Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ሁለቱ ኮሚሽኖች በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ጋር በአመራርና በአባላት ውስጥ ሥነምግባር ለማስረጽና ሙስናን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱን የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ሰብሳቢ እና የኢፌድሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ፣ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ፣ የክልሉ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል በተገኙበት ተፈርሟል።

ስምምነቱ በዘመናዊ መንገድ ጥናቶችን በማጥናት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲሁም ቀልጣፋና ፍትሃዊ ከሙስና የጸዳ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማድረስ መሰረት የሚጥል መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም የፓርቲው አመራሮችና አባላት የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ተልዕኮ በብቃት እንዲወጡ፣ በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ የተሻለ አቅም እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተመላክቷል።

በፓርቲው አመራሮችና አባላት መካከል በሥነምግባር፣ በአቅም ግንባታ፣ በሙስና መከላከል እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ለመለዋወጥና ጥናቶችን ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነቱ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው መገለፁን ከክልሉ የብልፅግና ፓርቲ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በኦሮሚያ ክልል በሙስና የተገኘ ሀብትን ከማስመለስ አንጻር ውጤታማ ስራ ተከናውኗል

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኦሮሚያ ክልል በሙስና የተገኘ ሀብት በማስመለስ እና የወንጀሉ ተሳታፊዎችን ተጠያቂ ከማድረግ አንጻር ውጤታማ ስራ መከናወኑን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለፀ።

የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ፥ በክልሉ በሙስና የተገኘ ሀብትን ከማስመለስና ወንጀለኞችን ተጠያቂ ከማድረግ አንጻር በተከናወኑ ስራዎች ላይ ያተኮረ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፥ በክልሉ በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት የተመዘበረ የመንግስት፣ የልማት ድርጅቶች እና የህዝብ ሀብት ለማስመለስ በኩል ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

በዚህም ባለፉት 9 ወራት 1 ሺህ 197 የሙስና ወንጀል ምርመራ መደረጉን ተናግረው፥ ምርመራ ከተደረገባቸው መዝገቦች ውስጥም 1 ሺህ 163 መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ውሳኔ በተሰጠባቸው የተለያዩ መዝገብ ተከሳሾችም ከአንድ አመት እስከ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ የተደረገ ሲሆን፥ በገንዘብም ከ2 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደተጣላባቸው ተናግረዋል።

የሙስና ወንጀሎቹ በዋናነት ከመሬት አስተዳደር፣ ከማዕድን ፍለጋና ማውጣት ስራዎች እንዲሁም ከመንግስት ግዥና ክፍያ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የተፈፀሙ ናቸው ብለዋል።

የሙስና ወንጀል ውጤት እንደሆኑ የተጠረጠሩ በርካታ ንብረቶች ታግደው ምርመራ ሲደረግባቸው መቆየቱን ጠቅሰው፥ በሙስና ወንጀል የተገኘውን ሀብት ከማስመለስ አንጻርም 1 ቢሊዮን 157 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሃብት ተመላሽ መደረጉን አቶ ጉዮ ዋረዮ አስታወቋል።

ከዚህም ባለፈ ከ1 ቢሊዮን 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ንብረቶች ታግደው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም አስረድተዋል።

የሙስና ወንጀል ለመከላከል በሚደረገው ስራ የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፥ ህብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲያግዝ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኮሚሽኑ ለአዲስ አበባ ትራፊክ ፓሊስ አመራርና አባላት በተለያየ ዙር ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ማጠናቀቁን አስታወቀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለከተማው ትራፊክ ፓሊስ አመራርና አባላት በሙያዊ ሥነምግባር፣ በብልሹ አሰራር ተጋላጭነት እና በሙስና መከላከል ዙሪያ በተለያየ ዙር ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ማጠናቀቁን አስታወቀ።

በስልጠና ማጠቃለያ የተገኙት የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር መቅደስ ተስፋዬ በተለያዩ ዙር በከተማችን የሚገኙ ሁሉንም የትራፊክ ፓሊስ አመራርና አባላት በስልጠናው እንዲሳተፉ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

ስልጠናው የተሻለ አቅም የሚፈጥርና ህብረተሰባችሁን ሥነምግባር በተላበሰ መልኩ እንድታገለግሉ የሚረዳ እንደሆነ አስባለሁ ብለዋል።

ም/ኮሚሽነሯ አያይዘውም ተቋማችን በቀጣይ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ትራፊክ መምሪያ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በስልጠናው የተሳተፉ አባላት በተግባር ስራዎቻቸው ላይ ተጨባጭ ለውጦችን አምጥቷል ወይስ አላመጣም የሚለው ዳሰሳ የሚደረግበት መሆኑንም አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ፓሊስ መምሪያ የቀጠና 4 ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ትዕግስት ኃይሉ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በተለያየ ዙር ለአባላቶቻችን የሥራ ላይ ሥነምግባርና ብልሹ አሰራርን መከላከል ላይ ስልጠና መስጠት በመቻሉ ምስጋና አቅርበው አባሎቻችን በቀጣይ ወደ መደበኛ ስራዎቻችን ስንመለስ ከስልጠናውን ያገኘነውን እውቀትና ተሞክሮ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ስልጠና ዳ/ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት እንደገለፁት የትራፊክ ፖሊስ አባላት ሙያዊ ሥነምግባር ተላብሰው፤ ከብልሹ አሰራር ፀድተው ተግባራትን ማከናወናቸው በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የሚደርስ አደጋ እንዲቀንስ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

አክለውም አባላቱ በሙያ ሥነምግባር መታነፃቸው የሙያውን ቅቡልነት ከፍ በማድረግ አዎንታዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን በመድረኩ ማመላከታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሰልጣኝ የትራፊክ ፓሊሶች በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና ለስራቸው የተሻለ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ገልፀው፥ በቀጣይ በስራዎቻችን ላይ የሚስተዋሉ ትናንሽ ክፍተቶችን በማረም ተግባር ላይ ለማዋል እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ባንካችን አዲስ እንደመሆኑ መጠን የብልሹ አሠራር ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት በእንጭጩ ሊቀጩ ይገባል - አቶ ታደሰ ሐጥያ

********

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ‘‘ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል መሪ ሀሳብ ለሲዳማ ባንክ አመራሮች ለሁለት ቀናት የሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በሥልጠናው የተገኙት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሐጥያ ሙስና በአገራችን ሁለንተናዊ እድገት ላይ ፀር ነው። ባንኮች ላይ ሲፈጸም ደግሞ ልንታገለው ይገባል፥ ጸያፍም ተግባር ነው ብለዋል።

አቶ ታደሰ ሐጥያ አክለውም ባንካችን አዲስ እንደመሆኑ መጠን የብልሹ አሠራር ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት በእንጭጩ ሊቀጩ ይገባል ብለዋል።

በባንኩ ላይ የሚከሰቱ ሙስና እና የሙስና መከላከያ ስልቶች ላይ ትኩረት ያደረግው ስልጠና በዶ/ር ምረተዓብ አብርሃም ተሰጥቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319