Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የአገልግሎት አሰጣጡን ከሙስና እና ብልሹ አሠራር ለመከላከል ቅንጅታዊ አሠራር ላይ በትኩረት ይሰራል - አቶ አበበ ከበደ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ከክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለኤጀንሲው አመራርና ሠራተኞች በሙስና ፅንሰ ሀሳብና በመልካም አስተዳደር መርሆዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው የተገኙት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ ከበደ ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃው የሚሰጡ አገልግሎቶች ከሙስና እና ብልሹ አሰራር ለማፅዳት ከሚመለከታቸው የህግ አካላት ጋር የተጀመረው ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ኤጀንሲው ባለፉት ወራት ከስር መዋቅሮች ባደረገው የጋራ እንቅስቃሴ በርካታ አካላት በህግ እንዲጠየቁ መደረጉን ገልፀው፥ ሙስናን መከላከል ከራስ ስለሚጀምር ሠራተኛው ራሱን ለለውጥ በማዘጋጀት የሪፎርም ስራዎች አተገባበር ላይ በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኤጀንሲው ም/ዳይሬክተር አቶ በድሩ ሀሰን በበኩላቸው ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሁሉም የትግሉ አካል ሊሆን እንደሚገባው ጠቁመው፥ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በየዳይሬክቶሬቶች በጥንቃቄ ሊተገበሩ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ ከኤጀንሲው ተግባር ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያለው በመሆኑ በቂ እውቀት ማግኘታቸውን ሰልጣኞች ገልፀው፥ ተጨማሪ ማብራሪያ በሚያስፈልጋቸው ነጥቦች ዙሪያ ጥያቄና አስተያየቶችን አቅርበዋል።

ለቀረቡት ጥያቄዎች በክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከል አማካሪ አቶ ደመቀ ታደሰ እና በክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፍትህአወቅ ፋንታሁን ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በሀሰተኛ ሰነድ ለመገልግል የሞከረች ግለሰብ በቁጥጥር ማዋሉን ኤጀንሲው አስታወቀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሀሰተኛ መሸኛ የተዘጋጀ መታወቂያና ልደት ሰርትፍኬት በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የሞከረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

በኤጀንሲው የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ዳ/ዳይሬክተር ወ/ሮ አስናቀች ሙህየ መጋቢት 3/2017 ዓ.ም በሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በየካ ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም በሀሰተኛ መሸኛ የተዘጋጀ መታወቂያና ልደት ሰርትፍኬት በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የሞከረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ተናግረዋል፡፡

ግለሰቧን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው የሙስና ወንጀል መከላከል ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ከኤጀንሲው የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ፍርድ ቤቱ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞ የከተማዋ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳለፈ።

የከተማዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሌሎች ተከሳሾች ላይም የቅጣት ውሳኔውን አሳልፏል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ወንጀሉን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 17 ንዑስ 2 እና አንቀጽ 9 ንዑስ 2 በተደነገገው መሰረት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው።

በዚህም አንደኛ ተከሳሽ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጸጋዬ ቱኬ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ በመባላቸው የ13 ዓመት ጽኑ እስራትና የ21 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል።

ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ተሰማ ዳንጉሼ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል የሦስት ዓመት ጽኑ እስራትና 1 ሺህ ብር የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በተጨማሪም ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ታሪኩ ታመነ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል 10 ዓመት ጽኑ እስራትና 41ሺህ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ አቶ ታፈሰ ቱናሻ እና 5ኛ ተከሳሽ አቶ ሰይፉ ዴሊሳ እያንዳንዳቸው በስምንት ዓመት ጽኑ እስራትና በቅደም ተከተላቸው 51 እና 76 ሺህ ብር እንዲቀጡ የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ያለንን ውስን ሀብት በአግባቡና ከሙስና በጸዳ መልኩ መጠቀም ይገባል - አቶ ተስፋዬ ወርቁ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ለጤና ዘርፍ ሠራተኞች የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ለ3ኛ ዙር እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በስልጠናው የተገኙት የጤና መድህን ዋና ዳሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ ያለንን ውስን ሀብት በአግባቡና ከሙስና በጸዳ መልኩ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።

በጤና ሚኒስቴር የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሻምበል ነጋሲ በበኩላቸው ሙስና ብዙ ትርጉም ያለው እና መጠነ ሰፊ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ በጋራ ልንታገለው ይገባል ብለዋል።

ስልጠናው በረዳት ፕሮፌሰር አብዱልሀኪም አባሜጫ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለፋይናንስ ዘርፍ ሠራተኞች ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ በሚል መሪ ሀሳብ ስልጠና እየተሰጠ ነው

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ለፋይናንስ ዘርፍ ሠራተኞች የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በመክፈቻ ንግግር ስልጠናውን ያስጀመሩት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሀና በርሄ ሁሉም ሠራተኛ ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታውን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል።

ስልጠናው በኮሚሽኑ የሥልጠና ጥራትና ተገቢነት ዴስክ ኃላፊ በአቶ የኋላሸት ደሳለኝ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319