Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የኮሚሽናችን አሠራር በማዘመንና ከእጅ ንክኪ ነፃ በማድረግ ለሙስና እና ብልሹ አሠራር ተጋላጭ እንዳይሆን የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - አቶ አዘዘው ጫኔ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች ሙስና በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ በሚል መሪ ሀሳብ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በስልጠናው የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ ስልጠናው ከተቋማችን አመራርና ሠራተኛች ባሻገር ለባለድርሻ አካላት ጠቃሚ በመሆኑ በተከታታይነት የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ በባህሪው ለሙስና እና ብልሹ አሠራር ተጋላጭ በመሆኑ አመራሩና ሠራተኛው በሥነምግባሩ አርዓያ እንዲሆንና ብልሹ አሠራርን አምርሮ እንዲታገል የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ተቋማችን ሥነምግባርን ከመገንባትና ሙስናን ከመከላከል አንፃር ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋርም ትኩረት በመስጠት እተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኮሚሽናችን አሠራር በማዘመንና ከእጅ ንክኪ ነፃ በማድረግ ለሙስና እና ብልሹ አሠራር ተጋላጭ እንዳይሆን የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልዋል፡፡

ለሁለት ቀናት የስልጠና ቆይታችሁ ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መልኩ ስልጠናውን መከታተል አልባችሁ ብለዋል፡፡

የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ስልጠናው በዘርፉ የሙስና እና ብልሹ አሠራር ተጋላጭትን ጥናት ላይ በተለዩ ችግሮች መነሻነት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

ተቋሙ ለሙስና እና ብልሹ አሠራር ተጋላጭነቱ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ አመራሩና ሠራተኛው በኮሚሽኑ ላይ የሚስተዋሉ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በጥናት በመለየት ቀዳዳዎችን መድፈን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኛ በአገርዓቀፍ ደረጃ ኮንትሮባንድ እንዳይበራከት የራሱን አስተዋፅኦ መወጣት አለበት፤ በተለይ ከመድሃኒት ጋር የሚስተዋሉ የኮንትሮባንድ ብልሹ አሠራሮች በዜጎች ህይዎት ላይ የሚደርሰውን ችግር በመረዳት በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር የራሳቸውን ኔትወርክ በመዘርጋት ሙስና እና ብልሹ አሰራር በሚሰሩ ግለሰቦች ላይ ክትትል በማድረግ የማያዳገም የዕርምት እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ስልጠናው በዶ/ር አወቀ አሸናፊ እና በዶ/ር የሱፍ ኢብራሒም እየተሰጠ ሲሆን፤ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319