Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የንብረት ማስመለስ አዋጁ አስፈላጊነት እና ይዞ የመጣው አዲስ ነገር (ክፍል ሁለት)

*************************

1. የንብረት ማስመለስ አዋጅ የተካተተው ውርስ ከወንጀል ህጉ የንብረት መውረስ ቅጣት የሚለይበት አግባብ፡- ንብረት መውረስ በጠቅላላው በወንጀል ሕጉ ወይም በሌሎች የወንጀል ድንጋጌዎች የንብረት መውረስ እንደቅጣት ያልተቀመጠ ቢሆንም እንኳን በድርጊቱ ጥቅም መገኘቱ ከተረጋገጠ ንብረቱ እንደሚወረስ የሚደነግግ ነው፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም ሰው ከወንጀል ድርጊቱ ሊጠቀም የማይገባ በመሆኑና በወንጀል ሕጉ መሠረት ንብረት የማይወረስባቸው ነገር ግን በእጅጉ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኙ ወንጀሎችንም የሚያካትት ነው፡፡

2. በጥፋተኝነት ላይ የተመሰረተ እና ያልተመሰረተ ውርስ ልዩነት፡- በጥፋተኝነት ላይ የተመሠረተ የንብረት መውረስ የውርስ መርህ ሲሆን፣ ሁሉንም የይግባኝ ሂደቶችን አልፎ የመጨረሻ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በሚቆጠር ለወንጀል ቅጣት አፈጻጸም በወንጀል ሕግ በተቀመጠው የይርጋ የጊዜ ገደብ ውስጥ ዐቃቤ ሕግ በሚያቀርበው ማመለክቻ መሰረት በፍርድ ቤት የሚሰጥ የውርስ ትዕዛዝ ነው፡፡

በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ የንብረት መውረስ በተለየ ሁኔታ በግልጽ ተዘረዝረው የተቀመጡ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ይህም የወንጀል ጉዳዩን የሚመራው ሥነ-ስርዓት ሂደት እና በሌሎች ምክንያቶች የወንጀሉን ተጠያቂነት ማስቀጠል የማይቻል ከሆነ ወይም የሚቋረጥበት ሁኔታ ሲፈጠር ወይም በማንኛውም ምክንያት የወንጀል ጥፋተኛነት ውሳኔ ማሰጠት የማይቻልበት ሁኔታ ከተፈጠረ እና ከወንጀል የተገኘ ጥቅም መኖሩ በማስረጃ ሲረጋገጥ የሚሰጥ የውርስ ውሳኔ ነው፡፡

3. ጥፋተኝነት በፍርድ ቤት ሳይሰጥ ንብረት እንዲወረስ ማደረግ የዜጎችን ህገ-መንገስታዊ ንብረት የማፍራት መብት የማይጥስ ስለመሆኑ፡- ይሄ ሥርዓት በዚሀ ህግ አዲስ የመጣ እና የተዋወቀ አይደለም፡፡ በአዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 35 ስር ጥፋተኝነት ሳይሰጥ ንብረት ስለሚወረስበት አግባብ ከሚታወቅበት ሶስት መነሻዎች (ተከሳሽ ሲሞት፣ ሲጠፋ ወይም ሳይታወቅ ሲቀር) ከሚለው ሰፋ ባለ መልኩ ተግባራዊ ሊሆን ወደሚችልበት ማዕቀፍ መጥቷል እንጂ አዲስ ሀሳብ አይደለም፡፡ ስለሆነም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ የሆነ የዕውቀትና የአረዳድ ችግር እንዳለ በማወቅ ወደተግባር መግባት ያስፈልጋል።

በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሰረተ ውርስ ሲባል ዐቃቤ ህግ እየተነሳ ንብረትን ይወርሳል ሳይሆን ጉዳዩ ላይ አሁንም ቢሆን የውርስ ትዕዛዝ መስጠት የሚችለው ፍርድ ቤት መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ መንገዱ ነው የተቀየረው እንጂ ለዐቃቤ ህግ የማይረጋገጥ/ የማይደረግ የዘፈቀደ ንብረትን የመውረስ ስልጣን ሰጥቶታል ማለት አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ በአዋጁ በተቀመጡት ሁኔታዎች የወንጀል ክስ ማቅረብ ሳይቻል ሲቀር (ለምሳሌ ሰውየው ቢሞት፣ ቢጠፋ፣ በይቅርታ ቢወጣ፣ በወንጀል የማስረጃ ምዘና በወንጀል ጥፋተኝነት ለማረጋገጥ የሚያስችል በቂ ወይም ተቀባይነት ያለው መረጃ ሳይገኝ ሲቀር) ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ፍትሃብሄራዊ ባህሪ ያለው የውርስ አቤቱታን ተከትሎ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት ይሄ የውርስ አይነት መርህ ሳይሆን ልዩ ሁኔታ መሆኑ ነው፡፡

4. አስር ዓመት ወደ ኋላ ሄዶ ተፈፃሚ የሚሆንበት መሰረቱ (የህግ አግባብ) እንዲሁም ምክንያት፡- የሀብት ማሰመለስ አዋጁ በአጠቃላይ ሲታይ ተፈጻሚነቱ ወደፊት ነው፤ ነገር ግን ክፍል 2 ስር የተደነገገው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ብቻ ተፈጻሚነቱ ወደ ኋላ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 8 ላይ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ክስ የሚቀርብበት ጊዜ እና የገንዘብ መጠን ተደንግጓል፡፡

በዚህ አንቀጽ ስር የተካተተው አዋጁ ወደ ኋላ 10 ዓመት ተመልሶ የሚሠራ መሆኑንና ይህንንም ለመክሰስ የአስር ሚሊዮን የገንዘብ ገደብ ተቀምጧል፡፡ ይህም የገንዘብ ገደብ የተቀመጠበት ዋነኛ ምክንያት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ያለውን የሰው ኃይል (የስራውን ስፋት መሸከምና ለመስራት የሚያስችል ልምድና ብቃት ያለው)፣ የመክሰስ አቅም እና የፋይናንስ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ የሃብት መጠን ያላቸውን ግለሰቦች በመተው ከፍተኛ ንብረት ያላቸውን ተጠያቂ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሕጉ ወደ ኋላ ተመልሶ እንደመስራቱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ማሕበራዊ እና የፋይናንስ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደርሳሉ ተብሎ የሚገመቱትን ግለሰቦችና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችን ተጠያቂ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡

ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ ወደ ኋላ ሄዶ የማይሰራ ከሆነ፣ ከዚህ በፊት በህገ ወጥ መንገድ ንብረት ያፈሩ ሰዎችን ህጉ ከወጣ በኋላ ብቻ ተጠያቂ የምናደርግ ከሆነ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ያገኙትን ንብረት ህጋዊ የማድረግ እንድምታ ያለው በመሆኑ እንዲሁም አዋጁ እንደሌሎች ህጎች ከወጣ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን ከሆነ በዚህ አዋጅ ልንጠይቅ የምንችለው ቀጣዩን ትውልድ ብቻ በመሆን ከአዋጁ አላማ እንፃር ወደ ኋላ ሄዶ እንዲሰራ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኗል፤ ከዚህ በተጨማሪም የሌሎች ሀገራት ልምድም ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ ህጋቸው ወደ ኋላ ሄዶ ተፈፃሚ እንደሚሆን ያመለክታል።

በሌላ በኩል አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ተጠያቂነት ያለምንም የገንዘብ መጠን ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡ ይህ ድንጋጌ እስካሁን ድረስ ከፍተኛ ውዝግብ እያስነሳ የሚገኝ ሲሆን፣ በተለየ ሁኔታ ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ በተለይም በአፈጻጸም ረገድ ከመነሻው ጀምሮ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ያልተፈለጉ ጉዳዮችን በመለየት በዝርዝር አሰራር ሂደት ሊቀረፉ ይገባል። አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ከመነሻውም ጀምሮ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን ለማስረዳት የሚቀርቡ ማስረጃዎችን በተመለከተ የተዛቡ ነገሮች በሚዲያም ሲቀርብ ስለነበር፤ አዋጁ ከመውጣቱ ጋር ተያይዞ የካፒታል መሸሽ እንዳያጋጥም ከጥቂት ዓመታት በፊት አብዛኛዉ ማህበረሰብ ግብይቱ ካሽ ቤዝድ በመሆኑ እና በመደበኛ የባንክ ሥርዓት ክፍያን ስለማይፈፅም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራት አስፈላጊ ነው።

5. ከ10 ዓመት ወደ ኋላ በመሄድ የሀብትን ምንጭ በመረጃ ማስረዳት ለኛ ሀገር የመረጃ አያያዝ ደካማ በሆነበት ዜጎች ላይ ጫና የማይፈጥር ስለመሆኑ፡- አዋጁ የሀብት ምንጭ አስረዳ ሲባል ሀብቱን ያገኘበትን እንዲያስረዳ እንጂ ለእያንዳንዱ ላፈራው ንብረት ደረሰኝ አቅርብ እያለ አይደለም፡፡

አንድ ሰው ያለ አግባብ ያፈራው ንብረት ቤት ቢሆን ቤቱን የገዛበት የሸያጭ ውል አይደለም የሀብት ምንጭ ማስረጃ ተደርጎ የሚቆጠረው፡፡ ቤቱን የገዛበትን ሀብት ያገኘበት ምንጭ ህጋዊ መሆኑን ማስረዳት መቻል አለበት፡፡ ቤቱን ለመግዛት ያወጣው ብር የተገኘው በህጋዊ መንገድ መሆኑን ነው የምርመራው/የክሱ ዋና ጭብጥ፤ ይህ ደግሞ የግድ በሰነድ ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም፡፡ ህጉ የሀብት ምንጭን ለማስረዳት የሰነድ ማስረጃ ብቻ ነው ብሎ ገደብ አላደረገም፡፡

6. አዋጁ ለጠቋሚዎች ማበረታቻ መስጠቱ መጠቃቂያ እንዳይሆን የተደረገ የህግ መዓቀፍ ስለመሆኑ፡- በወንጀል የተገኘን ሀብት በተመለከተ በራሱ የወንጀል ጥቆማ ብቻ ማቅረብ በቂ በመሆኑ ምክንያት የወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች አዋጅ እንዲሁም በወንጀል ሥነ-ስርዓት የሚገዛው ሂደት መሆኑ ይታወቃል፡፡
በንብረት ማስመለስ አዋጅ ስር ንብረት ጠቋሚ የሚለው ሃሳብ መሰረታዊ መነሻ በወንጀል እና በሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሀብት የሚያካብቱ ሰዎች በአመዛኙ የሰሩትን ወንጀል በማስረጃ ለማረጋገጥ እና በወንጀል ለመክሰስ ባይቻል እንኳን ምንም አይነት ህጋዊ ሥራ ወይም የገቢ ምንጭ ሳይኖራቸው ሰፊ ሀብት አካብተው የሚገኙ ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ በደንብ የሚታወቁ ቢሆንም ይህንን ማጋለጥ በራሱ በጠቋሚዎች ላይ የሚፈጥረው የንብረት እና የህልውና አደጋ ቀላል የማይባል በመሆኑ ምክንያት ለጠቋሚዎች ተገቢ የሚባል ማበረታቻ መስጠት በራሱ ጥቆማ ለመስጠት እንዲነሳሱ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አግኝተው እራሳቸውን የሚጠብቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት በራሱ ውጤታማ አሰራር እንደሆነ ከተለያዩ ሀገራት ልምድ ማየት ይቻላል፡፡

ነገር ግን የቀረበ ጥቆማ ሁሉ ክስ ይቀርብበታል ማለት አይደለም፡፡ ጥቆማው እንደማንኛውም ጥቆማ በምርመራ ውስጥ የሚያልፍ ሆኖ ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ሲኖረው ብቻ ነው ክስ የሚያቀረበው፡፡ ከዚህም አልፎ ደግሞ ጥቆማን መነሻ በማድረግ ክስ ቢቀርብም ዙሮ ዙሮ ውሳኔ የሚሰጠው ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች በግልጽ እና ገለልተኛ ችሎት ፊት ክርክር አድረገው መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፡፡

ስለዚህ ትክክለኛ እና መሰረታዊ ማስረጃ ያላቸው ጥቆማዎች ብቻ ተመርምረው ክስ የሚቀርብባቸው በመሆኑ የትኛውንም ያህል ጥቆማ ቢቀርብ መሰረተ ቢስ ከሆነ ምንም አይነት ውጤት ስለማያስከትል የዜጎች የንብረት መብት እንዲሁ በአሉባልታ ጣልቃ የሚገባበት አለመሆኑን እየተረጋገጠ የሚሄድ ጉዳይ ነው፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የትውልድን ሥነምግባር ለመገንባትና ሙስናን ለመከላከል ቅንጅታዊ አሰራርን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለዴሞክራሲ ተቋማትና ለአጋር አካላት ባለሙያዎች በኮምቦልቻ ከተማ ስልጠና መስጠቱን ገልጿል፡፡

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሀብታሙ ሞገስ ስልጠናው ቀጣይ በምናካሂደው የትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች ላይ በቅንጅት የምንሰራበትን የጋራ ማድረግ ላይ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

የሞራል እሴት በመገንባት የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና ብልሹ አሠራርን መከላከል እንዲሁም የሙስና ወንጀል ድንጋጌዎች በሚሉ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል የስልጠና ባለሙያ በሆኑት አቶ አብዱ መሀመድና አቶ ሀብታሙ አሰፋ ስልጠናው ተሰጥቷል።

የስልጠናው አላማ የሞራል ግንባታን በተቋማት ተግባራዊ በማድረግ የአመለካከት ለውጥ ለማምጣትና ሙስናን ለመከላከል መሆኑ ተገልጿል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሰው አስተሳሰቡ ካልተቀየረ በቀር በቅጣት ስለማይማር ሰውን ለመግራትና ሙስናን ለመከላከል በሞራል እሴት ግንባታ ላይ መስራት ትልቅ ውጤት ያመጣል ብለዋል፡፡

በሙስና ወንጀል ዙሪያ የሚሰሩ አቃቢ ህግና ፖሊሶች የሚሰሩት በተለመደው አግባብ እንጂ ኮሚሽኑ ትኩርት ሰጥቶ ወጥ የሆነ ግንዛቤ ስላልተፈጠረላቸው በአሰራሩ ላይ ችግር እየገጠመ መሆኑም ተነስቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በኃይማኖት ተቋማትና እድሮች ላይ ሰፊ የሆነ ሙስና እና የህዝብ ቅሬታ ባለበት ሁኔታ ኮሚሽኑ ጣልቃ ገብቶ አለመስራቱ ችግሩ እየተባባሰ መሆኑ መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ተቋማዊ አቅምን በማጠናከር ዘላቂ የሆነ የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ለመፍታት ከወዲሁ በትጋት መስራት ይጠበቃል - አቶ ፍቅሬ አማን

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ማዕከል ያደረገ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሄዷል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን የፓርቲያችን ብልጽግና ቀይ መስመር የሆኑትን ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን አምርሮ መታገልን ወቅቱ ይጠይቃል ብለዋል።

የህዝብ ፍላጎቶት፣ ስሜትና ጥያቄዎችን በተገቢው ለመረዳት የሚያግዙ ስልቶችን በመጠቀም የልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎችን ለማሳለጥ መትጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አመራሩ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት በማጎልበት በመልካም አስተዳድር ጉዳዮች ላይ የሚስተዋለውን ችግር በመቅረፍ ፈጣንና ጥራት ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

እያጋጠሙ ያሉትን ብልሹ አሰራሮችን የተደራጀ ብርቱ ትግል እንደሚደረግና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፥ 7/24 ሰዓት በመስራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተናበበ መልኩ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንዳሉት አመራሩ አገልጋይ ተኮር እሳቤን በመላበስ ለህዝብ የገባነውን ቃል በፍትሃዊነትና በታማኝነት ማገልገል መቻል አለብን ብለዋል።

ሌብነትና ብልሹ አሰራር ለጠንካራ ፓርቲ፣ መንግስትና ሀገር ግንባታ እንቅፋት በመሆናቸው ችግሩን በማጤን፣ በመመርመርና በጥልቀት በማየት ከምንጩ ለማድረቅ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ አብራርተዋል።

በመድረኩ የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳድር ሳንካ በሆኑትና በመንግስት ተቋማት የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ በፍትህ ስርዓት የሚስተዋሉ ጉድለቶች፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮች እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ከችግሮች መሻገር በሚያስችል መልኩ ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ በቀጣይ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን የተላበሰ የአሰራር ስርዓትን በመከተል የህዝቡን የመልካም አስተዳድርና ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ ብሎም በተናበበ መልኩ ለመስራት እንደሚያስችል መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል

*********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በሚመለከት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

👉 ሙስና እና ብልሹ አሠራር እያደረሰ ያለውን ሀገራዊ ጉዳት ለመቀነስ ምን እየተሠራ ነው?

👉 የፍትሕ ተደራሽነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት መንግሥት በቀጣይ ምን ለመስራት አስቧል?

👉 በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂት ለመፍታት በቀጣይ የሚቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?

👉 መንግሥት በድጎማ የሚያቀርበው ነዳጅ በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳይሸጥ ምን አይነት ጠንካራ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?

👉 የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር መንግሥት ምን እየሠራ ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319