Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል

*********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በሚመለከት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

👉 ሙስና እና ብልሹ አሠራር እያደረሰ ያለውን ሀገራዊ ጉዳት ለመቀነስ ምን እየተሠራ ነው?

👉 የፍትሕ ተደራሽነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት መንግሥት በቀጣይ ምን ለመስራት አስቧል?

👉 በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂት ለመፍታት በቀጣይ የሚቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?

👉 መንግሥት በድጎማ የሚያቀርበው ነዳጅ በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳይሸጥ ምን አይነት ጠንካራ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?

👉 የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር መንግሥት ምን እየሠራ ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስናን ለመከላከል የምክርቤት አባላት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

*********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስናን ለመከላከል የምክርቤት አባላት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ገልጿል፡፡

የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል በሙስና ፅንስ ሀሳብ ዙሪያ ለወረዳው የምክር ቤት አባላት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የወረዳው የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ ወ/ሮ ሰናይት ግርማው ሙስና ሀገራችንን በከፍተኛ ደረጃ የሚጓዳ፣ የሀገር እድገት እና የዜጓችን የወደፊት እጣ ፍንታ ወደ ኋላ የሚያስቀር መሆኑን ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሰናይት አክለውም ሙስናን ለመከላከል የምክርቤት አባላት ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ከስልጠናው ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ውይይት መደረጉን ከወረዳው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመንና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እየተሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

*********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመንና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 21ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በሚመለከት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በምላሻቸውም የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመንና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ሁለት ዋና ዋና ስራዎች መከናወን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

አንደኛው በቀበሌ ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ሲሆን፤ እያንዳንዱ ቀበሌ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅሞችን መገንባት መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ሁሉም ቀበሌዎች ያላቸውን ሃብት በቁጥር ለይተው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው። ይህ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ሁለተኛው መሶብ የተሰኘ አገልግሎት ሲሆን፣ በሙከራ ደረጃ በሲቪል ሰርቪስና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሲስተም ይጀመራል ሲሉም ገልጸዋል።

አገልግሎቱም በአንድ መስኮት ሁሉንም አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ አሰራር ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ተቋሙ የተጣለበትን ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በሥነምግባር የተገነባ ሠራተኛ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለገቢዎች ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች በሦስት ዙሮች በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በዚሁ መድረክ የገቢዎች ሚኒስቴር የሚንስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ታደሰ የገቢውን ዘርፍ ለማጠናከርና ተቋሙ የተጣለበትን ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በሥነምግባር የተገነባ ሠራተኛ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ይህን መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተቋማዊ ስጋት እና ሥራ አመራር ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ደስታ በበኩላቸው ሙስና የሀገርን ኢኮኖሚ ወደ ኋላ ከሚጎትቱ ጉዳዮች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የገቢው ዘርፍ ትልቁ የሀገሪቱ የትራንስፎርሜሽን አካል ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፥ በዚህ ዘርፍ የሚከናወኑ ማናቸውም አገልግሎቶች ከሙስና የጸዱ መሆን እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡

በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ሠልጣኞችም በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና ተገቢ እና በቂ እውቀት ያገኙበት በመሆኑ በቀጣይም መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ከሚሽን ዋና መ/ቤቶች አመራሮች እና ሠራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319