Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
ለገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራር እና ሰራተኞች ሥነ-ምግባር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራር እና ሰራተኞች ሥነ-ምግባር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ፈቃደ እንደገለፁት ሀገራችን ኢትዮጵያን በጽኑ የኢኮኖሚ መሰረት ላይ ለማቆም ተቋሙ የሚሰበስበው ገቢ ዋነኛ መሰረት መሆኑን አንስተው፥ ተግባራትን ስንሰራ በንጹህ ህሊና እና በንጹህ እጅ መሆን አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በአመራሩ እና በሰራተኛው አመለካከት ላይ በመስራት እና በማነቃቃት መልካም ሥነ-ምግባርን የተላበሰ አገልጋይን ማፍራት ተቋሙ መሰብሰብ ያለበትን ገቢ እንዲሰበስብ የሚያግዝ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የብሬክስሩ ትሬዲንግ አ.ማ ስራ አስኪያጅ እና ማህበረሰብ አንቂ አቶ ነፃነት ዘነበ እንደገለፁት ህይወትን በአዎንታዊ መልኩ እንዴት መቀየር ይቻላል? ቀና አስተሳሰብን መገንባት፣ አገልጋይነት እና ተጽኖ ፈጣሪነት እንዲሁም ስኬታማ ስራ እንዴት እንሰራለን? የሚሉት ሀሳቦች ላይ በማተኮር ለሚያጋጥሙን ችግሮች መፍትሄ በመሰጠት ሀገርን ታማኝ ሆኖ ማገልገል እና ስኬት ላይ አተኩሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑን መናገራቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት መፍጠር የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማጠናከር የጎላ ሚና አለው - ክቡር ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)

**

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 9/2016 ዓ.ም አዳማ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከኮሚሽኑ የሥራ ክፍል መሪ ስራ አስፈፃሚዎች እና ዴስክ ኃላፊዎች እንዲሁም ከ25 የዘርፍ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል አስፈፃሚዎች ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የዘርፎች የ20ኛ የዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አከባበር አፈፃፀም እና የዘርፎች የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ሥራ እንቅስቃሴ ላይ የሱፐርቭዥን ሪፖርትግምገማ ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንደገለፁት ሙስና ለሀገር መሠረታዊ ችግር በመሆኑ መከላከል ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት ያሳሰቡ ሲሆን፥ እያንዳንዱ ዘርፍ በራሱ አቅም ሙስናን መከላከል አስተዳደራዊ ተልዕኮውንም መወጣት አለበት ብለዋል።

ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ አክለውም ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት መፍጠር የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማጠናከር የጎላ ሚና መኖሩን ገልፀዋል።

በውይይቱ ተገኝተው ከመድረኩ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ በበኩላቸው ሙስና ውስብስብ ወንጀል በመሆኑ አሰራራችን በተቀናጀ መልኩ የአቅም ግንባታ ክፍተቶችን በመሙላት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

በተመሳሳይ እቅዶቻችን በመናበብ መስራት  አላማን ከግብ ለማድረስ እንደሚረዳ የገለፁት ም/ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው፥ ሁሉም ዘርፎች ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ኃላፊነት እና ግዴታ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ም/ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው አክለውም የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ እስታንዳርድ እየወጣ መሠራት አለበት ብለዋል።

በመድረኩ ኮሚሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት ትኩረት ከተሰጡት ጉዳዮች መካከል አንዱ ሲሆን፥ የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ፣ የሙስና ጥናት ግኝቶች እና የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠናዎች በትኩረት ተዳሰዋል።

መድረኩ በነገው ዕለትም የሚቀጥል ሲሆን፥ የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴ አፈፃፀም፥ አንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት እንዲሁም የዘርፍ ተኮር የሙስና መከላከል ጥናት ፕሮፖዛል ግምገማ ቀርቦ ውይይት ይካሄድበታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽኑ የሙስና ሥጋት ባለባቸው አምስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሙስና መከላከል ጥናት ሊያካሄድ ነው

*

(የፌ
.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም አዳማ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ በሆኑ አምስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሙስና መከላከል ጥናት ሊያካሄድ ነው።

ይህ የተባለው  የዝርዝር አሰራር ሥርዓት ጥናቱ ፕሮፖዛል ለኮሚሽኑ የሥራ ክፍል መሪ ስራ አስፈፃሚዎች እና ዴስክ ኃላፊዎች እንዲሁም ከ25 የዘርፍ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል አስፈፃሚዎች ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው።

ጥናት ሊካሄድባቸው የተመረጡ እና ፕሮፖዛል የተዘጋጀላቸው  አምስቱ ርዕሰ ጉዳዮች በአገራችን የገቢ ግብር እና ታክስ አሰባሰብ የሙስና እና ብልሹ አሠራር ወንጀል ድርጊቶች መንስኤዎችና መፍትሔዎች፣ በአገራችን የጉምሩክ አሠራር ሥርዓት እና የኮንትሮባንድ እርምጃዎች ውጤታማነት፣ በአገርችን የወጪ እና ገቢ ንግድ የዉጭ ምንዛሪ አስተዳደር የአሠራር ሥርዓት ግልጽነት እና ተጠያቂነት፣ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት አሠራር ሥርዓት ግልጽነት እንዲሁም በአገራችን የዉጭ አገር የሰራተኞች ስምሪት አሠራር ሥርዓት ግልጽነት እና የሰራተኞች ተጠቃሚነት የሚሉ ናቸው፡፡

ጥናቱ የሚካሄድባቸው  አምስቱ ርዕሰ ጉዳዮች በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ጥናት መሪ ሥራ አስፈፃሚ እና ዴስክ ኃላፊዎች ለተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት ተካሄዶባቸዋል።

ከመድረኩ በቀረበው ጥያቄ እና አስተያየት ላይ በም/ኮሚሽነሮች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን  በፕሮፖዛሎች ላይ የተሰጡት አስተያየቶችን በማካተትና በማሻሻል የሙስና መከላከል ጥናት እንደሚካሄድ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!


ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የፋይናንስ ደህንነት ብሔራዊ ኮሚቴ ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ማስቀመጡ ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፋይናንስ ደህንነት ብሔራዊ ኮሚቴ ታህሳስ 08/2016 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ አስቀምጧል።

የፋይናንስ ደህንነት ብሔራዊ ኮሚቴ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአገር ውስጥ ያሉ ተቋማት መካከል የስራ ትብብርና ቅንጅት እንዲጠናከርና ውጤታማ እንዲሆን የተቋቋመ ነው።

የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የፌዴራል የመንግስት ተቋማት የበላይ ኃላፊዎች የተዋቀረ ሲሆን፥ በስሩም በተለያዩ ቴክኒካል የስራ ቡድኖች የተደራጀ ነው።

ብሔራዊ ኮሚቴው ወንጀሎቹን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ጋር በተያያዘ አገራዊ የትብብርና ቅንጅት ስራዎችን ውጤታማነት ከማሳደግ አንጻር የተዘጋጀው የውስጥ የአሰራር ስርዓት ላይ ተወያይቶ ያጸደቀ ሲሆን፥ በዚሁ መሰረት ወደ ስራ እንዲገባ ወስኗል።

በሌላ በኩል ደግሞ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርትኝነትን በገንዘብ መርዳት ጋር በተያያዘ በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ተጠንቶ በቀረበው ጥናት ላይ ተወያይቶ በሚመለከታቸው አካላት በቀጣይ መወሰድ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ማስቀመጡን ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 780/2005 አውጥታ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ትገኛለች።

አዋጁ ወንጀሎቹን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደ ስራ ባህሪያቸው ሃላፊነትን ለይቶ ያስቀመጠ ሲሆን፥ በባለድርሻ አካላት መካከል የሚኖር ትብብርና ቅንጅትም የተጠናከረ እንዲሆን በግልጽ ተመላክቷል።

ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የፌደራል የመንግስት ተቋማት የፋይናስ ደህንነት የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት መካከል የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ይገኝበታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡