ፍርድ ቤቱ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ
******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞ የከተማዋ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳለፈ።
የከተማዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሌሎች ተከሳሾች ላይም የቅጣት ውሳኔውን አሳልፏል።
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ወንጀሉን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 17 ንዑስ 2 እና አንቀጽ 9 ንዑስ 2 በተደነገገው መሰረት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው።
በዚህም አንደኛ ተከሳሽ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጸጋዬ ቱኬ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ በመባላቸው የ13 ዓመት ጽኑ እስራትና የ21 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል።
ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ተሰማ ዳንጉሼ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል የሦስት ዓመት ጽኑ እስራትና 1 ሺህ ብር የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
በተጨማሪም ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ታሪኩ ታመነ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል 10 ዓመት ጽኑ እስራትና 41ሺህ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ አቶ ታፈሰ ቱናሻ እና 5ኛ ተከሳሽ አቶ ሰይፉ ዴሊሳ እያንዳንዳቸው በስምንት ዓመት ጽኑ እስራትና በቅደም ተከተላቸው 51 እና 76 ሺህ ብር እንዲቀጡ የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቷል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ያለንን ውስን ሀብት በአግባቡና ከሙስና በጸዳ መልኩ መጠቀም ይገባል - አቶ ተስፋዬ ወርቁ
************************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ለጤና ዘርፍ ሠራተኞች የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ለ3ኛ ዙር እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናው የተገኙት የጤና መድህን ዋና ዳሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ ያለንን ውስን ሀብት በአግባቡና ከሙስና በጸዳ መልኩ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።
በጤና ሚኒስቴር የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሻምበል ነጋሲ በበኩላቸው ሙስና ብዙ ትርጉም ያለው እና መጠነ ሰፊ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ በጋራ ልንታገለው ይገባል ብለዋል።
ስልጠናው በረዳት ፕሮፌሰር አብዱልሀኪም አባሜጫ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ለፋይናንስ ዘርፍ ሠራተኞች ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ በሚል መሪ ሀሳብ ስልጠና እየተሰጠ ነው
************************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ለፋይናንስ ዘርፍ ሠራተኞች የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በመክፈቻ ንግግር ስልጠናውን ያስጀመሩት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሀና በርሄ ሁሉም ሠራተኛ ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታውን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል።
ስልጠናው በኮሚሽኑ የሥልጠና ጥራትና ተገቢነት ዴስክ ኃላፊ በአቶ የኋላሸት ደሳለኝ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

የትምህርት ዘርፉ አመራሮች በሥነምግባራችን አርዓያ መሆን ከቻልን ሀገር እናሻግራለን - ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ
************************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ሀሳብ ለትምህርት ዘርፍ አመራሮች የሥነምግባርና ሙስና መከላከል ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናው የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ትምህርት የትውልድ ሥነምግባርን ለመቅረፅ ቁልፍ መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡
ግብረ-ገብነትን በካሪኩለም በማካተት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ በትምህርት እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑን ገልፀው፤ ይህም ሀገሩን የሚወድና በሥነምግባሩ የታነፀ ትውልድ ለማፍራት አይነተኛ መሳሪያ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በትምህርት ዘርፉ የጀመርናቸውን የቴክኖሎጂ ሥርዓቶች አጠናክረን በማስቀጠል ሀሰተኛ የትምህርት መረጃንና ኩረጃን ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡
አመራሩ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በጥናት በመለየት ቀዳዳዎችን መድፈን እንደሚገባ ገልፀው፤ ችግሩን የእቅዳችን አንድ አካል በማድረግ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ዘርፉ አመራሮች በሥነምግባራችን አርዓያ መሆን ከቻልን ሀገር እናሻግራለን ያሉት ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ፣ በሥነምግባር አርዓያ በመሆንና ተቋማችንን አውቀን ከመራን ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመቀነስ አያቅተንም ብለዋል፡፡
የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ስልጠናው በትምህርት ዘርፍ ያለውን የሙስና ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ትምህርት ለአንድ አገር እድገት የመሠረት ድጋይ መሆኑን ገልፀው፤ ለዚህም የትምህርት ዘርፉ ትውልድን በማነፅና ዜጋን በመቅረፅ ረገድ ግንባር ቀደም ነው ብለዋል፡፡
ሙስና እና ብልሹ አሰራር የአስተሳሰብ መበላሸት እና የማህበራዊ እሴቶች መሸርሸር ውጤት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አመራሩ ከተማሪዎች ምግብ አቅርቦት፣ የትምህርት ቁሳቁስ ግዥ፣ ከቴክኖሎጂና የምርምር አቅርቦት እና ከፕሮጀክቶች እርክክብ እንዲሁም የሙያ ብቃት እድሳትና ስረዛ ጋር የሚስተዋሉትን ብልሹ አሠራሮች የመከላከል ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
ከሀሰተኛ ትምህርት አሰጣጥና ኩረጃ እንዲሁም ለተማሪዎች ያለአግባብ ውጤት ከመስጠት አኳያ ችግሮችን በመለየት መፍታት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡
ስልጠናው በፕሮፌሰር አለማየሁ ተ/ማሪያም እና በዶ/ር አቢ ለማ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።