Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
ለስድስት የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ተሰጠ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለስድስት ዩኒቨርሲቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናው ከወልቂጤ፣ ከወራቤ፣ ከዋቸሞ፣ ከወላይታ ሶዶ፣ ከጂንካ እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ለተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለሁለት ቀናት በክላስተር መሰጠቱ ተገለጿል።

የሥልጠናው ዓላማ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በግዥ ላይ የሚፈጸመውን ሙስና የመከላከል አቅምን በማሳደግ ከሙስና እና ብልሹ አሠራር የጸዳ የግዥ ሥርዓት እንዲከተሉ ማስቻል ነው ተብሏል፡፡

በመንግስት ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስናን መከላከል እና በሥነምግባራዊ አመራር ላይ ትኩረት ያደረገውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ዴስክ ኃላፊና ባለሙያዎች መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

በስልጠናው ከስድስቱ ዩኒቨርስቲ የተወጣጡ የግዥና ንብረት እንዲሁም የፋይናንስና በጀት አስተዳደር ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች፣ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊዎች፣ የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሌሎች የሚመለከተቸው አካላት ተሳታፊ መሆናቸውን ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማዕከልነት በምስራቁ የአገራችን ክፍል ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ የተለያዩ አመራሮች በመንግስት ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስናን መከላከል እና በሥነምግባራዊ አመራር ላይ ያተኮረ ስልጠና በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ዴስክ ኃላፊና ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት ተሰጥቷል፡፡

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከአምስት ዩኒቨርሲቲ ለተወጣጡ አመራሮች በተሰጠው ስልጠና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የቀብሪዳህር፣ የጅግጅጋ እና የሀረማያ እንዲሁም የኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ህጋዊ አገልግሎትን በህጋዊ መንገድ ይጠይቁ፥ ጉቦ አይክፈሉ!

***

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ለመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራር እና በግዥ ላይ የሚፈፀም ሙስና መከላከል ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተሰጠ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከስድስት አጎራባች ዩኒቨርሲቲ ለተውጣጡ አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራር እና በግዥ ላይ የሚፈፀም ሙስና መከላከል ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ተሰጥቷል።

በስልጠናው የተገኙት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ እንደተናገሩት ስልጠናው በሀገር ደረጃ በአራት ክላስተሮች ተከፋፍሎ በሀዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በአርባምንጭ እና በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ መሆኑን ገልፀው፥ ዓላማዉም በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በግዢ ላይ የሚፈፀም ሙስናን ለማስቀረት እንዲሁም ሙስናን መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሆኑን አመላክተዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ አክለውም ስልጠናው አስቸኳይ የሙስና መከላከል ስርዓትን፣ በግዢ ሂደት ላይ የሚፈፀም ሙስና እና የሙስና አጠራጣሪ ምልክቶችን እንዲሁም የመከላከያ ስልቶችን ያከተተ መሆኑን ጠቅሰው፥ በግዢ ስርዓቱ የሚፈፀም ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና ክፍተቶችንም ለመድፈን ይህን መሰል ስልጠና በመስጠት አቅምን ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሸን የስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ ኃይማኖት ገ/እግዚሔብር ስልጠናውን በሚሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት የስልጠናው ዓላማ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አርዓያነት ያላቸውን የአመራር ክህሎት በማጎልበት ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን የሚጠየፍ ዜጋን በማፍራት ረገድ የሚያደርጉትን አስተዋጾኦ ለማጎልበት መሆኑን ገልፀው፥ ኮሚሸኑ በ25 የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች ላይ ባደረገው ጥናት በግዥ ስርዓት አፈጻጸም ላይ ክፍተቶች መኖራቸው ተናግረዋል። ከነዚህም መካከል የትምህርት ሴክተር አንዱ መሆኑንና ድርጊቱን ለመከላከል ስልጠናው ማስፈለጉን አስረድተዋል።

ለሁለት ቀናት በተሰጠው ስልጠና በማዕከልነት የተመረጠውን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከዲላ፣ ከአርሲ፣ ከቡሌ ሆራ እና ከመደወላቡ እንዲሁም ከቦረና ዩኒቨርስቲ የተወጣጡ 78 የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንቶች፣ የፋይናንስ፣ የግዢና ንብረት አስተዳደር፣ የዉስጥ ኦዲት፣ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ዳይሬክተሮች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ዲኖች፣ የግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጆችና ከፋይናንስ፣ ግዢና ንብረት ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ስራ አስፈፃሚዎች መሳተፋቸዉን ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽኑ 20ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል አከባበር የዘርፎች የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከመሪ ስራ አስፈፃሚዎች እና ዴስክ ኃላፊዎች እንዲሁም ከ25 የዘርፍ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል አስፈፃሚዎች ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው።

*******
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ለገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራር እና ሰራተኞች ሥነ-ምግባር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራር እና ሰራተኞች ሥነ-ምግባር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ፈቃደ እንደገለፁት ሀገራችን ኢትዮጵያን በጽኑ የኢኮኖሚ መሰረት ላይ ለማቆም ተቋሙ የሚሰበስበው ገቢ ዋነኛ መሰረት መሆኑን አንስተው፥ ተግባራትን ስንሰራ በንጹህ ህሊና እና በንጹህ እጅ መሆን አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በአመራሩ እና በሰራተኛው አመለካከት ላይ በመስራት እና በማነቃቃት መልካም ሥነ-ምግባርን የተላበሰ አገልጋይን ማፍራት ተቋሙ መሰብሰብ ያለበትን ገቢ እንዲሰበስብ የሚያግዝ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የብሬክስሩ ትሬዲንግ አ.ማ ስራ አስኪያጅ እና ማህበረሰብ አንቂ አቶ ነፃነት ዘነበ እንደገለፁት ህይወትን በአዎንታዊ መልኩ እንዴት መቀየር ይቻላል? ቀና አስተሳሰብን መገንባት፣ አገልጋይነት እና ተጽኖ ፈጣሪነት እንዲሁም ስኬታማ ስራ እንዴት እንሰራለን? የሚሉት ሀሳቦች ላይ በማተኮር ለሚያጋጥሙን ችግሮች መፍትሄ በመሰጠት ሀገርን ታማኝ ሆኖ ማገልገል እና ስኬት ላይ አተኩሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑን መናገራቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡