ለመንግስት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተሰጠ
**
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለስድስት የመንግስት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው የተገኙት የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አህመድ ሙስጠፋ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት አመራሩ በሥነምግባር በመታነጽ በዩኒቨርስቲያቸው ውስጥ በግዥ ላይ የሚፈጸምን ሙስና የመከላከል አቅምን በማሳደግ ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የጸዳ የግዥ ስርዓት እንዲከተሉ ለማስቻል የተዘጋጀ ስልጠና በመሆኑ ሰልጣኞች ትኩረት አድርገው እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡
ስልጠናው በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ዴስክ ኃላፊና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፤ በሥነምግባራዊ አመራር እና በመንግስት ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስናን መከላከል ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለሁለት ቀናት የተሰጠው ሲሆን፤ ከጅማ፣ ጋምቤላ፣ ቦንጋ፣ መቱ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንቶች፣ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት፣ የፋይናንስ፣ የግዥ፣ የንብረት እና የቢዝነስና ገቢ ማመንጫ ስራ አስፈጻሚዎች፤ የውስጥ ኦዲት እና የተማሪዎች መሠረታዊ አገልግሎት እንዲሁም የግንባታ መሠረተ-ልማት ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ፓስፖርትና ቪዛ ለውጭ ዜጎች በመስጠትና ግለሰቦችን ወደ ውጭ በመላክ የሙስና ወንጀል ለተከሰሱ 38 ሰዎች የክስ ዝርዝር ደረሰ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ፓስፖርትና ቪዛ ለውጭ ሀገር ዜጎች በመስጠትና ሰነድ አልባ ግለሰቦችን ወደ ውጭ በመላክና በተያያዥ የሙስና ወንጀል ለተከሰሱ 38 ተከሳሾች የክስ ዝርዝር እንዲደርስ ተደረገ።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዘርፍ ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ረቡዕ የተከሳሾቹን የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ በ60 ግለሰቦች ላይ በየደረጃው 15 የሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወሳል።
በአጠቃላይ 60 ሺህ ገጽ የሰነድ ማስረጃዎችና የክስ ዝርዝሩ በፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር በኩል ተመሳክሮ ባለመጠናቀቁ ምክንያት ክስ ዝርዝሩንና የሰነድ ማስረጃውን ለመጠባበቅ ለዛሬ በተሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የደረሰውን የክስ ዝርዝርና የሰነድ ማስረጃዎችን ለቀረቡ ለ38 ተከሳሾች እንዲደርስ አድርጓል።
ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እንዲደርሳቸው ከተደረጉ 38 ተከሳሾች መካከል በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የምዝገባና ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታምሩ ግንበቶ አዋልሶ፣ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የውጪ ዜጎች ቁጥጥርና ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጅላሉ በድሩ ሰማ፣ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቡድን አስተባባሪ ከድር ሰዒድ ስሩር፣ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የኬላዎች ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ቦጋለ በዳዳ ይገኙበታል።
ሌሎች 22 ተከሳሾች ግን ችሎት ያልቀረቡ ሲሆን፥ ችሎት ካልቀረቡት መካከል ሁለቱ ቀደም ብሎ በምርመራ ላይ እያሉ በዋስ መፈታታቸውን ዐቃቤ ሕግ ለችሎቱ ገልጿል። ሌላ ችሎት ያልቀረበ አንድ ተከሳሽን በሚመለከት ደግሞ ከአሶሳ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሎ ዛሬ በአውሮፕላን እየመጣ መሆኑን አብራርቷል።
ፍርድ ቤቱ ክስ እንዲደርሳቸው የተደረጉ 38 ተከሳሾችን ማንነት የማረጋገጥ ስራ አከናውኗል።
በሌላ በኩል ዐቃቤ ሕግ 54ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰ ፈራኦል የተባለ ተከሳሽ ላይ ያቀረበው ክስ እንዲቋረጥለት ለችሎቱ አመልክቷል። የፍርድ ቤቱም በዐቃቤ ሕግ ጥያቄ መሰረት ክሱ እንዲቋረጥ አድርጓል።
በዚህ በተመሰረተባቸው ክስ ላይ የተመላከተባቸው ድንጋጌ ዋስትና መብት የማያስከለክል መሆኑን ተከትሎ የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት የኬላዎች ዘርፍ ቡድን መሪ የነበረው 5ኛ ተከሳሽ አይክፋው ጓሳዬ ገረመው እና አለሚቱ የኔ አየሁ የተባለች 49ኛ ተከሳሽን በሚመመከት በጠበቆች በኩል የዋስትና መብት ይፈቀድልን የሚል ጥያቄ ተነስቷል።
በዐቃቤ ሕግ በኩል ዋስትና ጥያቄ ላይ መቃወሚያ ያልቀረበ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱ 5ኛ ተከሳሽን በ20 ሺህ እና 49ኛ ተከሳሽን ደግሞ በ10 ሺህ ብር ዋስ አሲዘው ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የችሎቱ ዳኞች በአጠቃላይ የቀረበው ክስ ዝርዝር ዛሬ እንደደረሳቸው በመጥቀስ ክሱን ተመልከቶ በችሎት በንባብ ለማሰማት ለታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ያልቀረቡ ተከሳሾችን የፌደራል ፖሊስ በአድራሻቸው አፈላልጎ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብ መታዘዙን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
በሙስና ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች በጥቅም በመመሳጠር ከህግ ውጪ ጉቦ በዶላር እየተቀበሉ ለውጭ ዜጎች ከህግና አሰራር ውጪ ቪዛ በመስጠት፣ ሰነድ አልባ ዜጎችን በህገወጥ መንገድ ከሀገር በማስወጣት፣ መንግስት ላይ ጉዳት ማድረስ የሚሉ ነጥቦች በየተሳትፎ ደረጃ ተጠቅሶ በክስ ዝርዝሩ ተካቷል።

ለስድስት የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ተሰጠ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለስድስት ዩኒቨርሲቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው ከወልቂጤ፣ ከወራቤ፣ ከዋቸሞ፣ ከወላይታ ሶዶ፣ ከጂንካ እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ለተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለሁለት ቀናት በክላስተር መሰጠቱ ተገለጿል።
የሥልጠናው ዓላማ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በግዥ ላይ የሚፈጸመውን ሙስና የመከላከል አቅምን በማሳደግ ከሙስና እና ብልሹ አሠራር የጸዳ የግዥ ሥርዓት እንዲከተሉ ማስቻል ነው ተብሏል፡፡
በመንግስት ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስናን መከላከል እና በሥነምግባራዊ አመራር ላይ ትኩረት ያደረገውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ዴስክ ኃላፊና ባለሙያዎች መሰጠቱ ተገልጿል፡፡
በስልጠናው ከስድስቱ ዩኒቨርስቲ የተወጣጡ የግዥና ንብረት እንዲሁም የፋይናንስና በጀት አስተዳደር ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች፣ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊዎች፣ የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሌሎች የሚመለከተቸው አካላት ተሳታፊ መሆናቸውን ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማዕከልነት በምስራቁ የአገራችን ክፍል ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ የተለያዩ አመራሮች በመንግስት ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስናን መከላከል እና በሥነምግባራዊ አመራር ላይ ያተኮረ ስልጠና በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ዴስክ ኃላፊና ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት ተሰጥቷል፡፡
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከአምስት ዩኒቨርሲቲ ለተወጣጡ አመራሮች በተሰጠው ስልጠና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የቀብሪዳህር፣ የጅግጅጋ እና የሀረማያ እንዲሁም የኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡

ህጋዊ አገልግሎትን በህጋዊ መንገድ ይጠይቁ፥ ጉቦ አይክፈሉ!
***