ሙስናን እና የመልካም አስተዳደር ብልሹነትን ለመቅረፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሙስናን እና የመልካም አስተዳደር ብልሹነት ለመቅረፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ዑሱማን አህመድ ገልፀዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዑሱማን አህመድ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና የብልሹ አሰራር ክፍታቶችን ለማረም የሚያስችል የመወያያ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተካሄዶበታል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ሙስናን በመቅረፍ በሀገር ዕድገት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመግታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ዑሱማን አህመድ አስገንዝበዋል።
በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት መልኩን እያቀያየረ ህዝቡን እያማረረ ያለውን የኑሮ ውድነትና ዋጋ ግሽበት ጫናዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በህገወጦች ላይ የተጠናከረ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ተናግረዋል።
አቶ ኢሳቅ አክለውም ኮሚቴው በሕገ-ወጥ የከተማና ገጠር መሬት ወራራ፣ በየቦታው ህገ-ወጥ ኬላዎች እንዲነሱ እና ችግሮችን ለማስቀረት ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ ማሳሰባቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ኮሚቴው ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ፈጠራና ስልጠና ከመስጠት ባለፈ በሁሉም የህዝብ እሮሮ የሚታዩ ችግሮችን በማጤንና በማስተካከል ለህብተሰቡ ተጠቃሚነት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

የንብረት ማስመለስ አዋጁ አስፈላጊነት እና ይዞ የመጣው አዲስ ነገር (ክፍል ሁለት)
*************************
1. የንብረት ማስመለስ አዋጅ የተካተተው ውርስ ከወንጀል ህጉ የንብረት መውረስ ቅጣት የሚለይበት አግባብ፡- ንብረት መውረስ በጠቅላላው በወንጀል ሕጉ ወይም በሌሎች የወንጀል ድንጋጌዎች የንብረት መውረስ እንደቅጣት ያልተቀመጠ ቢሆንም እንኳን በድርጊቱ ጥቅም መገኘቱ ከተረጋገጠ ንብረቱ እንደሚወረስ የሚደነግግ ነው፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም ሰው ከወንጀል ድርጊቱ ሊጠቀም የማይገባ በመሆኑና በወንጀል ሕጉ መሠረት ንብረት የማይወረስባቸው ነገር ግን በእጅጉ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኙ ወንጀሎችንም የሚያካትት ነው፡፡
2. በጥፋተኝነት ላይ የተመሰረተ እና ያልተመሰረተ ውርስ ልዩነት፡- በጥፋተኝነት ላይ የተመሠረተ የንብረት መውረስ የውርስ መርህ ሲሆን፣ ሁሉንም የይግባኝ ሂደቶችን አልፎ የመጨረሻ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በሚቆጠር ለወንጀል ቅጣት አፈጻጸም በወንጀል ሕግ በተቀመጠው የይርጋ የጊዜ ገደብ ውስጥ ዐቃቤ ሕግ በሚያቀርበው ማመለክቻ መሰረት በፍርድ ቤት የሚሰጥ የውርስ ትዕዛዝ ነው፡፡
በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ የንብረት መውረስ በተለየ ሁኔታ በግልጽ ተዘረዝረው የተቀመጡ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ይህም የወንጀል ጉዳዩን የሚመራው ሥነ-ስርዓት ሂደት እና በሌሎች ምክንያቶች የወንጀሉን ተጠያቂነት ማስቀጠል የማይቻል ከሆነ ወይም የሚቋረጥበት ሁኔታ ሲፈጠር ወይም በማንኛውም ምክንያት የወንጀል ጥፋተኛነት ውሳኔ ማሰጠት የማይቻልበት ሁኔታ ከተፈጠረ እና ከወንጀል የተገኘ ጥቅም መኖሩ በማስረጃ ሲረጋገጥ የሚሰጥ የውርስ ውሳኔ ነው፡፡
3. ጥፋተኝነት በፍርድ ቤት ሳይሰጥ ንብረት እንዲወረስ ማደረግ የዜጎችን ህገ-መንገስታዊ ንብረት የማፍራት መብት የማይጥስ ስለመሆኑ፡- ይሄ ሥርዓት በዚሀ ህግ አዲስ የመጣ እና የተዋወቀ አይደለም፡፡ በአዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 35 ስር ጥፋተኝነት ሳይሰጥ ንብረት ስለሚወረስበት አግባብ ከሚታወቅበት ሶስት መነሻዎች (ተከሳሽ ሲሞት፣ ሲጠፋ ወይም ሳይታወቅ ሲቀር) ከሚለው ሰፋ ባለ መልኩ ተግባራዊ ሊሆን ወደሚችልበት ማዕቀፍ መጥቷል እንጂ አዲስ ሀሳብ አይደለም፡፡ ስለሆነም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ የሆነ የዕውቀትና የአረዳድ ችግር እንዳለ በማወቅ ወደተግባር መግባት ያስፈልጋል።
በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሰረተ ውርስ ሲባል ዐቃቤ ህግ እየተነሳ ንብረትን ይወርሳል ሳይሆን ጉዳዩ ላይ አሁንም ቢሆን የውርስ ትዕዛዝ መስጠት የሚችለው ፍርድ ቤት መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ መንገዱ ነው የተቀየረው እንጂ ለዐቃቤ ህግ የማይረጋገጥ/ የማይደረግ የዘፈቀደ ንብረትን የመውረስ ስልጣን ሰጥቶታል ማለት አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ በአዋጁ በተቀመጡት ሁኔታዎች የወንጀል ክስ ማቅረብ ሳይቻል ሲቀር (ለምሳሌ ሰውየው ቢሞት፣ ቢጠፋ፣ በይቅርታ ቢወጣ፣ በወንጀል የማስረጃ ምዘና በወንጀል ጥፋተኝነት ለማረጋገጥ የሚያስችል በቂ ወይም ተቀባይነት ያለው መረጃ ሳይገኝ ሲቀር) ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ፍትሃብሄራዊ ባህሪ ያለው የውርስ አቤቱታን ተከትሎ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት ይሄ የውርስ አይነት መርህ ሳይሆን ልዩ ሁኔታ መሆኑ ነው፡፡
4. አስር ዓመት ወደ ኋላ ሄዶ ተፈፃሚ የሚሆንበት መሰረቱ (የህግ አግባብ) እንዲሁም ምክንያት፡- የሀብት ማሰመለስ አዋጁ በአጠቃላይ ሲታይ ተፈጻሚነቱ ወደፊት ነው፤ ነገር ግን ክፍል 2 ስር የተደነገገው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ብቻ ተፈጻሚነቱ ወደ ኋላ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 8 ላይ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ክስ የሚቀርብበት ጊዜ እና የገንዘብ መጠን ተደንግጓል፡፡
በዚህ አንቀጽ ስር የተካተተው አዋጁ ወደ ኋላ 10 ዓመት ተመልሶ የሚሠራ መሆኑንና ይህንንም ለመክሰስ የአስር ሚሊዮን የገንዘብ ገደብ ተቀምጧል፡፡ ይህም የገንዘብ ገደብ የተቀመጠበት ዋነኛ ምክንያት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ያለውን የሰው ኃይል (የስራውን ስፋት መሸከምና ለመስራት የሚያስችል ልምድና ብቃት ያለው)፣ የመክሰስ አቅም እና የፋይናንስ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ የሃብት መጠን ያላቸውን ግለሰቦች በመተው ከፍተኛ ንብረት ያላቸውን ተጠያቂ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሕጉ ወደ ኋላ ተመልሶ እንደመስራቱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ማሕበራዊ እና የፋይናንስ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደርሳሉ ተብሎ የሚገመቱትን ግለሰቦችና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችን ተጠያቂ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡
ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ ወደ ኋላ ሄዶ የማይሰራ ከሆነ፣ ከዚህ በፊት በህገ ወጥ መንገድ ንብረት ያፈሩ ሰዎችን ህጉ ከወጣ በኋላ ብቻ ተጠያቂ የምናደርግ ከሆነ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ያገኙትን ንብረት ህጋዊ የማድረግ እንድምታ ያለው በመሆኑ እንዲሁም አዋጁ እንደሌሎች ህጎች ከወጣ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን ከሆነ በዚህ አዋጅ ልንጠይቅ የምንችለው ቀጣዩን ትውልድ ብቻ በመሆን ከአዋጁ አላማ እንፃር ወደ ኋላ ሄዶ እንዲሰራ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኗል፤ ከዚህ በተጨማሪም የሌሎች ሀገራት ልምድም ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ ህጋቸው ወደ ኋላ ሄዶ ተፈፃሚ እንደሚሆን ያመለክታል።
በሌላ በኩል አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ተጠያቂነት ያለምንም የገንዘብ መጠን ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡ ይህ ድንጋጌ እስካሁን ድረስ ከፍተኛ ውዝግብ እያስነሳ የሚገኝ ሲሆን፣ በተለየ ሁኔታ ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ በተለይም በአፈጻጸም ረገድ ከመነሻው ጀምሮ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ያልተፈለጉ ጉዳዮችን በመለየት በዝርዝር አሰራር ሂደት ሊቀረፉ ይገባል። አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ከመነሻውም ጀምሮ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን ለማስረዳት የሚቀርቡ ማስረጃዎችን በተመለከተ የተዛቡ ነገሮች በሚዲያም ሲቀርብ ስለነበር፤ አዋጁ ከመውጣቱ ጋር ተያይዞ የካፒታል መሸሽ እንዳያጋጥም ከጥቂት ዓመታት በፊት አብዛኛዉ ማህበረሰብ ግብይቱ ካሽ ቤዝድ በመሆኑ እና በመደበኛ የባንክ ሥርዓት ክፍያን ስለማይፈፅም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራት አስፈላጊ ነው።
5. ከ10 ዓመት ወደ ኋላ በመሄድ የሀብትን ምንጭ በመረጃ ማስረዳት ለኛ ሀገር የመረጃ አያያዝ ደካማ በሆነበት ዜጎች ላይ ጫና የማይፈጥር ስለመሆኑ፡- አዋጁ የሀብት ምንጭ አስረዳ ሲባል ሀብቱን ያገኘበትን እንዲያስረዳ እንጂ ለእያንዳንዱ ላፈራው ንብረት ደረሰኝ አቅርብ እያለ አይደለም፡፡
አንድ ሰው ያለ አግባብ ያፈራው ንብረት ቤት ቢሆን ቤቱን የገዛበት የሸያጭ ውል አይደለም የሀብት ምንጭ ማስረጃ ተደርጎ የሚቆጠረው፡፡ ቤቱን የገዛበትን ሀብት ያገኘበት ምንጭ ህጋዊ መሆኑን ማስረዳት መቻል አለበት፡፡ ቤቱን ለመግዛት ያወጣው ብር የተገኘው በህጋዊ መንገድ መሆኑን ነው የምርመራው/የክሱ ዋና ጭብጥ፤ ይህ ደግሞ የግድ በሰነድ ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም፡፡ ህጉ የሀብት ምንጭን ለማስረዳት የሰነድ ማስረጃ ብቻ ነው ብሎ ገደብ አላደረገም፡፡
6. አዋጁ ለጠቋሚዎች ማበረታቻ መስጠቱ መጠቃቂያ እንዳይሆን የተደረገ የህግ መዓቀፍ ስለመሆኑ፡- በወንጀል የተገኘን ሀብት በተመለከተ በራሱ የወንጀል ጥቆማ ብቻ ማቅረብ በቂ በመሆኑ ምክንያት የወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች አዋጅ እንዲሁም በወንጀል ሥነ-ስርዓት የሚገዛው ሂደት መሆኑ ይታወቃል፡፡

በንብረት ማስመለስ አዋጅ ስር ንብረት ጠቋሚ የሚለው ሃሳብ መሰረታዊ መነሻ በወንጀል እና በሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሀብት የሚያካብቱ ሰዎች በአመዛኙ የሰሩትን ወንጀል በማስረጃ ለማረጋገጥ እና በወንጀል ለመክሰስ ባይቻል እንኳን ምንም አይነት ህጋዊ ሥራ ወይም የገቢ ምንጭ ሳይኖራቸው ሰፊ ሀብት አካብተው የሚገኙ ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ በደንብ የሚታወቁ ቢሆንም ይህንን ማጋለጥ በራሱ በጠቋሚዎች ላይ የሚፈጥረው የንብረት እና የህልውና አደጋ ቀላል የማይባል በመሆኑ ምክንያት ለጠቋሚዎች ተገቢ የሚባል ማበረታቻ መስጠት በራሱ ጥቆማ ለመስጠት እንዲነሳሱ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አግኝተው እራሳቸውን የሚጠብቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት በራሱ ውጤታማ አሰራር እንደሆነ ከተለያዩ ሀገራት ልምድ ማየት ይቻላል፡፡
ነገር ግን የቀረበ ጥቆማ ሁሉ ክስ ይቀርብበታል ማለት አይደለም፡፡ ጥቆማው እንደማንኛውም ጥቆማ በምርመራ ውስጥ የሚያልፍ ሆኖ ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ሲኖረው ብቻ ነው ክስ የሚያቀረበው፡፡ ከዚህም አልፎ ደግሞ ጥቆማን መነሻ በማድረግ ክስ ቢቀርብም ዙሮ ዙሮ ውሳኔ የሚሰጠው ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች በግልጽ እና ገለልተኛ ችሎት ፊት ክርክር አድረገው መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፡፡
ስለዚህ ትክክለኛ እና መሰረታዊ ማስረጃ ያላቸው ጥቆማዎች ብቻ ተመርምረው ክስ የሚቀርብባቸው በመሆኑ የትኛውንም ያህል ጥቆማ ቢቀርብ መሰረተ ቢስ ከሆነ ምንም አይነት ውጤት ስለማያስከትል የዜጎች የንብረት መብት እንዲሁ በአሉባልታ ጣልቃ የሚገባበት አለመሆኑን እየተረጋገጠ የሚሄድ ጉዳይ ነው፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ነገር ግን የቀረበ ጥቆማ ሁሉ ክስ ይቀርብበታል ማለት አይደለም፡፡ ጥቆማው እንደማንኛውም ጥቆማ በምርመራ ውስጥ የሚያልፍ ሆኖ ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ሲኖረው ብቻ ነው ክስ የሚያቀረበው፡፡ ከዚህም አልፎ ደግሞ ጥቆማን መነሻ በማድረግ ክስ ቢቀርብም ዙሮ ዙሮ ውሳኔ የሚሰጠው ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች በግልጽ እና ገለልተኛ ችሎት ፊት ክርክር አድረገው መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፡፡
ስለዚህ ትክክለኛ እና መሰረታዊ ማስረጃ ያላቸው ጥቆማዎች ብቻ ተመርምረው ክስ የሚቀርብባቸው በመሆኑ የትኛውንም ያህል ጥቆማ ቢቀርብ መሰረተ ቢስ ከሆነ ምንም አይነት ውጤት ስለማያስከትል የዜጎች የንብረት መብት እንዲሁ በአሉባልታ ጣልቃ የሚገባበት አለመሆኑን እየተረጋገጠ የሚሄድ ጉዳይ ነው፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የትውልድን ሥነምግባር ለመገንባትና ሙስናን ለመከላከል ቅንጅታዊ አሰራርን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ
************************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለዴሞክራሲ ተቋማትና ለአጋር አካላት ባለሙያዎች በኮምቦልቻ ከተማ ስልጠና መስጠቱን ገልጿል፡፡
የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሀብታሙ ሞገስ ስልጠናው ቀጣይ በምናካሂደው የትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች ላይ በቅንጅት የምንሰራበትን የጋራ ማድረግ ላይ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የሞራል እሴት በመገንባት የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና ብልሹ አሠራርን መከላከል እንዲሁም የሙስና ወንጀል ድንጋጌዎች በሚሉ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል የስልጠና ባለሙያ በሆኑት አቶ አብዱ መሀመድና አቶ ሀብታሙ አሰፋ ስልጠናው ተሰጥቷል።
የስልጠናው አላማ የሞራል ግንባታን በተቋማት ተግባራዊ በማድረግ የአመለካከት ለውጥ ለማምጣትና ሙስናን ለመከላከል መሆኑ ተገልጿል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሰው አስተሳሰቡ ካልተቀየረ በቀር በቅጣት ስለማይማር ሰውን ለመግራትና ሙስናን ለመከላከል በሞራል እሴት ግንባታ ላይ መስራት ትልቅ ውጤት ያመጣል ብለዋል፡፡
በሙስና ወንጀል ዙሪያ የሚሰሩ አቃቢ ህግና ፖሊሶች የሚሰሩት በተለመደው አግባብ እንጂ ኮሚሽኑ ትኩርት ሰጥቶ ወጥ የሆነ ግንዛቤ ስላልተፈጠረላቸው በአሰራሩ ላይ ችግር እየገጠመ መሆኑም ተነስቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በኃይማኖት ተቋማትና እድሮች ላይ ሰፊ የሆነ ሙስና እና የህዝብ ቅሬታ ባለበት ሁኔታ ኮሚሽኑ ጣልቃ ገብቶ አለመስራቱ ችግሩ እየተባባሰ መሆኑ መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡