Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ሁለንተናዊ ተቋማዊ አቅም በማቀናጀትና በመረባረብ ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን መታገል እንደሚገባ ተገለጸ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መካከል ብልሹ አሰራርንና ሙስናን ለመታገል በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የክልሉ ሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙሉሰው ዘውዴ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ የመደመር ሳንካ የሆኑት ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን በጽኑ አቋም በመታገል ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መረባረብ ይገባል።

የስምምነት ሰነዱ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማሳለጥ ውጤታማ የሆነ የሙስና እና ብልሹ አሰራሮች ላይ ማዕከል አድርጎ በጥብቅ ዲስፕሊን እና በተጠናከረ መልኩ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለፀረ-ሙስና ትግሉ የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት፣ ጥናት ላይ ተመስርቶ ሙስናን መከላከል እና መረጃዎችን መለዋወጥ እንዲሁም የትውልድ ሥነምግባር ግንባታው ላይ በጋራ ተቀናጅቶ መስራት የኮሚሽኖች የስምምነት አንኳር ጉዳዮች እንደሆነ ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ ገልጸዋል።

በመግባቢያ ሰነዱ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አይበራ እንደገለጹት፤ በየደረጃው ያለው አመራር፣ ባለሙያና ህብረተሰቡ በሙስና እና ብልሹ አሰራሮች ላይ የተቀናጀ ትግል በማድረግ የተጀመረውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ መረባረብ ይገባል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ተቋማት ሁለንተናዊ አቅም በማቀናጀት በመረባረብ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣትና የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተቀናጀና በተደራጀ ሁኔታ ሙስና እና ብልሹ አሰራር በመከላከል የሀገራችንን እና የክልሉን ሁለንተናዊ ብልጽግና እንዲረጋገጥ ሁሉም አመራርና ባለሙያዎች በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

በመንግስት እና ህዝብ መካከል ሆኖ በህገ ወጥ ተግባር ላይ የተሰማራውን ኃይል በተቀናጀ መንገድ ተጨባጭነት ያለው የሙስና መከላከል በመስራት እንዲነጠል ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል በየደረጃው በተደረጉ የተቀናጁ ጥረቶች በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡ መሆኑን ገልጸው፣ ይህን የተቀናጀ ጥረት የመንግስትና ህዝባዊ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በቁርጠኝነት መታገል እንደሚገባ አመላክተዋል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ያዙ እንደገለጹት፤ በፀረ-ሙስና ትግል ላይ በጋራ አቋም ከሰራን ፓርቲው ያስቀመጣቸውን ግቦች ለማሳካት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

ሙስና እና ሌብነት የብልጽግና ፓርቲ ቀይ መስመር በመሆኑ እነዚህን ብልሹ አሰራሮችን ከምንጩ ለማድረቅ አመራሩና ባለሙያው በጽኑ አቋም መታገል እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

በየደረጃዉ የሚገኙ አባላትና አመራር በፕሮግራም፣ በመተዳደሪያ ደንብ እና በዲስፒሊን መመሪያ የተቀመጡ የፀረ-ሙስና ትግል አቅጣጫዎች ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ የፀረ-ሙስና ህጎችና አሰራሮች ግንዛቤ ኖሯቸዉ ተልዕኳቸዉን በብቃትና በቁርጠኝነት መወጣት ይጠበቃል ብለዋል።

የክልሉ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰብሳቢ ወ/ሮ ራሄል ለዊ በበኩላቸው ጠንካራ ኮሚሽንና ፓርቲ ለመገንባት የፀረ-ሙስና ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በቁርጠኝነት መስራት አለብን ብለዋል።

ሌብነትን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር አመራሩ የመሪነት ሚናውን መወጣት እንዳለበት መግለፃቸውን የደ.ሬቴ.ድ ዘግቧል።

በመግባቢያ የስምምነት ሰነዱ ላይ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች፣ የክልሉ የህብረት ኮሚሽን ኮሚቴ አባላት፣ የዞን የኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሥነምግባር የታነፀ ሠራዊት ተልዕኮውን በድል እንደሚወጣ ተገለፀ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በጦላይ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አመራሮችና ሠራዊት አባላት የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ተሰጥቷል።

በትምህርቱም በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ውስጥ እየሰለጠኑ ያሉ ሰልጣኝ ምልምል ወታደሮች፣ የ27ኛ ዙር መጋቢ ሃምሳ አለቃ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና የስታፍ ክፍል አባላቶች የተሳተፉ ሲሆን፣ በሥነምግባር የታነፀ ሠራዊት ተልዕኮውን በድል መወጣት እንደሚችልም ተገልጿል።

በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የሥነምግባር ክትትል ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ሰፊነሽ ቢረዳ ውትድርና የህይወት መስዋዕትነት የሚከፈልበት፣ ሀገርንና ህግን የሚጠበቅበት ውድና እጅግ የተከበረ የሙያ ዘርፍ በመሆኑ መሰረቱ ሥነምግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ውትድርና እጅግ የተከበረ ሙያ በመሆኑ ለሙያው የሚመጥን ሥነምግባር ያስፈልገዋል ያሉት ሌተናል ኮሎኔል ሰፊነሽ፣ መከላከያ ሰራዊታችን በጥሩ ሥነምግባርና ሙያዊ ዲሲፕሊን ሀገርንና ህዝብን ማገልገል ስለሚጠበቅበት ትምህርቱን መስጠት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ትምህርቱን የሰጡት ሻምበል አብዮት መንገሻ እንደ ተቋም በሥነምግባር የታነፀ መከላከያ ሠራዊት ለመገንባት ዓላማ ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን አስታውሰው፣ ሁሉም የመከላከያ ሠራዊት አባላት መልካም ሥነምግባርንና ጥሩ ባህሪን በመላበስ የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ በጀግንነት በታማኝነትና በሙያዊ ዲሲፕሊን ማከናወን ይጠበቅበታል ሲሉ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ በሚል መሪ ሀሳብ ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአምቦ ዙሪያ ፕሮጀክት ሳይት ላይ ላሉ የተቋሙ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች የሥነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የንብረት ማስመለስ አዋጁ አስፈላጊነት እና ይዞ የመጣዉ አዲስ ነገር (ክፍል አንድ)

***************

1. የንብረት ማስመለስ ምንነት

የንብረት ማስመለስ ማለት በህገወጥ ድርጊት ምክንያት የተገኘን/የተመዘበረ ሃብትን/ንብረትን መመርመር፣ መለየት፣ ማገድ፣ መያዝ እንዲሁም መውረስና ማስተዳደርን የሚያካትት የህግ ሂደት ነው፡፡

2. የንብረት ማስመለስ አዋጁ አስፈላጊነት እና ይዞ የመጣዉ አዲስ ነገር፡- የንብረት ማስመለስ አዋጁ (አዋጅ ቁጥር 1364/2017) አስፈላጊነት እና ይዞ የመጣዉ አዲስ ነገር በተመለከተ ኢትዮጵያ የተመድ እና የማፑቶ ፀረ-ሙስና ስምምነቶችን ፈርማ ያጸደቀች አገር ናት፡፡

2.1. የንብረት ማስመለስ አዋጁ አስፈላጊነት

የተለያዩ የአለም ዓቀፍ ግዴታዎች ያለባት በመሆኑ እና የንብረት ማስመለስ ሕግጋት፣ ስምምነቶችና ልምዶች ጋር በተጣጣመ መልኩ መዘጋጀት የሚያስፈልግ በመሆኑ፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ ማንኛውም ዓይነት የገንዘብ ወይም የንብረት ጥቅም የሚያስገኝ ወይም ጉዳት እንዲደርስ የሚያደርግ ወንጀል በመፈጸም የተገኘውን ጥቅም ወይም የደረሰውን ጉዳት የሚያካክስ የሀብት ማስመለስ ሥርዓት የሚደነግጉ እዚህም እዛም የተበታተኑ የነበሩ መሆኑ፣ የንብረት ማስመለስ ሕግ ላይ ተጠቃልለው የማይገኙ በመሆናቸው በአፈጻጸም እና በሀብት ማስተዳደር ሂደት ላይ የራሳቸው የሆነ ክፍተት ማስከተላቸው ተጠቃሽ ነው፡፡

እነዚህ የንብረት ማስመለስ ድንጋጌዎች ወደ አንድ የሕግ ማዕቀፍ በማምጣት እና ለሁሉም የወንጀል ዓይነቶች እንዲያገለግሉ በማድረግ ለመሰረታዊ የሕግና የአፈጻጸም ጥያቄዎች ወጥነት ያለውና በቂ መልስ የሚሰጥ ሕግ እንዲኖር ማድረግ አላማ በማድረግ የወጣ ነው፡፡

2.2. የንብረት ማስመለስ ህግ አላማ

የንብረት ማስመለስ ህግ ዋና አለማው የወንጀል ፍሬ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመያዝ፣ ለማገድ፣ ለመውረስ ወይም ለማስተዳደር የሚያስችል ግልጽና ዝርዝር የሕግ ማዕቀፍ በማበጀት ማንም ሰው ከሕገ-ወጥ ድርጊት ማናቸውንም አይነት የኢኮኖሚ ጥቅም እንዳያገኝ ለማድረግ እና የንብረት ማስመለስ ሕግ ወንጀልን በመከላከል ሂደት ያለውን ከፍተኛ ሚና ለማሳካት የሚያስችል የንብረት ማስመለስና ማስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ነው፡፡

3. የንብረት ማስመለስ የህግ መአቀፍ (አዋጅ) ዲያስፖራዎችን ኢላማ ያደረገ አለመሆኑ እና መደበኛ ባልሆነ መልኩ ገንዘብ በመላክ ንብረት ያፈሩትን ስጋት ላይ የማይጥል እንዲሁም ኢንቨስትመንትን የማይጎዳ መሆኑን እንደሚከተለው መጥቀስ ይቻላል፡፡

👉🏿 በመሰረቱ የትኛውም ህግ አንድን የማህበረሰብ ክፍል ኢላማ/ታርጌት/ አደርጎ በሆነ መልኩ ሊወጣ አይችልም፡፡ የህግ መርህም አይደለም፡፡ በመሆኑም ህጉ ትኩረት አድርጎ የተነሳው የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል የለም፡፡ ህግ ሁሌም ትኩረት የሚያደርገው ህገወጥ ተግባሩ ላይ እንጂ ግለሰብ፣ ድርጅት ወይም የተወሰነን ማህበረሰብ አይደለም፡፡

👉🏿 ይህ ህግ የሚመለከተው በህገወጥ መንገድ ከግለሰቦች፣ ከህዝብ እና ከመንግስት ላይ በወንጀል ድርጊት ምክንያት ንብረትና ሀብት ያፈሩ ሰዎችን ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች በህገ-ወጥ መንገድ ያገኙትን ንብረት ልትጠቀሙበት አይገባም ማለት ደግሞ በየትኛውም መመዘኛ ትክክለኛ እና ህጋዊ አካሄድ ነው፡፡

ከዚህ ውጪ ግን ቁጥጥር የማይደረግበት የገንዘብ ፍሰት መኖር፣ ዜጎች ከላባቸው ይልቅ በወንጀል ድርጊት የሚከብሩበትን የሚያበረታታ፣ ሀገር በተቃራኒው የዜጎችን ፍትሀዊ የሀብት ተጠቃሚነት ከማጥፋቱም በላይ በዚህ መልክ የሚገኙ ንብረቶች ምንም አይነት ክትትልና ቁጥጥር ስለማይደረግባቸው ተመልሶ ለተለያየ አይነት የወንጀል መፈፀሚያነት ሊውሉ እንደሚችሉ መረዳት ያስፈልጋል፡፡

ስለዚህ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚሸሹ ሀብቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስራን በግልጽ ስርዓት መምራት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ፍሰትን የሚያረጋገጥ በመሆኑ ለኢንቨስትመንት ሳቢ እና አስተማማኝ አካባቢ የሚፈጥር ነው፤ በዚህም ህጋዊ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ባለሃብቶችንና ዜጎችን ከህገ-ወጥ የሀብት ሰብሳቢዎች የሚጠብቅ ህግ ነው፡፡

👉🏿 አንድን ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ይዟል የሚባልን ሰው በሚመረመርበት ወቅት ከውጭ ሀገር ተልኮለት የሰራውን ቤት ወይም ለኑሮ የሚያስፈልገውን ጥቂት ነገር ላይ ትኩረት ያደረገ ሳይሆን አጠቃላይ ግለሰቡ የመኖሪያ ቦታ፣ በተደጋጋሚ ግለሰቡ የሚገኝበት ቦታ፣ ግለሰቡ የሚይዛቸው ቅንጡ መኪናዎች፣ ጌጣጌጦች፣ የኑሮ ሁኔታ መደበኛ ያልሆነ የባንክ ተቀማጭና ግብይቶች (መሬት፣ ቤት ወይም የትኛውም ንብረት)፣ ከተለያዩ ተቋማት (ውጭ ሀገርም፣ ሀገር ውስጥም) እንዲሁም ከግለሰቦች የሚመጣ ሪፖርት ወይም ጥቆማ በአንድነት የሚታዩ ጉዳዮች ናቸው እንጂ በጥቂት ጉዳዮች (ማንኛውም ሰው ለኑሮ የሚያስፈልገውን መጠቀሚያ) ላይ ያነጣጠረ አይደለም፡፡

👉🏿 ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ የአንድን ግለሰብ/ድርጅት ምንጩ የማይታወቀውን ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ህጋዊ የገቢ ምንጩ ምን እንደሆነ በጥንቃቄ የሚታይ ስለሆነ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አፍርቷል ብሎ ለመጠርጠር የአንድን ግለሰብ ሙሉ ፋይናንሻል ፕሮፋይል መስራት በተለይም በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት መለየት አስፈላጊ በመሆኑ በሂደቱ ከፍተኛ የሆነውን የገንዘብ እንቅስቃሴውን በማየት የሚወሰን እንጂ አንድ/ጥቂት የሆነን የገንዘብ እንቅስቃሴን ብቻ በማየት የሚወሰን አይደለም፡፡

4. ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ኃላፊነት የመብት መጠበቂያ መንገድ የተቀመጡለት መሆኑን መመልከት ይቻላል፡፡ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ኃላፊነትን በተመለከተ የመብት መጠበቂያ መንገድ የተቀመጡለት ስለመሆኑ በአወጁ በግልፅ የተደነገገ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

4.1. የመብት መጠበቂያ፡- ጉዳዩ ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት ተጠርጣሪው ስለንብረቱ ህጋዊ ምንጭ ለዐቃቤ ህግ/ለሀብት መርማሪ የማስረዳት መብት የሚሰጥ መሆኑ እና ነፃና ገለልተኛ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጪነት የሚካተት መሆኑ እንዲሁም ከዚህ በተጨማሪ የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሠው የንብረት ምንጩን ለማስረዳት በራሱ ላይ የወንጀል ኃላፊነት የሚያመጣበት ማስረጃ ቢሰጥም በወንጀል ችሎት ላይ ማስረጃ ሆኖ እንዳይቀርብ በማድረግ የመብት ጥበቃን ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም የታወቀ መረጃን አጠቃቀም እና ለሶስተኛ ወገን ይህን መረጃ ስለማሳወቅ የሚመለከት ገደብ መኖሩ፣ የቅን ልቦና ገዢዎችን መብት ያከበረ መሆኑ እና ዝቅተኛው የንብረት ዋጋ ግምት መነሻ (10,000,000) የልዩነት ዋጋ (ጠቅላላ ሀብት ሳይሆን) ተደርጎ መቀመጡ ይጠቀሳሉ፡፡

4.2. ተቋማዊ ጥበቃ፡- ገለልተኛ የሆነ ቁጥጥር እና በዳኝኘት አካል ወይም በዳኛ የሚወሰን ጉዳይ ነው፡፡

4.3 ተግባራዊ ጥበቃዎች፡- ፍትሃዊ ሂደት እና ሥነ-ስርዓት በተለይም ምርመራ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅና ያለው በጊዜ የተገደበ፣ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ መሆን ይገባዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
"የተቋማት መልካም ተሞክሮ ቅኝት"

*******

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በተቋማት ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል ሰፊ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ከዚህም ባሻገር በአገርዓቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የሙስና ትግል ያለኅብረተሰብ ተሳትፎ ከግብ ማድረስ ስለማይቻል ትግሉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የብሔራዊ ሙስና መጠቆሚያ ዲጂታል መተግበሪያ ስርዓት /National Corruption Reporting System – NCRS/ በመዘርጋት ዜጎች በየተቋማቱ አገልግሎት ለማግኘት ሄደው የሙስና ተግባር ሲያጋጥማቸው ያለምንም ሥጋት በስልካቸው ጥቆማ የሚሰጡበት ሥርዓት ዘርግቶ መረጃዎችን እየተቀበለ ይገኛል፡፡

ከኮሚሽኑ ባሻገር ተቋማት የሙስና ወንጀሎችን በተለያዩ አማራጮች ከህብረተሰቡ እየተቀበሉና መፍትሄ እየሰጡ ነው፡፡ ለአብነት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሙስና ወንጀል መቀበያ ስርዓት https://eeuethics.et/ በመዘረጋት ጥቆማዎችን በመቀበል ለመረጃዎች መፍትሄ እየሰጠ መሆኑ በመልካም ተሞክሮ የሚወሰድ ነው፡፡

ሌሎችም ተቋማትም በተመሳሳይ የራሳቸውን የሙስና ወንጀል መቀበያ ስርዓት በመዘርጋት ስራዎችን እየተገበሩ ከሆነ መልካም ተሞክሮ ስለሚሆን በኮሚሽኑ የማህበራዊ ሚዲያ መልዕክት መቀበያ ላይ እንዲያስቀምጡልን ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319