Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
11.8K subscribers
11.5K photos
274 videos
32 files
3.3K links
Download Telegram
የሥነምግባር ግንባታንና የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ የተማሪዎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው - ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ

*****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም) የፌዴራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጆች ለሚገኙ ዕጩ ሥነምግባር አምባሳደር ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቋል።

በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ ዕጩ ሥነምግባር አምባሳደር ተማሪዎቹ በሥልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር በትምህርት ተቋማቸው የመልካም ሥነምግባር እሴቶችን በማስፋፋትና ሙስናን በመከላከል ንቁ ሚና መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ዕጩ አምባሳደሮቹ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በስም ብቻ ሳይወሰኑ በተግባር ማሳየት እንደሚገባቸው ያስገነዘቡት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ በተቋማቸው የሚከናወኑ የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ተግባራትን ከሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈጻሚዎች ጋር በመቀናጀት ከማቀድ እስከ መተግበርና መከታተል ድረስ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በተለይም በተማሪዎች መካከል የሚታዩ የሥነምግባር ጉድለቶችን በግልጽ ውይይት ለመፍታት፣ መልካም ተግባራትን ለማበረታታትና የእኩዮቻቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል።

የሚያነሷቸው ሐሳቦችና የሚያከናውኗቸው ተግባራት ቀጣይነትና ተጨባጭ ውጤት እንዲኖራቸው ዕጩ አምባሳደሮቹ ከተቋማቸው የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎች፣ ከመምህራንና ከሌሎች የተማሪ አደረጃጀቶች ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባቸውም አመላክተዋል።

በተጨማሪም የሚያጋጥሟቸውን ችግሮችና የሚያገኟቸውን ውጤቶች በመመዝገብ፣ ልምድ በመለዋወጥና ለችግሮች የመፍትሔ ሐሳቦችን በማቅረብ የዕጩ አምባሳደርነት ሚናቸውን ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የአቅም ግንባታ ሥልጠናው የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ያካተተ ሲሆን፣ በፀረ-ሙስና ሕጎችና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ማስተባበሪያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሐረጎት አብርሃ የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ስምምነትን፣ በዲጂታል የሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፈን በላይነህ የሙስና ወንጀል ሕጎችን እንዲሁም በፀረ-ሙስና ሕዝብ ግንዛቤ ማስተባበሪያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ እንዳልካቸው ለሊሳ(ፒ.ኤች.ዲ) የሥነምግባር አምባሳደር ተማሪዎች የአሠራር ፕሮቶኮል ላይ ሥልጠናዎችን ሰጥተዋል።

ዕጩ ሥነምግባር አምባሳደር ተማሪዎቹም በሥልጠናው በተነሱ ርዕሰ ጉዳዮችና ከተቋማቸው ተግባራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን፣ ሐሳቦችንና አስተያየቶችን አቅርበዋል።

በተለይም የሥነምግባር ክበባትን ማጠናከር፣ የተማሪዎችን ተሳትፎ ማሳደግ፣ ሙስናን መከላከልና የሚያጋጥሙ የሙስና ድርጊቶችን ማጋለጥ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ላነሷቸው ጥያቄዎች ምክትል ኮሚሽነሩና የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ውይይቱም ተማሪዎቹ በሥልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ ከተቋማቸው ተግባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲያያይዙና በቀጣይ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ተግዳሮቶች በጋራ እንዲመክሩ ዕድል ፈጥሯል።

በሥልጠናው መጠናቀቂያ ላይም ዕጩ ሥነምግባር አምባሳደር ተማሪዎቹ በሥነምግባር አርአያ ለመሆን፣ በትምህርት ተቋማቸው የመልካም ሥነምግባር ባህልን ለማስፋፋት፣ የሥነምግባር ክበባትን ለማጠናከር፣ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለመከላከልና ለማጋለጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ የአቋም መግለጫ አቅርበዋል።

የአቅም ግንባታ ሥልጠናው ተማሪዎቹ የሥነምግባር አምባሳደርነት ኃላፊነታቸውን በእውቀት፣ በክህሎትና በባለቤትነት እንዲወጡ ከማገዙም በላይ፣ በትምህርት ተቋማት ዘላቂ የሥነምግባር ባህል ለመገንባት የተማሪዎች ንቁ ተሳትፎ ያለውን ወሳኝ ሚና አጉልቶ አሳይቷል።

ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፣ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚ ጠቋሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚ ጠቋሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

በስልክ ቁጥር ለመጠቆም፦ 0953222299/55

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በኮሚሽኑ የሚዘጋጀው የጥቅምት ወር 2ኛ ዙር ዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ

*****

ሙሉ ዲጂታል ጋዜጣውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ 👇
https://drive.google.com/file/d/1KQ8AnXHr4NJwpIDJqy-aWT2QlivIjC9x/view?usp=drivesdk

ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፣ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚ ጠቋሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚ ጠቋሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

በስልክ ቁጥር ለመጠቆም፦ 0953222299/55

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡