የትውልድ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራን ውጤታማ ለማድረግ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ግንባር ቀደም ተዋናዮች ናቸው - ም/ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም አዳማ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በዘርፎች የ6 ወር የሥራ አፈፃፀም እና በኮሚሽኑ በ26 ዘርፎች ላይ በተደረገ የሱፐርቪዥን ሪፖርትና ግብረ-መልስ ላይ ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ መክፈቻ ላይ የተገኙት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ የትውልድ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራን ውጤታማ ለማድረግ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ግንባር ቀደም ተዋናዮች ናቸው ብለዋል።
በየተቋማት ያሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች በርካታ ተግባራት እየሰሩ ቢሆንም ውጤታማና ስኬታማ ሥራ ሰርተዋል ማለት አይቻልም።
ስለሆነም በቀጣይ ቀሪ ወራት በሥነምግባር ግንባታ ስልጠና እና ሙስና መከላከል እንዲሁም የሙስና ተጋላጭነት ጥናትና መረጃ ልውውጥ ሥራን በቅንጅት የምንሰራ ይሆናል ብለዋል።
በተለይ የዘርፍ ፎረሙን በማጠናከር ተግባራትን በጋራ እንደሚሰራ ጠቁመው፥ ዛሬን ጨምሮ ለቀጣይ ሶስት ቀናት ውጤታማ የውይይትና ስልጠና ጊዜ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
በግምገማ መድረኩ የኮሚሽኑ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የዘርፎች የሥነምግባር ግንባታና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚዎች እየተሳተፋ ይገኛል።
በሌላ መድረክም ለአዳዲስ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳሬክተሮች እና ባለሙያዎች የሥራ ማስጀመሪያ ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን፥ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት በሚኖረው ቆይታ በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዲጂታል ሥርዓት ላይ ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ኮሚሽኑ "ለወጣቶች ሥነምግባር ግንባታ የሚዲያ ሚና" በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ ማካሄዱን ገለፀ
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን "ለወጣቶች ሥነምግባር ግንባታ የሚዲያ ሚና" በሚል ርዕስ የሚዲያ ፎረም የጋራ መድረክ በይርጋለም ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ በመልካም ሥነምግባር የታነፀ ወጣት ለሀገርና ለዴሞክራሲ ግንባታ ሚናዉ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚዲያዎች ወጣቱን በሥነምግባር የማነጽ ሥራ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።
የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ኤልያስ በበኩላቸው ለአንድ ሀገር እድገት፣ ልማትና ለውጥ ጠንካራ ሚዲያ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀው፥ ለዚሁም ከሚዲያዎች ብዙ ስራ ይጠበቃል ብለዋል።
ሚዲያዎች የእውቀት ልውውጥ የሚደረግበት ድልድይ ነው ያሉት አቶ አሸናፊ፥ የትውልድ ሥነምግባር ላይ ግንዛቤ ከመፍጠርና በቂ መረጃ እንዲደርስ ከማድረግ አኳያ ተግባራት መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በፎረሙ አሸናፊ ኤልያስን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የሚዲያ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች መገኘታቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።