በህገ-ወጥ ድርጊት ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ 65 ተጠርጣሪዎች ተያዙ
*******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አካባቢ በመሆን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ 65 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።
ከተጠርጣሪዎቹ በተጨማሪም በአጠቃላይ ሰባት በሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ ቤቶች መታሸጋቸውን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተጠርጣሪዎቹ በተለያየ የሕገ-ወጥ የድለላ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ፣ በተለያየ የማጭበርበርና የማታለል ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የኦን ላይን የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሞሉ መሆናቸው ተመላክቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር በቅንጅት ባደረጉት ልዩ ኦፕሬሽን መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

የሙስና ወንጀል ውስብስብ ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ስጋት ነው - ሌተናል ኮሎኔል ሺሻይ ተስፋሁን
*******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የመከላከያ ሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት "ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ለኢትዮጵያ መከለከያ መረጃ የሠራዊት አባላት እና ሲቪል ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የመከላከያ ሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት የሙስና መረጃ ትንተና ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ሺሻይ ተስፋሁን ሙስና በየትኛውም የስራ መስክ ላይ በስውር እና በረቀቀ መንገድ ሊፈፀም የሚችል ውስብስብ ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
ወንጀሉን ውስብስብ ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ የሙስና ወንጀል ሲፈፀም ጉዳቱ በቀጥታ በአንድ ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ አለማረፉ ነው፡፡
በዚህም ምክንያት ሁሉም ወንጀሉን በጋራ ለመከላከል ቸለልተኝነቱ እየበዛ በመምጣቱ፣ ወንጀሉ እየተስፋፋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ መረጃ ስልጠና ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ያሬድ ሰለሞን በበኩላቸው የሠራዊቱ ቁልፍ ተግባር የሀገርን ዳር-ድንበር በመጠበቅ የህዝቦቿን ሰላም በፅኑ መሰረት ላይ ማቆም ቢሆንም በየሚሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ባላማወቅ ለቀላልም ሆነ ለከባድ የሙስና ወንጀሎች ተጋላጭ እንዳይሆን ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው ሀገሩን በፍቅር የሚያገልግል እና በሥነምግባር የታነፀ ወታደር እንዲቀረፅ ሁሉም የተቋሙ አባል የራሱን ድርሻ እንዲወጣ በማደረግ በኩል የራሱን ሚና መጫዎት እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ሀሳብ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮች በተለያዩ ዲስትሪክቶች ስልጠና ተሰጥቷል
*******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ሀሳብ በአዳማ እና በአሰላ ዲስትሪክት እንዲሁም በዋናው መስሪያ ቤት ለሚሰሩ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮች የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው ሙስና እና ብልሹ አሰራር በሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚያስከትለውን አስከፊ ጉዳት ለባንኩ መካከለኛ አመራሮች ግንዛቤ በማስጨበጥ ከተቋማቸው አልፈው ሀገራቸውን እንዲከላከሉ ለማስቻል ያለመ ነው።
በባንኩ ላይ የሚከሰቱ ሙስና እና የሙስና መከላከያ ስልቶች ላይ ትኩረት ያደረግው ስልጠና በዶ/ር በረከት ሰለሞን፣ በዶ/ር ይልቃል ሙሉአለም እና በዶ/ር እንድሪስ የባ እንዲሁም በዶ/ር ያሲን ሁሴን ለሁለት ቀናት ተሰጥቷል።