Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመንና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እየተሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

*********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመንና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 21ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በሚመለከት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በምላሻቸውም የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመንና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ሁለት ዋና ዋና ስራዎች መከናወን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

አንደኛው በቀበሌ ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ሲሆን፤ እያንዳንዱ ቀበሌ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅሞችን መገንባት መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ሁሉም ቀበሌዎች ያላቸውን ሃብት በቁጥር ለይተው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው። ይህ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ሁለተኛው መሶብ የተሰኘ አገልግሎት ሲሆን፣ በሙከራ ደረጃ በሲቪል ሰርቪስና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሲስተም ይጀመራል ሲሉም ገልጸዋል።

አገልግሎቱም በአንድ መስኮት ሁሉንም አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ አሰራር ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ተቋሙ የተጣለበትን ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በሥነምግባር የተገነባ ሠራተኛ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለገቢዎች ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች በሦስት ዙሮች በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በዚሁ መድረክ የገቢዎች ሚኒስቴር የሚንስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ታደሰ የገቢውን ዘርፍ ለማጠናከርና ተቋሙ የተጣለበትን ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በሥነምግባር የተገነባ ሠራተኛ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ይህን መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተቋማዊ ስጋት እና ሥራ አመራር ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ደስታ በበኩላቸው ሙስና የሀገርን ኢኮኖሚ ወደ ኋላ ከሚጎትቱ ጉዳዮች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የገቢው ዘርፍ ትልቁ የሀገሪቱ የትራንስፎርሜሽን አካል ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፥ በዚህ ዘርፍ የሚከናወኑ ማናቸውም አገልግሎቶች ከሙስና የጸዱ መሆን እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡

በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ሠልጣኞችም በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና ተገቢ እና በቂ እውቀት ያገኙበት በመሆኑ በቀጣይም መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ከሚሽን ዋና መ/ቤቶች አመራሮች እና ሠራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የግብር ተመን ቀንሰን እንገምትላችኋለን በማለት ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ የተቀበሉ ሁለት የግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የግብር ተመን ቀንሰን እንገምትላችኋለን በማለት ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ የተቀበሉ ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተጠርጣሪ ሠራተኞችና ገንዘቡን ከንግዱ ማህበረሰብ ሲያሰባስቡ የነበሩ አምስት ተጠርጣሪ ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ሲዳሞ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኙ አሮጌ ዕቃ እየገዙ ከሚሸጡ ነጋዴዎች፤ ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞች ነጋዴዎቹን በማነጋገር ለመንግስት የምትከፍሉትን የግብር የዋጋ ተመን ቀንሰን እንሰራላችኋለን ይሏቸዋል።

ይህንንም ለማስፈጸም እናንተ በአምስት ሰዎች አስተባባሪነት ከእያንዳንዱ ነጋዴ ብር አሰባስባችሁ የድርሻችንን ስጡን በማለት ከ89 ነጋዴዎች ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ ሰብስበዋል።

የዚህን ድርጊት መፈጸም ከህብረተሰቡ መረጃ የደረሰው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሁለቱን የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞችና አምስቱን ነጋዴዎች መጋቢት 9/2017 ዓ.ም ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።

ህጋዊነት የጎደለውን አካሄድ በመከተል ከመንግስት አሰራር ውጪ የንግዱን ማህበረሰብ በማሳሳት ባልተፈለገ አግባብ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙና የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሀገርን እና ህዝብን ለጉዳት የሚዳርጉ መሰል አካላት ሲገጥሙ የንግዱ ማህበረሰብም የጀመረውን ወንጀለኛን የማጋለጥ አበረታች ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል ህጋዊ አሰራርን ሊከተል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319