ዜጎች መልካም ሥነምግባርን እንዲላበሱ ማስተማር ከመገናኛ ብዙኃን ይጠበቃል
************************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 9/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሚዲያ ተቋማት ከሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል አንጻር ያላቸውን ሚና የተመለከተ ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ላይ የሚዲያ ተቋማት ባለሙያዎች እና የዘርፉ መሪዎች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) "ሙስና እንደ ሀገር የያዝነውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ ወደ ኋላ የሚጎትት ብልሹ ተግባር መኾኑን በመገንዘብ በጋራ መታገል ይገባል" ብለዋል።
ሌብነት የሀገርን እድገት እና የሕዝብን ጥቅም ወደ ኋላ ለመጎትት በጥቂት አጥፊ እጆች የሚፈጸም የሥነምግባር ብልሽት ስለመኾኑም ተናግረዋል። ይህንን ተግባር በማረም በኩል የመገናኛ ብዙኃን ሚና ከፍተኛ ስለመኾኑም ጠቁመዋል።
አሚኮን ጨምሮ ሁሉም የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እና ባለሙያዎች የሕዝብ አገልግሎት ተቋማትን አሠራር መፈተሽ እና ማጋለጥ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በተለይም ጠንካራ የምርመራ ጋዜጠኝነት ሥራን መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የመንግሥት መሪዎች ሥልጣን እና ተጠያቂነትን ጎን ለጎን የያዙ ናቸው፣ ኀላፊነታቸውን እንዴት እየተወጡ እንደኾነ ለሕዝብ ማሳወቅ እና ያጎደሉት ነገር ሲኖርም ለተጠያቂነት አጋልጦ መስጠት ይገባል ብለዋል።
በሥነምግባራቸው፣ በሀገር ወዳድነታቸው እና በታማኝነታቸው ታዋቂ እና ሞዴል የኾኑ ሰዎችን ተሞክሮ በሚዲያ በማቅረብ መጭውን ትውልድ በምግባር ማነጽ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአሚኮ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥየ በበኩላቸው ሙስናን በጋራ ቆሞ ከመከላከል አኳያ በርካታ ክፍተቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
የአፈር ማዳበሪያን እንደ አብነት ያነሱት አቶ ሙሉቀን፣ ይህንን የሕዝብ ህልውና የኾነ ሀብት መስረቅ "ከእናት ጡት እንደመስረቅ" መቁጠር እንዴት አቃተን ሲሉ ጠይቀዋል።
የብልሹ አሠራር እና የሌብነትን ተግባር በጋራ በመቆም መታገል ለነገ የማይባል ሥራ መኾኑንም አንስተዋል።
አሚኮ በሁሉም ሚዲየሞቹ በመጠቀም በሥነምግባር የታነጸ ትውልድ የመፍጠር ኀላፊነቱን እንደሚወጣም ገልጸዋል።
አሚኮ በምርመራ ጋዜጠኝነት እና የተለያዩ ፕሮግራሞቹን በመጠቀም ብልሹ አሠራሮችን የማጋለጥ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ማሩ ቸኮል ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ከመቅረፍ አንጻር የመገናኛ ብዙኃን ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በተለይም ሌብነትን እና ብልሹ አሠራርን የሚጠየፍ ትውልድ ከመገንባት አኳያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
መገናኛ ብዙኃን መልካም እሴቶችን እና ባሕርያትን ማራመድ፣ ሥነምግባር የጎደላቸውን ድርጊቶች እና አመለካከቶች ደግሞ እንዳይስፋፋ መታገል አለባቸው ነው ያሉት።
የትምህርት ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ እና የመሳሰሉት ተቋማት መልካም ሥነምግባርን ለተተኪው ትውልድ ለማስረጽ የሚያደርጉትን አስተምህሮ በሚዲያ ሥራ ማገዝ እንደሚገባም ምክትል ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።
አቶ ማሩ እንዳሉት የተቋማትን ተግባራት፣ በጀት እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን በመከታተል እና ለሕዝብ ሪፖርት በማቅረብ የሕዝብ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ስለመዋሉ መከታተልም ከመገናኛ ብዙኃን ይጠበቃል።
መልካም ሥነምግባር ለሀገር እድገት ያለውን ፋይዳ ገልጦ ማሳየት እና ዜጎች መልካም ሥነምግባርን እንዲላበሱ መምከር እና ማስተማርም ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ይጠበቃል ብለዋል።
ሙስናን በማጋለጥ ወንጀለኞችን ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል የምርመራ ጋዜጠኝነት ሥራ መከናወን እንዳለበትም ምክትል ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችም ሙስናን የሚጠየፍ ትውልድ በመፍጠሩ ረገድ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ ማረጋገጣቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመታገል በሚከናወኑ የሚዲያ ሥራዎች ላይ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዳለበትም ባለሙያዎች ገልጸዋል።
ተጨባጭ ጥፋት በተገኘባቸው ሰዎች ላይም የተጠያቂነት አሠራርን ማስፈን እንደሚገባ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች አሳስበዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

አገልግሎቱ በ22 አመራርና ሰራተኞች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የደሞዝ ቅጣት እርምጃ ወስጃለው አለ
********
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 9/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት ሰባት ወራት ውስጥ ብልሹ አስራርን ለማስወገድ ባከናወናቸው ተግባራት በ22 አመራርና ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቋል፡፡
እርምጃው የተወሰደው ከደንበኞች የቀረቡ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ እና አስፈላጊው ማጣሪያ ተደርጎ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ መላኩ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
እርምጃ ከተወሰደባቸው አመራር እና ሰራተኞች መካከል 3ቱ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እና 19ኙ የደመወዝ ቅጣት የተቀጡ መሆናቸውን ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የብልሹ አሰራር እና የሙስና ጥቆማ መስጫ ዲጂታል የሞባይል መተግበሪያ ስራ ላይ ማዋሉ የሚታወስ ነው፡፡

ሙያዊ ሥነምግባርን በመላበስ ራስን ከብልሹ አሰራር መጠበቅ እንደሚገባ ተገለፀ
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 9/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለአዲስ ከተማ፣ ለልደታ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ትራፊክ ፖሊስ ዲቪዥን አመራርና አባላት በሙያዊ ሥነምግባር፣ በብልሹ አሰራር ተጋላጭነት እና በሙስና መከላከል ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
የከተማው የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር መቅደስ ተስፋዬ ስልጠናው ከዚህ ቀደም በተለያዩ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት መሰጠቱን ገልፀው፥ ሙያዊ ሥነምግባር በመላበስ ራስን ከብልሹ አሰራር መጠበቅ አንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ሙስናን መከላከል ግለሰባዊ ሳይሆን ሀገራዊ ጉዳይ ነው ያሉት ም/ኮሚሽነሯ፥ ይህን ተግባር ውጤታማ ለማድረግ ዋነኛ ባለድርሻ አካል በመሆን ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዋል።
የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ስልጠና ዳ/ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት እንደገለፁት የትራፊክ ፖሊስ አባላት ሙያዊ ሥነምግባርን ተላብሰውና ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ተግባራትን ማከናወናቸው በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የሚደርስ አደጋ እንዲቀንስ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም አባላቱ በሙያ ሥነምግባር መታነፃቸው የሙያውን ቅቡልነት ከፍ በማድረግ አወንታዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ሙስናን እና የመልካም አስተዳደር ብልሹነትን ለመቅረፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሙስናን እና የመልካም አስተዳደር ብልሹነት ለመቅረፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ዑሱማን አህመድ ገልፀዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዑሱማን አህመድ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና የብልሹ አሰራር ክፍታቶችን ለማረም የሚያስችል የመወያያ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተካሄዶበታል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ሙስናን በመቅረፍ በሀገር ዕድገት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመግታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ዑሱማን አህመድ አስገንዝበዋል።
በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት መልኩን እያቀያየረ ህዝቡን እያማረረ ያለውን የኑሮ ውድነትና ዋጋ ግሽበት ጫናዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በህገወጦች ላይ የተጠናከረ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ተናግረዋል።
አቶ ኢሳቅ አክለውም ኮሚቴው በሕገ-ወጥ የከተማና ገጠር መሬት ወራራ፣ በየቦታው ህገ-ወጥ ኬላዎች እንዲነሱ እና ችግሮችን ለማስቀረት ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ ማሳሰባቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ኮሚቴው ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ፈጠራና ስልጠና ከመስጠት ባለፈ በሁሉም የህዝብ እሮሮ የሚታዩ ችግሮችን በማጤንና በማስተካከል ለህብተሰቡ ተጠቃሚነት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የንብረት ማስመለስ አዋጁ አስፈላጊነት እና ይዞ የመጣው አዲስ ነገር (ክፍል ሁለት)
*************************
1. የንብረት ማስመለስ አዋጅ የተካተተው ውርስ ከወንጀል ህጉ የንብረት መውረስ ቅጣት የሚለይበት አግባብ፡- ንብረት መውረስ በጠቅላላው በወንጀል ሕጉ ወይም በሌሎች የወንጀል ድንጋጌዎች የንብረት መውረስ እንደቅጣት ያልተቀመጠ ቢሆንም እንኳን በድርጊቱ ጥቅም መገኘቱ ከተረጋገጠ ንብረቱ እንደሚወረስ የሚደነግግ ነው፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም ሰው ከወንጀል ድርጊቱ ሊጠቀም የማይገባ በመሆኑና በወንጀል ሕጉ መሠረት ንብረት የማይወረስባቸው ነገር ግን በእጅጉ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኙ ወንጀሎችንም የሚያካትት ነው፡፡
2. በጥፋተኝነት ላይ የተመሰረተ እና ያልተመሰረተ ውርስ ልዩነት፡- በጥፋተኝነት ላይ የተመሠረተ የንብረት መውረስ የውርስ መርህ ሲሆን፣ ሁሉንም የይግባኝ ሂደቶችን አልፎ የመጨረሻ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በሚቆጠር ለወንጀል ቅጣት አፈጻጸም በወንጀል ሕግ በተቀመጠው የይርጋ የጊዜ ገደብ ውስጥ ዐቃቤ ሕግ በሚያቀርበው ማመለክቻ መሰረት በፍርድ ቤት የሚሰጥ የውርስ ትዕዛዝ ነው፡፡
በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ የንብረት መውረስ በተለየ ሁኔታ በግልጽ ተዘረዝረው የተቀመጡ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ይህም የወንጀል ጉዳዩን የሚመራው ሥነ-ስርዓት ሂደት እና በሌሎች ምክንያቶች የወንጀሉን ተጠያቂነት ማስቀጠል የማይቻል ከሆነ ወይም የሚቋረጥበት ሁኔታ ሲፈጠር ወይም በማንኛውም ምክንያት የወንጀል ጥፋተኛነት ውሳኔ ማሰጠት የማይቻልበት ሁኔታ ከተፈጠረ እና ከወንጀል የተገኘ ጥቅም መኖሩ በማስረጃ ሲረጋገጥ የሚሰጥ የውርስ ውሳኔ ነው፡፡
3. ጥፋተኝነት በፍርድ ቤት ሳይሰጥ ንብረት እንዲወረስ ማደረግ የዜጎችን ህገ-መንገስታዊ ንብረት የማፍራት መብት የማይጥስ ስለመሆኑ፡- ይሄ ሥርዓት በዚሀ ህግ አዲስ የመጣ እና የተዋወቀ አይደለም፡፡ በአዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 35 ስር ጥፋተኝነት ሳይሰጥ ንብረት ስለሚወረስበት አግባብ ከሚታወቅበት ሶስት መነሻዎች (ተከሳሽ ሲሞት፣ ሲጠፋ ወይም ሳይታወቅ ሲቀር) ከሚለው ሰፋ ባለ መልኩ ተግባራዊ ሊሆን ወደሚችልበት ማዕቀፍ መጥቷል እንጂ አዲስ ሀሳብ አይደለም፡፡ ስለሆነም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ የሆነ የዕውቀትና የአረዳድ ችግር እንዳለ በማወቅ ወደተግባር መግባት ያስፈልጋል።
በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሰረተ ውርስ ሲባል ዐቃቤ ህግ እየተነሳ ንብረትን ይወርሳል ሳይሆን ጉዳዩ ላይ አሁንም ቢሆን የውርስ ትዕዛዝ መስጠት የሚችለው ፍርድ ቤት መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ መንገዱ ነው የተቀየረው እንጂ ለዐቃቤ ህግ የማይረጋገጥ/ የማይደረግ የዘፈቀደ ንብረትን የመውረስ ስልጣን ሰጥቶታል ማለት አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ በአዋጁ በተቀመጡት ሁኔታዎች የወንጀል ክስ ማቅረብ ሳይቻል ሲቀር (ለምሳሌ ሰውየው ቢሞት፣ ቢጠፋ፣ በይቅርታ ቢወጣ፣ በወንጀል የማስረጃ ምዘና በወንጀል ጥፋተኝነት ለማረጋገጥ የሚያስችል በቂ ወይም ተቀባይነት ያለው መረጃ ሳይገኝ ሲቀር) ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ፍትሃብሄራዊ ባህሪ ያለው የውርስ አቤቱታን ተከትሎ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት ይሄ የውርስ አይነት መርህ ሳይሆን ልዩ ሁኔታ መሆኑ ነው፡፡
4. አስር ዓመት ወደ ኋላ ሄዶ ተፈፃሚ የሚሆንበት መሰረቱ (የህግ አግባብ) እንዲሁም ምክንያት፡- የሀብት ማሰመለስ አዋጁ በአጠቃላይ ሲታይ ተፈጻሚነቱ ወደፊት ነው፤ ነገር ግን ክፍል 2 ስር የተደነገገው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ብቻ ተፈጻሚነቱ ወደ ኋላ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 8 ላይ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ክስ የሚቀርብበት ጊዜ እና የገንዘብ መጠን ተደንግጓል፡፡
በዚህ አንቀጽ ስር የተካተተው አዋጁ ወደ ኋላ 10 ዓመት ተመልሶ የሚሠራ መሆኑንና ይህንንም ለመክሰስ የአስር ሚሊዮን የገንዘብ ገደብ ተቀምጧል፡፡ ይህም የገንዘብ ገደብ የተቀመጠበት ዋነኛ ምክንያት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ያለውን የሰው ኃይል (የስራውን ስፋት መሸከምና ለመስራት የሚያስችል ልምድና ብቃት ያለው)፣ የመክሰስ አቅም እና የፋይናንስ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ የሃብት መጠን ያላቸውን ግለሰቦች በመተው ከፍተኛ ንብረት ያላቸውን ተጠያቂ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሕጉ ወደ ኋላ ተመልሶ እንደመስራቱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ማሕበራዊ እና የፋይናንስ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደርሳሉ ተብሎ የሚገመቱትን ግለሰቦችና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችን ተጠያቂ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡
ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ ወደ ኋላ ሄዶ የማይሰራ ከሆነ፣ ከዚህ በፊት በህገ ወጥ መንገድ ንብረት ያፈሩ ሰዎችን ህጉ ከወጣ በኋላ ብቻ ተጠያቂ የምናደርግ ከሆነ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ያገኙትን ንብረት ህጋዊ የማድረግ እንድምታ ያለው በመሆኑ እንዲሁም አዋጁ እንደሌሎች ህጎች ከወጣ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን ከሆነ በዚህ አዋጅ ልንጠይቅ የምንችለው ቀጣዩን ትውልድ ብቻ በመሆን ከአዋጁ አላማ እንፃር ወደ ኋላ ሄዶ እንዲሰራ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኗል፤ ከዚህ በተጨማሪም የሌሎች ሀገራት ልምድም ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ ህጋቸው ወደ ኋላ ሄዶ ተፈፃሚ እንደሚሆን ያመለክታል።
በሌላ በኩል አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ተጠያቂነት ያለምንም የገንዘብ መጠን ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡ ይህ ድንጋጌ እስካሁን ድረስ ከፍተኛ ውዝግብ እያስነሳ የሚገኝ ሲሆን፣ በተለየ ሁኔታ ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ በተለይም በአፈጻጸም ረገድ ከመነሻው ጀምሮ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ያልተፈለጉ ጉዳዮችን በመለየት በዝርዝር አሰራር ሂደት ሊቀረፉ ይገባል። አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ከመነሻውም ጀምሮ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን ለማስረዳት የሚቀርቡ ማስረጃዎችን በተመለከተ የተዛቡ ነገሮች በሚዲያም ሲቀርብ ስለነበር፤ አዋጁ ከመውጣቱ ጋር ተያይዞ የካፒታል መሸሽ እንዳያጋጥም ከጥቂት ዓመታት በፊት አብዛኛዉ ማህበረሰብ ግብይቱ ካሽ ቤዝድ በመሆኑ እና በመደበኛ የባንክ ሥርዓት ክፍያን ስለማይፈፅም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራት አስፈላጊ ነው።
5. ከ10 ዓመት ወደ ኋላ በመሄድ የሀብትን ምንጭ በመረጃ ማስረዳት ለኛ ሀገር የመረጃ አያያዝ ደካማ በሆነበት ዜጎች ላይ ጫና የማይፈጥር ስለመሆኑ፡- አዋጁ የሀብት ምንጭ አስረዳ ሲባል ሀብቱን ያገኘበትን እንዲያስረዳ እንጂ ለእያንዳንዱ ላፈራው ንብረት ደረሰኝ አቅርብ እያለ አይደለም፡፡
አንድ ሰው ያለ አግባብ ያፈራው ንብረት ቤት ቢሆን ቤቱን የገዛበት የሸያጭ ውል አይደለም የሀብት ምንጭ ማስረጃ ተደርጎ የሚቆጠረው፡፡ ቤቱን የገዛበትን ሀብት ያገኘበት ምንጭ ህጋዊ መሆኑን ማስረዳት መቻል አለበት፡፡ ቤቱን ለመግዛት ያወጣው ብር የተገኘው በህጋዊ መንገድ መሆኑን ነው የምርመራው/የክሱ ዋና ጭብጥ፤ ይህ ደግሞ የግድ በሰነድ ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም፡፡ ህጉ የሀብት ምንጭን ለማስረዳት የሰነድ ማስረጃ ብቻ ነው ብሎ ገደብ አላደረገም፡፡
6. አዋጁ ለጠቋሚዎች ማበረታቻ መስጠቱ መጠቃቂያ እንዳይሆን የተደረገ የህግ መዓቀፍ ስለመሆኑ፡- በወንጀል የተገኘን ሀብት በተመለከተ በራሱ የወንጀል ጥቆማ ብቻ ማቅረብ በቂ በመሆኑ ምክንያት የወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች አዋጅ እንዲሁም በወንጀል ሥነ-ስርዓት የሚገዛው ሂደት መሆኑ ይታወቃል፡፡