Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ተቋማዊ አቅምን በማጠናከር ዘላቂ የሆነ የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ለመፍታት ከወዲሁ በትጋት መስራት ይጠበቃል - አቶ ፍቅሬ አማን

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ማዕከል ያደረገ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሄዷል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን የፓርቲያችን ብልጽግና ቀይ መስመር የሆኑትን ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን አምርሮ መታገልን ወቅቱ ይጠይቃል ብለዋል።

የህዝብ ፍላጎቶት፣ ስሜትና ጥያቄዎችን በተገቢው ለመረዳት የሚያግዙ ስልቶችን በመጠቀም የልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎችን ለማሳለጥ መትጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አመራሩ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት በማጎልበት በመልካም አስተዳድር ጉዳዮች ላይ የሚስተዋለውን ችግር በመቅረፍ ፈጣንና ጥራት ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

እያጋጠሙ ያሉትን ብልሹ አሰራሮችን የተደራጀ ብርቱ ትግል እንደሚደረግና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፥ 7/24 ሰዓት በመስራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተናበበ መልኩ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንዳሉት አመራሩ አገልጋይ ተኮር እሳቤን በመላበስ ለህዝብ የገባነውን ቃል በፍትሃዊነትና በታማኝነት ማገልገል መቻል አለብን ብለዋል።

ሌብነትና ብልሹ አሰራር ለጠንካራ ፓርቲ፣ መንግስትና ሀገር ግንባታ እንቅፋት በመሆናቸው ችግሩን በማጤን፣ በመመርመርና በጥልቀት በማየት ከምንጩ ለማድረቅ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ አብራርተዋል።

በመድረኩ የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳድር ሳንካ በሆኑትና በመንግስት ተቋማት የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ በፍትህ ስርዓት የሚስተዋሉ ጉድለቶች፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮች እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ከችግሮች መሻገር በሚያስችል መልኩ ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ በቀጣይ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን የተላበሰ የአሰራር ስርዓትን በመከተል የህዝቡን የመልካም አስተዳድርና ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ ብሎም በተናበበ መልኩ ለመስራት እንደሚያስችል መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል

*********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በሚመለከት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

👉 ሙስና እና ብልሹ አሠራር እያደረሰ ያለውን ሀገራዊ ጉዳት ለመቀነስ ምን እየተሠራ ነው?

👉 የፍትሕ ተደራሽነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት መንግሥት በቀጣይ ምን ለመስራት አስቧል?

👉 በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂት ለመፍታት በቀጣይ የሚቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?

👉 መንግሥት በድጎማ የሚያቀርበው ነዳጅ በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳይሸጥ ምን አይነት ጠንካራ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?

👉 የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር መንግሥት ምን እየሠራ ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስናን ለመከላከል የምክርቤት አባላት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

*********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስናን ለመከላከል የምክርቤት አባላት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ገልጿል፡፡

የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል በሙስና ፅንስ ሀሳብ ዙሪያ ለወረዳው የምክር ቤት አባላት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የወረዳው የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ ወ/ሮ ሰናይት ግርማው ሙስና ሀገራችንን በከፍተኛ ደረጃ የሚጓዳ፣ የሀገር እድገት እና የዜጓችን የወደፊት እጣ ፍንታ ወደ ኋላ የሚያስቀር መሆኑን ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሰናይት አክለውም ሙስናን ለመከላከል የምክርቤት አባላት ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ከስልጠናው ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ውይይት መደረጉን ከወረዳው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመንና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እየተሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

*********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመንና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 21ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በሚመለከት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በምላሻቸውም የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመንና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ሁለት ዋና ዋና ስራዎች መከናወን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

አንደኛው በቀበሌ ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ሲሆን፤ እያንዳንዱ ቀበሌ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅሞችን መገንባት መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ሁሉም ቀበሌዎች ያላቸውን ሃብት በቁጥር ለይተው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው። ይህ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ሁለተኛው መሶብ የተሰኘ አገልግሎት ሲሆን፣ በሙከራ ደረጃ በሲቪል ሰርቪስና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሲስተም ይጀመራል ሲሉም ገልጸዋል።

አገልግሎቱም በአንድ መስኮት ሁሉንም አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ አሰራር ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319