋን መፈፀም እንዳለበት አስታወቀ
******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤሻንጉል ጉምዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በማሕበር ለተደራጁ አካላት የሚደረገው የመሬት አሰጣጥ ግልፅና ተጠያቂነት ባለው አኳኋን መፈፀም እንዳለበት አስታወቀ፡፡
የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽር አቶ መንግስቱ ላሎ በዘርፉ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችን ለመዝጋትም ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር መዘርጋት፣ ደንብና መመሪያዎችን አክብሮና ጠብቆ መስራት ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመዝጋትም ኮሚሽኑ ረዘም ያለ ጊዜ በመውስድ በአሶሳ ከተማ አስተተዳር መሬት ልማት ማኔጅመንት የከተማ ቦታ አሰጣጥ ላይ ባደረገው የአሰራር ስርዓት ጥናት ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ 10 ግኝቶችን የጠቆመ ሲሆን፣ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ምክረ ሐሳቦችንም አመላክቷል፡፡
ጥናቱን ያቀረቡት በኮሚሽኑ የአሰራር ጥናት ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ፍቃዱ ሰብስቤ በዋናነት የመረጃ አያያዝና ልውውጥ ክፍተቶች አገልግሎቶች እንዲጓተቱና ዘርፉ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ እንዲሆን መደረጉንአስረድተዋል፡፡
ችግሮችን ለመፍታትም አሰራሮችን በማዘመንና ከሰው ንክኪ በጸዳ መልኩ በቴክኖሎጅ መፈፀም፣ ስራውን በባለቤትነትና በተጠያቂነት መስራት የሚያስችሉ እንደ መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ አሰራሮችን መዘርጋትና ለውጤታማነት መጠቀም እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ በጥናቱ የተለዩ ምክረ ሃሳቦችንም መተግበር የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል፡፡
በጥናት ግኝቱ ውይይት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱልከሪም አብዱራሂም ጨምሮ የከተማ አስተዳድሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገፁ መረጃውን አጋርቷል፡፡

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሙስና በሁሉም ዘርፎች የሚያስከትለውን ጉዳት በመረዳት በህብረት መታገል ይኖርብናል!
*************

ሀሰተኛ የታክስ ደረሰኞችን በማዘጋጀትና መገልገል እንዲሁም ያለፍቃድ መነገድ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ150 ሺህ ብር እንዲቀጣ ውሳኔ ተላለፈበት
************