Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ሰነድን አስመስሎ ጊዜዉ ያለፈበትን የጸረ-ወባ ኬሚካል ሲሰበስቡ በነበሩ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ ተላለፈ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ህግ መንግስታዊ ሰነድን አስመስሎ ጊዜው ያለፈበትን የፀረ-ወባ ኬሚካል ሲሰበስቡ በነበሩ ተከሳሾች ላይ በመሰረተዉ የወንጀል ክስ የጥፋተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ መሰጠቱን አስታውቋል።

ውሳኔ የተሰጠው ለክልሉ ፍትሕ ቢሮ እና ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በደረሰዉ የወንጀል ጥቆማ መነሻ በተጠርጣሪዎች 1ኛ ምንአሉ አበበ፣ 2ኛ ሰይፉ ጋሊ እና 3ኛ ተመስገን መና በተባሉ ግለሰቦች ላይ የወንጀል ምርመራ በማጣራት የክልሉ ዐቃቤ ህግም የደረሰዉን የምርመራ መዝገብ በመቀበል ከላይ በተጠቀሱ ተካሳሾች ላይ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመሰረተዉ ክስ መሆኑ ተገልጿል።

ክሱ የተመሠረተው ሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 881/2007 በመተላለፍ በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል የሙስና ወንጀል እና የፀረ-ተባይ ምዝገባና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 674/2002 በመተላለፍ በፈጸሙት ወንጀል ነው።

ተከሳሾች ጊዜዉ ያለፈበትን የፀረ-ወባ ኬሚካል እንዲሰበስቡ ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር የተጻፈ መንግስታዊ ሰነድ በማስመሰል ለክልሉ ጤና ቢሮ ይዞ በመቅረብ ቢሮዉንም ህጋዊ ሰነድ ይዘዉ የቀረቡ በማስመሰልና በማሳሳት የድጋፍ ደብዳቤ በክልሉ ለሚገኙ ስድስድቱም ዞኖች ጊዜዉ ያለፈበትን የፀረ-ወባ ኬሚካል እንዲሰበስቡ የሚል ደብዳቤ ካጻፉ በኃላ ከኮንታ ዞን 76 ኩንታል እና 33 ኬረጢት የፀረ-ወባ ኬሚካል ጭነዉ መዉሰዳቸው በክሱ ተዘርዝሯል።

በተጨማሪም ከሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የፀረ-ወባ ኬሚካል ለመዉሰድ ኮድ አ.አ-3 -B- 57075 በሆነዉ አይሱዙ መኪና በመጫን ሂደት ላይ እያሉ ከፌዴራል ጤና ተቋማት ተጻፉ የተባሉ ደብዳቤዎች ሀሰተኛ በመሆናቸው የክልሉ ዐቃቤ ህግ ክስ መመስረቱ ተገልጿል።

ክሱ በሰዉና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መቅረቡንና ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ተከሳሾች በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበባቸዉን የወንጀል ድርጊት ማስተባበል ባለመቻላቸዉ በቀን 04/07/2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ መሰጠቱን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ገልጿል።

በዚሁ መሠረት በ1ኛ እና በ2ኛ ተከሳሾች ላይ 5 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና በብር 10,000 እንዲቀጡ እንዲሁም 3ኛ ተከሳሽ በ 2 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 3,000 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ በማስወሰንና ለወንጀል ድርጊት ማስፈጸሚ የተገለገሉበት ኮድ አአ-3 –B- 57075 የሆነዉ የአይሱዙ የጭነት መኪና ዉርስ እንዲሆን መወሰኑን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አሳውቋል።

በመሆኑም መሠል ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ሲመለከቱ ህብረተሰቡ በዜጐች ላይ የጤና ጉዳትና በሀገር ላይ ኪሳራ ከመድረሱ በፊት ህጎወጦችን ለህግ አካላት በመጠቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቢሮው ጥሪ ማስተላለፋን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ሀሳብ ለትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት አመራሮች ስልጠና ተሰጥቷል

********

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ሀሳብ ለትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት አመራሮች የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናው ሙስና እና ብልሹ አሰራር በሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚያስከትለውን አስከፊ ጉዳት ለድርጅቱ አመራሮች ግንዛቤ በማስጨበጥ ከተቋማቸው አልፈው ሀገራቸውን እንዲከላከሉ ለማስቻል ያለመ ነው።

በድርጅቱ ላይ የሚከሰቱ ሙስና እና የሙስና መከላከያ ስልቶች ላይ ትኩረት ያደረግው ስልጠና በዶ/ር አቢ ለማ ለሁለት ቀናት የተሰጠ ሲሆን፥ በቀጣይም ለድርጅቱ ሠራተኞች የሚሰጥ ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስናን መዋጋት የሚችል የተቋም ሠራተኛን በማፍራት የተጣለብንን ሀገራዊ ተልዕኮዎች ማሳካት ይጠበቅብናል - ኮ/ል ስለሺ ነገራ

********

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 6/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ በመከላከያ ዘርፍ ለመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለየሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አመራርና ሠራተኞች ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚወሰዱ መከላከያ ስልቶች ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት ሥልጠና በአምቦ ከተማ ተሰጥቷል፡፡

በመክፈቻ ንግግር ስልጠናውን ያስጀመሩት የሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮ/ል ስለሺ ነገራ ሙስናን መዋጋት የሚችል የተቋም ሠራተኛን በማፍራት የተጣለብንን ሀገራዊ ተልዕኮዎች ማሳካት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ስልጠናውን የሰጡት ሻ/ቃ ኤፍሬም ተሸመ በበኩላቸው የሙስና ወንጀል ዓይነቶችን ጠንቅቆ በማወቅ ራስን ብሎም ሃገርን ከሙስና ስጋት መጠበቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ”ሙስና የሀገርን እድገት የሚያቀጭጭ የዜጎችን የማደግ ዕድል የሚገታ አደገኛ ወንጀል በመሆኑ ሁሉም ዜጋ የመታገል ኃላፊነት አለበት ብለዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኢትዮጵያ ለጀመረችውና መድረስ ለምታስበው የለውጥ ጉዞ እንቅፋት የሆነውን ሙስና በጋራ ልንታገለው ይገባል - ወ/ሮ አየለች እሸቴ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 6/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በትምህርት ዘርፍ ባጠናው የሙስና ተጋላጭነት ሥጋት ጥናት ዙሪያ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዷል።

በመድረኩ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ኢትዮጵያ ለጀመረችውና መድረስ ለምታስበው የለውጥ ጉዞ እንቅፋት የሆነውን ሙስና በጋራ መታገል ያስፈልጋል።

በተለይ የትምህርት ዘርፉ ትውልዱን በመልካም ሥነምግባር የመቅረፅና ሙስናን የመከላከል ኃላፊነት አለበት ብለዋል።

ሚኒስትር ዴታዋ አክለውም ዘርፉ ትውልድን በሥነምግባር ከመገንባት አኳያ የአንበሳውን ድርሻ የሚወጣ ተቋም መሆኑን ጠቁመው፥ ለዚህም ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ የግብረገብነት ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አመራሩ በጥናቱ የተለዩ የብልሹ አሠራር አዝማሚያዎችን የእቅድ አካል በማድረግ ቀዳዳዎችን መድፈን እንደሚገባ ገልፀው፥ ችግሩን ለመቅረፍም ከኮሚሽኑ ጋር በትብብርና ቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ በበኩላቸው በትምህርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥርዓት ማበጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ሙስና እንደ ሀገር የልማት ግቦችን ለማሳካት ግንባር ቀደም ማነቆ በመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው ዘርፍ ተኮር የሙስና መከላከል ጥናት ተቋማት ያሉባቸውን ክፍተቶች በማሳየት በየደረጃው ያለው አመራር ችግሩን በማወቅ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራና ሙስና ከመፈፀሙ በፊት ለመከላከል ያግዛል ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል የሚቻለው መብቱን በገንዘብ የማይገዛ ማህበረሰብ ስንፈጥር ነው፥ ለዚህም የትምህርት ዘርፍ ትውልዱን በሥነምግባር ማነፅ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በቀጣይም በትምህርት ዘርፍ የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ እንደሚሰራ ጠቁመው፥ አመራሩም ለውጤታማነቱ በግንባር ቀደምትነት አርዓያ በመሆን የማስመዝገብ ሥራውን በኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

የኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ጥናት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው በትምህርት ዘርፍ የሙስና ተጋላጭነት ጥናትና የአመራሩ ሚና በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የጥናት ሪፖርት አቅርበው ተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት በማንሳት ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታዎችና አመራሮች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት አመራሮች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶችና አመራሮች እንዲሁም የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319