ቀበሌ ላይ መዋቅርን በማጠናከር አገልጋይነትን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ
*********************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደር ሪፎርም ለመተግበር የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙ ጠቀሜታ እና አካሄድን በመረዳት ሥራውን መጀመር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በተመረጡ ተቋማት መጀመር እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል። በሪፎርሙ የየደረጃው ሲቪል ሰርቪስ ተቋም አርዓያ በመኾን መጀመር እንዳለበትም ገልጸዋል።
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመልካም አሥተዳደር ችግር ሥር የሰደደ መኾኑን ጠቅሰው፣ የመንግሥት ሪፎርምም ፈተናዎች እንደሚያጋጥሙት ገልጸዋል።
በክልልም ኾነ በሀገር ደረጃ ሕዝብ የሚጠብቀውን አገልግሎት እና የመልካም አሥተዳደር ማስፈን ሥራ ላይ ፈተና እያጋጠመ ነው ያሉት ዶክተር መኩሪያ፥ ይህም በጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል። መንግሥትም ችግሩን ተረድቶ ለመፍትሄው እየሠራ መኾኑን አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ከተቋቋመ 117 ዓመታት እንደኾነው የጠቀሱት ዶክተር መኩሪያ፣ እስካሁን ትልልቅ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰዋል። ነገር ግን ዓለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ አለመድረሱን ጠቁመዋል።
መንግሥት ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር በማስተካከል አገልግሎት አሰጣጥ እና ሕገ ወጥ የሰው ኃይል ሥምሪትን ለማስተካከል እንደሚሠራም ገልጸዋል።
በፌዴራል፣ ክልል፣ ዞን፣ ከተማ ወይም ወረዳ ላይ ብንኾንም ለሕዝባችን የሚመጥን ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት አገልግሎቱን እናሻሽላለን ሲሉ ተናግረዋል።
አማራ ክልል ወደ ኋላ እንዳይቀር በፌዴራል ደረጃ የሚካሄዱ የሪፎርም ሥራዎችን በመተግበር የለውጡ ተሳታፊ እና የውጤቱ ተጠቃሚ እንዲኾንም አደራ ብለዋል።
የክልሉ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) የመንግሥትን የመፈጸም አቅም በተቋማዊ ልህቀት ለመገንባት በመዘጋጀት እና በመተግበር አሁናዊ የመንግሥት አሥተዳደር እና አገልግሎት ቁመና ላይ መግባባት ይገባል ብለዋል።
የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጡ ገና ዜጎችን የሚያረካ ሥርዓት አለመገንባቱን ጠቅሰው፥ የአገልግሎት አሰጣጡም ጊዜው ያለፈበት መኾኑን ገልጸዋል። የቅሬታ ምንጭ የኾኑ የአገልግሎት ዘርፎችንም ለይቶ በቴክኖሎጂ በማገዝ ማሻሻል እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሲቪል ሰርቪሱ ሌብነትን እና ብልሹ አሠራርን የማይሸከም አድርጎ የመምራትን እና የሠራተኛውን ሥነምግባር የማሻሻልን አስፈላጊነት ዶክተር አብዱ ሁሴን አንስተዋል።
የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ብቁ የሰው ኃይል እጥረት ካጋጠመው ችግሮች ውስጥ መኾኑን ጠቅሰዋል። በመኾኑም የተቋማት ብቃት የሚለካው በሰዎች፣ በአሠራር እና በአደረጃጀት እንዲሁም በሥነምግባር እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም በመኾኑ የሰው ሃብትን ለማልማት ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።
ሲቪል ሰርቫንቱን ከልማት አኳያም የረጅም እና የአጭር ጊዜ ሥልጠና በመስጠት እና የሥነምግባር ግንባታ በማድረግ የአፈጻጸም ውጤታማነትን የሚያበረታቱ መስኮች ላይ ርብርብ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደር ነጻ እና ገለልተኛ ለማድረግም የብቁ ተቋማትን በመገንባት ነጻነት እና ገለልተኝነት እንደሚረጋገጥ ተናግረዋል።
የሙያ ምደባ፣ የሥራ ምዘና እና የክፍያ ሥርዓት አለመኖርን እና የተደራጀ የመረጃ ሥርዓት እጥረትን በመፍታት የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደርን ለማሻሻል የሲቪል ሰርቪሱ የሰው ሃብት ልማት ተቋሙን እንደሚደገፍ ገልጸዋል።
የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባንቻምላክ ገብረ ማርያም በበኩላቸው ሲቪል ሰርቪሱ በሥነምግባሩ የተመሰገነ፣ ለዜጎች ቀልጣፋ እና ፍትሐዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚተጋ እንዲኾን ተደርጎ መገንባት እንዳለበት መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ለሁሉም ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እየሠራ መኾኑንም ተናግረዋል። አገልግሎቶቹ ዲጂታላይዝድ እንዲኾኑም የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።
የመልካም አሥተዳደር ችግርን የሚፈታ የሪፎርም ሥራን በማሥተባበር እና የመንግሥት አሥተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ፖሊሲ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያዝበት መሪዎች ሠራተኞቻቸውን በአርኣያነት መምራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

መልካም የሥራ ሥነምግባር ያላቸው አመራሮችና ሠራተኞች ህዝባቸውን ተጠቃሚ ተቋማቸውን ፍሬያማ ያደርጋሉ!
***************
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
***************
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኮሚሽኑ በክልሉ በየደረጃው ለሚገኙ ለኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ስልጠና መስጠቱን ገለፀ
*******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከክልል ጀምሮ በየደረጃው ለሚገኙ ለክልሉ ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ስልጠና መስጠቱን ገልጿል፡፡
ከዚህ በፊት ሁለቱ ኮሚሽኖች በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ስምምነት ሰነድ የተፈራረሙ ሲሆን፣ ይህንን መነሻ በማድረግ ኮሚሽኖቹ በተናጠልና በጋራ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ዙሪያ ስልጠናው ትኩረት ተደርጎ ተሰጥቷል፡፡
በሥልጠናው የተገኙት የክልሉ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሳቤላ ፍቃድ በየደረጃው የሚገኘው አመራር ለአሠራር ግልፅነትና ተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ሀብትና ንብረቱን በማስመዝገብ ግንባር ቀደም እንዲሆንና ለሙስና መከላከል ስራው አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ወ/ሮ ሳቤላ አክለውም የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ለሥነምግባር መኮንኖች ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ የሀብት ማስመዝገብ ስራው በታሰበለት ልክ እንዲሄድ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ማሩ ቸኮል የስልጠና ሰነዱን በማቅረብ በጋራ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ ሰፋ ያለ ስልጠና ሰጥተዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት መንግስትና ፓርቲው በሚያዘጋጃው የትግል መስመሮች በመታገል ዜጎች በፀረ-ሙስና ትግሉ እንዲሳተፉ በማድረግ እና ሙስናን የሚጠየፍ ማህበረሰብ መፍጠር ይኖርብናል ሲሉ አቶ ማሩ በገለፃቸው ተናግረዋል።
በፓርቲው እና በመንግሥት የሚጠበቅን ሥነምግባር በመላበስና አርዓያ በመሆን፣ የህዝብና መንግስት ሀብት ለታለመለት አላማ እንዲውል በመከታተል ክልላዊ የፀረ-ሙስና ትግሉን መደገፍ እንደሚገባ ምክትል ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።
በመድረኩም ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል በየደረጃው የሚገኙ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ከሥነምግባር መኮንኖች ጋር በጋራ ውጤታማ ሥራ በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በስልጠናው ሁለቱም ኮሚሽኖች በቀጣይ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ግልፅነት መያዛቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በስልጠና መድረኩ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሀብታሙ ሞገስ፣ የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ አቶ እሱባለው መሰለ እና ጽ/ቤት ኃላፊዋ ወ/ሮ ሳቤላ ፍቃድ እንዲሁም ከክልል ጀምሮ በየደረጃዉ የሚገኙ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን አመራሮች ተገኝተዋል።

በህገ-ወጥ ድርጊት ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ 65 ተጠርጣሪዎች ተያዙ
*******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አካባቢ በመሆን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ 65 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።
ከተጠርጣሪዎቹ በተጨማሪም በአጠቃላይ ሰባት በሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ ቤቶች መታሸጋቸውን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተጠርጣሪዎቹ በተለያየ የሕገ-ወጥ የድለላ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ፣ በተለያየ የማጭበርበርና የማታለል ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የኦን ላይን የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሞሉ መሆናቸው ተመላክቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር በቅንጅት ባደረጉት ልዩ ኦፕሬሽን መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሙስና ወንጀል ውስብስብ ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ስጋት ነው - ሌተናል ኮሎኔል ሺሻይ ተስፋሁን
*******************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የመከላከያ ሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት "ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ለኢትዮጵያ መከለከያ መረጃ የሠራዊት አባላት እና ሲቪል ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የመከላከያ ሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት የሙስና መረጃ ትንተና ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ሺሻይ ተስፋሁን ሙስና በየትኛውም የስራ መስክ ላይ በስውር እና በረቀቀ መንገድ ሊፈፀም የሚችል ውስብስብ ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
ወንጀሉን ውስብስብ ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ የሙስና ወንጀል ሲፈፀም ጉዳቱ በቀጥታ በአንድ ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ አለማረፉ ነው፡፡
በዚህም ምክንያት ሁሉም ወንጀሉን በጋራ ለመከላከል ቸለልተኝነቱ እየበዛ በመምጣቱ፣ ወንጀሉ እየተስፋፋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ መረጃ ስልጠና ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ያሬድ ሰለሞን በበኩላቸው የሠራዊቱ ቁልፍ ተግባር የሀገርን ዳር-ድንበር በመጠበቅ የህዝቦቿን ሰላም በፅኑ መሰረት ላይ ማቆም ቢሆንም በየሚሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ባላማወቅ ለቀላልም ሆነ ለከባድ የሙስና ወንጀሎች ተጋላጭ እንዳይሆን ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው ሀገሩን በፍቅር የሚያገልግል እና በሥነምግባር የታነፀ ወታደር እንዲቀረፅ ሁሉም የተቋሙ አባል የራሱን ድርሻ እንዲወጣ በማደረግ በኩል የራሱን ሚና መጫዎት እንዳለበት ተገልጿል፡፡