ኮሚሽኑ በክልሉ በየደረጃው ለሚገኙ ለኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ስልጠና መስጠቱን ገለፀ
*******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከክልል ጀምሮ በየደረጃው ለሚገኙ ለክልሉ ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ስልጠና መስጠቱን ገልጿል፡፡
ከዚህ በፊት ሁለቱ ኮሚሽኖች በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ስምምነት ሰነድ የተፈራረሙ ሲሆን፣ ይህንን መነሻ በማድረግ ኮሚሽኖቹ በተናጠልና በጋራ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ዙሪያ ስልጠናው ትኩረት ተደርጎ ተሰጥቷል፡፡
በሥልጠናው የተገኙት የክልሉ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሳቤላ ፍቃድ በየደረጃው የሚገኘው አመራር ለአሠራር ግልፅነትና ተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ሀብትና ንብረቱን በማስመዝገብ ግንባር ቀደም እንዲሆንና ለሙስና መከላከል ስራው አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ወ/ሮ ሳቤላ አክለውም የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ለሥነምግባር መኮንኖች ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ የሀብት ማስመዝገብ ስራው በታሰበለት ልክ እንዲሄድ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ማሩ ቸኮል የስልጠና ሰነዱን በማቅረብ በጋራ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ ሰፋ ያለ ስልጠና ሰጥተዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት መንግስትና ፓርቲው በሚያዘጋጃው የትግል መስመሮች በመታገል ዜጎች በፀረ-ሙስና ትግሉ እንዲሳተፉ በማድረግ እና ሙስናን የሚጠየፍ ማህበረሰብ መፍጠር ይኖርብናል ሲሉ አቶ ማሩ በገለፃቸው ተናግረዋል።
በፓርቲው እና በመንግሥት የሚጠበቅን ሥነምግባር በመላበስና አርዓያ በመሆን፣ የህዝብና መንግስት ሀብት ለታለመለት አላማ እንዲውል በመከታተል ክልላዊ የፀረ-ሙስና ትግሉን መደገፍ እንደሚገባ ምክትል ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።
በመድረኩም ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል በየደረጃው የሚገኙ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ከሥነምግባር መኮንኖች ጋር በጋራ ውጤታማ ሥራ በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በስልጠናው ሁለቱም ኮሚሽኖች በቀጣይ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ግልፅነት መያዛቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በስልጠና መድረኩ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሀብታሙ ሞገስ፣ የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ አቶ እሱባለው መሰለ እና ጽ/ቤት ኃላፊዋ ወ/ሮ ሳቤላ ፍቃድ እንዲሁም ከክልል ጀምሮ በየደረጃዉ የሚገኙ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ተገኝተዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

በህገ-ወጥ ድርጊት ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ 65 ተጠርጣሪዎች ተያዙ
*******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አካባቢ በመሆን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ 65 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።
ከተጠርጣሪዎቹ በተጨማሪም በአጠቃላይ ሰባት በሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ ቤቶች መታሸጋቸውን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተጠርጣሪዎቹ በተለያየ የሕገ-ወጥ የድለላ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ፣ በተለያየ የማጭበርበርና የማታለል ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የኦን ላይን የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሞሉ መሆናቸው ተመላክቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር በቅንጅት ባደረጉት ልዩ ኦፕሬሽን መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሙስና ወንጀል ውስብስብ ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ስጋት ነው - ሌተናል ኮሎኔል ሺሻይ ተስፋሁን
*******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የመከላከያ ሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት "ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ለኢትዮጵያ መከለከያ መረጃ የሠራዊት አባላት እና ሲቪል ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የመከላከያ ሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት የሙስና መረጃ ትንተና ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ሺሻይ ተስፋሁን ሙስና በየትኛውም የስራ መስክ ላይ በስውር እና በረቀቀ መንገድ ሊፈፀም የሚችል ውስብስብ ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
ወንጀሉን ውስብስብ ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ የሙስና ወንጀል ሲፈፀም ጉዳቱ በቀጥታ በአንድ ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ አለማረፉ ነው፡፡
በዚህም ምክንያት ሁሉም ወንጀሉን በጋራ ለመከላከል ቸለልተኝነቱ እየበዛ በመምጣቱ፣ ወንጀሉ እየተስፋፋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ መረጃ ስልጠና ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ያሬድ ሰለሞን በበኩላቸው የሠራዊቱ ቁልፍ ተግባር የሀገርን ዳር-ድንበር በመጠበቅ የህዝቦቿን ሰላም በፅኑ መሰረት ላይ ማቆም ቢሆንም በየሚሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ባላማወቅ ለቀላልም ሆነ ለከባድ የሙስና ወንጀሎች ተጋላጭ እንዳይሆን ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው ሀገሩን በፍቅር የሚያገልግል እና በሥነምግባር የታነፀ ወታደር እንዲቀረፅ ሁሉም የተቋሙ አባል የራሱን ድርሻ እንዲወጣ በማደረግ በኩል የራሱን ሚና መጫዎት እንዳለበት ተገልጿል፡፡