Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.87K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ሀሳብ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮች በተለያዩ ዲስትሪክቶች ስልጠና ተሰጥቷል

*******************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ሀሳብ በአዳማ እና በአሰላ ዲስትሪክት እንዲሁም በዋናው መስሪያ ቤት ለሚሰሩ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮች የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናው ሙስና እና ብልሹ አሰራር በሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚያስከትለውን አስከፊ ጉዳት ለባንኩ መካከለኛ አመራሮች ግንዛቤ በማስጨበጥ ከተቋማቸው አልፈው ሀገራቸውን እንዲከላከሉ ለማስቻል ያለመ ነው።

በባንኩ ላይ የሚከሰቱ ሙስና እና የሙስና መከላከያ ስልቶች ላይ ትኩረት ያደረግው ስልጠና በዶ/ር በረከት ሰለሞን፣ በዶ/ር ይልቃል ሙሉአለም እና በዶ/ር እንድሪስ የባ እንዲሁም በዶ/ር ያሲን ሁሴን ለሁለት ቀናት ተሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ወደ ራሱ አካውንት ብር ሲያስተላልፍ የነበረ የባንክ ሠራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

*******************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ደቡበ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ዳሽን ባንክ ካሸር ላይ ሲሰራ የነበረ ሠራተኛ 3.2 ሚሊየን ብር ወደራሱ አካውንት ብር ሲያስተላልፍ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ በመጣራት ላይ መሆኑን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመቅደላ ወረዳ የዳሽን ባንክ ሠራተኛው መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሎች አካውንት ላይ 3 ሚልየን 200 ሺህ ብር ወደ ራሱ አካውንት ሲያስገባ የወረዳው ፖሊስ በደረሰው መረጃ መሠረት ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የምርመራ ውጤቱን ተከታትሎ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በወረዳ 2 በሰላምና ፀጥታ ኃላፊ የሚመራው የክትትል ቡድን በማደራጀት ከአያት እስከ ጣፎ አደባባይ ድረስ መንግስትና ህዝብ የሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለራስ ያልተገባ ጥቅም በማዋል መኪናዎችን በማስቆም ገንዘብ ሲቀበሉ የነበሩ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሠራተኞች ላይ እርምጃ ተወስዷል።

ይህንን ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፈንጅ የተያዙት ተጠርጣሪ ወንጀለኞች 1ኛ ዳኛቸው ጎንፋ ዋቅጅራ ባለሙያ፣ 2ኛ ዳዊት ፍቅሬ እና 3ኛ ይልቃል ጌጤ (ሹፌር) በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፥ ግለሰቦቹ በፈፀሙት ያልተገባ ወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319