Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የተቋማትን አሠራር ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በማስፈን ለሀገር ልማትና ብልፅግና ፀር የሆነውን የሙስና ወንጀል ለመከላከል በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 7/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የጋምቤላ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለማጃንግ ዞን እና ለጎደሬ ወረዳ አመራር፣ ለግዥና ፋይናንስ እና ለፍትህ ዘርፍ አመራሮች እንዲሁም ለሥነምግባር መኮነኖች በስ ሥራ ላይ ሥነምግባር፣ ግዥና ሙስና በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናው የተገኙት የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትህትና ቢኒያም ሙስና ቀይ መስመር መሆኑ አንደ ፓርቲና መንግስት አቅጣጫ የተቀመጠበት በመሆኑ አመራሩ ተጠያቂነት እንደማይቀር በማመን ከሙስና እና ኢ-ሥነምግባራዊነት ራሱን እንዲያርቅና እጁን ከመሰብሰቡ ባሻገር ትክክልኛ ሀብቱን እንዲያስመዘግብ አሳስበዋል።

እንደ ዞንም ሆነ እንደ ወረዳ ያለውን ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ የመሬት አያያዝና ልማት እንዲሁም የመንግስት በጀት አጠቃቀም ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳ ለማድረግና በፍትሃዊነት ለመጠቀም የአመራሩና ባለሙያው አቅም በማብቃት ያሉብንን የአሠራር ክፍተቶች ለመሙላት፣ መመሪያ እንዲተገበር ለማስቻል እንዲህ ያሉ ስልጠናዎች አስፈላጊ በመሆናቸው ቀጣይነት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።

የክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና መከላከል ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አዲሱ ታደሰ በበኩላቸው የስልጠናው ዋና ዓላማ በመንግሥት መ/ቤቶችም ሆነ በልማት ድርጅቶች የአሰራር ብልሽቶች ሊያስከትሉ የሚችሉ ክፍተቶች በመለየት የግንዛቤ መፍጠሪያ ሥራዎች በማጠናከር ሙስናንን አስቀድሞ መከላከል ትኩረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራሮች በመንግስትና በህዝብ ሀብት የሚፈፀሙ ወንጀሎች በመሆናቸው ሁሉም ዜጋ በቁርጠኝነት ሊታገላቸው እንደሚገባም አሳስበዋል ።

የኮሚሽኑ የሙስና ወንጀል መከላከል ዳይሬክተር ወ/ሮ መሠረት ሙሉቀን፥ ኮሚሽኑ ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንዲቻል ሥልጠናዎችን ማዘጋጀትና ትምህርት መሥጠት መሆኑን ገልፀው፥ ጠቃሜታው ጉልህ እንደሆነ አመላክተዋል።

ስለሆነም የተቋማትን አሰራር ግልፅና ተጠያቂነት ያለበት ለማድረግ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች እንዲሟሉ ማድረግ ይገባል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ወ/ሮ መሠረት አክለውም ለዕድገትና ብልፅግና ተግዳሮት የሆነውን የሙስና ወንጀልን ለመከላከል የባለድርሻ አካላትንና የዜጎችን ንቁ ተሳትፎ የሚጠይቅ ሥራ በመሆኑ በትብብር እንድንሠራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኮሚሽኑ በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ እያካሄደ መሆኑን ገለፀ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ውይይቱ በሀገሪቱ የሚከሰቱ የሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ያለመ መሆኑን ተመላክቷል።

በወቅቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሶፈንያስ ደስታ ሙስና ሀገርን የሚያወድም አደገኛ በሽታ ነዉ ብለዋል።

በሙስና የሚከሰቱ ችግሮች በጊዜ ካልተቀረፈ በሀገሪቱ የሚፈለገውን ልማት ማስመዝገብ እንደማይቻል ገልፀው፣ ለዚህም በትውልድ ላይ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በትውልድ ላይ ሥነምግባር ማስተማር ይገባል ያሉት አቶ ሶፈንያስ፣ የክልሉ ኮሚሽንም ትውልድን በሥነምግባር ለማነጽ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ለውይይቱ መነሻ የሚሆን በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ ቀርቦ ዉይይት የሚደረግ ይሆናል።

በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ እንደሆኑም ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319