Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የግብር ተመን ቀንሰን እንገምትላችኋለን በማለት ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ የተቀበሉ ሁለት የግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የግብር ተመን ቀንሰን እንገምትላችኋለን በማለት ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ የተቀበሉ ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተጠርጣሪ ሠራተኞችና ገንዘቡን ከንግዱ ማህበረሰብ ሲያሰባስቡ የነበሩ አምስት ተጠርጣሪ ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ሲዳሞ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኙ አሮጌ ዕቃ እየገዙ ከሚሸጡ ነጋዴዎች፤ ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞች ነጋዴዎቹን በማነጋገር ለመንግስት የምትከፍሉትን የግብር የዋጋ ተመን ቀንሰን እንሰራላችኋለን ይሏቸዋል።

ይህንንም ለማስፈጸም እናንተ በአምስት ሰዎች አስተባባሪነት ከእያንዳንዱ ነጋዴ ብር አሰባስባችሁ የድርሻችንን ስጡን በማለት ከ89 ነጋዴዎች ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ ሰብስበዋል።

የዚህን ድርጊት መፈጸም ከህብረተሰቡ መረጃ የደረሰው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሁለቱን የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞችና አምስቱን ነጋዴዎች መጋቢት 9/2017 ዓ.ም ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።

ህጋዊነት የጎደለውን አካሄድ በመከተል ከመንግስት አሰራር ውጪ የንግዱን ማህበረሰብ በማሳሳት ባልተፈለገ አግባብ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙና የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሀገርን እና ህዝብን ለጉዳት የሚዳርጉ መሰል አካላት ሲገጥሙ የንግዱ ማህበረሰብም የጀመረውን ወንጀለኛን የማጋለጥ አበረታች ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል ህጋዊ አሰራርን ሊከተል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319