በ26 ዘርፎች ላይ የተጀመሩ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን - ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው
********
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም አዳማ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በዘርፎች የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም እና በኮሚሽኑ በሁሉም ዘርፎች ላይ በተደረገ የሱፐርቪዥን ሪፖርትና ግብረ-መልስ ላይ የግምገማ መድረክ አካሄዷል።
በመድረኩ የተገኙት በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው በ26 ዘርፎች ላይ የተጀመሩ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል በተቋማት ላይ ያሉ የውስጥ ኦዲት፣ ህግ አገልግሎት፣ ተቋማዊ ለውጥ እና የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
በቀጣይም ለህብረተሰቡ እሮሮ የሆኑ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሠራሮችን መከላከል ላይ በማተኮር እንሰራለን ብለዋል።
የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ከተቋማት አመራሮች ጋር ያላችሁን ግንኙነት፣ ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራዎችን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በቀጣይ የሱፐርቪዥን ሥራን አንዱ ዘርፍ ሌላውን የሚያይበት አሠራርን በመከተል እርስ በርዕስ ልምድ የምትለዋወጡበትና አቅም የምትገነባቡበት ይሆናል ብለዋል።
የተጀመረውን ዘርፍ ተኮር የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥልጠናውን አጠናክረን በማስቀጠል ሁሉንም ዘርፎች ተደራሽ እንደሚሆን ተናግረዋል።
በመድረኩ የዘርፎች የ6 ወር የሥራ አፈፃፀም እና በኮሚሽኑ በሁሉም ዘርፎች ላይ የተደረገው የሱፐርቪዥን ሪፖርትና ግብረ-መልስ ቀርቦ ግምገማ ተካሄዶበታል።
በሌላ መድረክም በተቋማት በአዲስ ለተመደቡ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳሬክተሮች እና ባለሙያዎች የሥራ ማስጀመሪያ ስልጠና፣ ብሔራዊ የሙስና መቀበያ መተግበሪያ ላይ እንዲሁም በዲጂታል የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ሥርዓት (EARS) ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ወድቆ ያገኘውን 26 ሺህ ብር የመለሰው የኮሚሽኑ ባለሙያ ምስጋና ተቸረው
********
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻንጉል ጉሙዝ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል ከሶስት ጓደኞቹ ጋር መንገድ ላይ ሲንቀሳቀስ ወድቆ ያገኘውን 26,000 ( ሃያ ስድስት ሺህ) ብር ለባለቤቱ በመመለሱ ምስጋና ተችሮታል።
አቶ አወቀ 26 ሺህ ብሩን ከሶስት የሥራ ባልደረቦቹ ጋር በመንገድ ሲንቀሳቀስ ቀድሞ በማየትና በማንሳት ለጓደኞቹ ብር እንዳገኘ ይናገራል፥ ጓደኞቹ ግን አላመኑም፤ ነገር ግን በሚያምነው ኃይማኖት ሲምልላቸው ለማመን ተገደዋል።
የተገኘውም ብር ተቆጥሮ መጠኑ ታወቀ፥ የብሩ ባለቤትም አድራሻ ተገኘና ተደውሎ ቦታው ድረስ በመምጣት 26 ሺህ ብር እንደጠፋበት ተናገረ፤ ብሩ በላቡ ያፈራው መሆኑ በመረጋገጡ በምስክር ፊት ገንዘቡ ሊሰጠው ችሏል፡፡ በምላሹም ምስጋናቸውን ለአቶ አወቀ ችረዋል፡፡
አቶ አወቀ በየመድረኩ የሚያስተምሩትን የሥነምግባር ስልጠና እና የብልሹ አሰራር አፀያፊነት በተግባር በማሳየታቸው ለሌሎች ያስተምራል በሚል ኮሚሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገፁ መረጃውን አጋርቷል።

አሜሪካ በቀድሞ የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት “ከፍተኛ የሙስና ወንጀል” ውንጀላ ተከትሎ የጉዞ እገዳ መጣሏን ገለፀች
********
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞ የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት ክሪስቲና ፈርናንዴዝ በቢሮ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ "በከፍተኛ ሙስና" ውስጥ ተሳትፋለች በሚል ክስ ምክኒያት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ከልክሏቸዋል።
የአርጀንቲና የቀድሞ ፕሬዚዳንት የሆኑት ክሪስቲና ኤሊሳቤት ፈርናንዴዝ ዴ ኪርችነር ('CFK') እና የአርጀንቲና የቀድሞ የፕላን ሚኒስትር ጁሊዮ ሚጌል ዴ ቪዶ ('ዴ ቪዶ') እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ጭምር የጉዞ እገዳ የተጣለባቸው መሆኑ ተመላክቷል።
ኪርችነር እና ዴ ቪዶ "የሕዝብ ሥራ ኮንትራቶችን የሚያካትቱ በርካታ የጉቦ ስልቶችን በማደራጀት እና በገንዘብ ጥቅም በማግኘት ቦታቸውን አላግባብ በመጠቀም ከአርጀንቲና መንግስት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ተዘርፏል" ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
የተለያዩ ፍርድ ቤቶች ጥንዶቹን በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው የፈረደባቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።
"ዩናይትድ ስቴትስ የህዝብን ስልጣን ለግል ጥቅማቸው ለሚጠቀሙ ግለሰቦችን ተጠያቂነትን ማራመዷን ትቀጥላለች" ሲል ሩቢዮ ተናግሯል። "እነዚህ ውሳኔዎች ከፍተኛ የመንግስት እርከኖችን ጨምሮ ዓለምአቀፍ ሙስናን ለመከላከል ያለንን ቁርጠኝነት ያረጋግጣሉ" ብለዋል።
በኖቬምበር ላይ የአርጀንቲና ፍርድ ቤት በፈርናንዴዝ ላይ የስድስት አመት እስራት እና የእድሜ ልክ እገዳን ማፅናቱ አስታውሶ ኤንቢሲ ኒውስ ዘግቧል።
የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት በስልጣን ዘመናቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በህዝብ ስራ ፕሮጀክቶች በመመዝበር በ2022 በሶስት ዳኞች ተከሰው ተፈርዶባቸዋል። ይግባኝ ቢጠይቁም ከፍተኛው ፍርድ ቤት የመጀመሪያውን ብይን ማፅናቱ ተገልጿል።
ፈርናንዴዝ ሁሉንም ክሶች ውድቅ በማድረግ እስር ቤት የወጡ ሲሆን፥ በደቡብ አሜሪካ አገር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዋና የፖለቲካ መሪ መሆናቸው ተመላክቷል።