FastMereja.com
47.1K subscribers
4.12K photos
210 videos
5 files
558 links
Download Telegram
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ መቀሌ ገብቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች በመቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመቀሌ ከተማ ነዎሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የርዕሳነ መስተዳደሮቹ የመቀሌ ጉዞ ለትግራይ ክልል አጋርነታቸውን ለማሳየት እና በመልሶ ግንባታ ሂደት የድርሻውን ለማበርከት ዓላማ ያደረገ ነው።

@fastmereja
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ የሺጥላ በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገደሉ።

የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ግርማ የሺጥላ የተገደሉት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ተሳትፈው በመመለስ ላይ ሳሉ መሆኑ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፓርቲያቸው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በሆኑት በአቶ ግርማ የሺጥላ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን በጽህፈት ቤታቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል” በማለት፣ “በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው” በማለት ግድያውን አውግዘዋል።

ጨምረውም አቶ ግርማ ተወልደው ባደጉበት አካባቢ፣ “ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪ እና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልህ ማሳያ ነው” ብለዋል።

በገዢው የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ እና በአማራ ክልል ቅርንጫፉ ውስጥ ከፍተኛ አመራር በሆኑት በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ ለተፈጸመው ግድያ ተጠያቂው ማን እንደሆነ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው አቶ ግርማ የሺጥላ እና አብረዋቸው ይጓዙ በነበሩ ሰዎች ላይ ሲሆን፣ በሌሎቹ ላይ ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ቢቢሲ ከአማራ ክልል እና ከፌደራል መንግሥቱ የሚመለከታቸው አካላት ስለጥቃቱ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

ዘገባው የቢቢሲ ነው።

@fastmereja
ዛሬ ማለዳ በበና ፀማይ ወረዳ ሉቃ ቀበሌ የዘነበው ዝናብ በአካባቢው ጉዳት አድርሶአል።

ዝናቡ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ከመኖሪያ ቄያቸው ያፈናቀለ ሲሆን አንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከጂንካ ወደ አርባ ምንጭ ሲጓዝ የነበረውን መንገድ በማሳት ከመደበኛ መስመር ውጭ በመቆም ተሳፋሪዎች ያለምንም ችግር ለመትረፍ ችለዋል ሲል የደቡብ ኦሞ ኮሙኒኬሽን ነው የዘገበው።

@fastmereja
አረንጓዴው ጎርፍ በዛምቢያ
#FastMereja
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዛምቢያ ንዶላ በተካሄዱ የታዳጊዎች እና የወጣቶች አትሌቲክስ ውድድሮች በመጀመሪያው ቀን ድል አድርገዋል።

በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች ከ20 ዓመት በታች በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በዚህም አትሌት አስማረች አንለይ በአንደኝነት የወርቅ ሜዳሊያ ስታጠልቅ፣ አትሌት የኔዋ ንብረት 2ኛ በመሆን የብር እንዲሁም አትሌት ዓይናዲስ መብራቱ በሦስተኝነት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

@fastmereja
ጀርመን ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰራተኞችን እንደምትፈልግ ገለጸች፡፡

የአውሮፓ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቷ ጀርመን የሰለጠኙ ሰራተኞችን እንደምትፈልግ ያስታወቀች ሲሆን እጥረቱን ለመፍታት የስደተኞችን ፖሊስ እስከ ማሻሻል እንደምትደርስ አስታውቃለች፡፡

የሚሻሻለው የስደተኞች ፖሊሲም ሀገሪቱ የገጠማትን የሰራተኞች እጥረት በአጭር ጊዜ መፍታት እንደሚያስችላት የጀርመን የሰራተኞች እና የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

እንደ ዶቸቬለ ዘገባ ከሆነ ለዚህ የሚረዳ ረቂቅ ህግ ተዘጋጅቶ ለሀገሪቱ ካቢኔ የቀረበ ሲሆን ህጉ እንዲጸድቅ ለሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት ተልኳል፡፡
በዚህ ረቂቅ ህግ መሰረት ጀርመን ከአውሮፓ ውጪ ካሉ ሀገራት በዓት 60 ሺህ ሰራተኞችን ወደ ሀገሯ ለማስገባት ያስችላታል ተብሏል፡፡

ጀርመንኛ የስራ ቋንቋ መቻል፣ የስራ ልምድ፣ ከጀርመን ጋር ያለ ነባር ግንኙነት እና እድሜ ዋነኛ መመልመያ መስፈርቶች እንደሆኑ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የጀርመን ሰራተኞች ሚኒስትር ሁበርተስ ሄይል ከመመለመያ መስፈርቶቹ ውስጥ ሶስቱን ያሟላ ወደ ጀርመን እንዲገባ ሊፈቀድ እንደሚችል መናገራቸው ተገልጿል፡፡

ወጣት ጀርመናዊያን ቅንጡ የስራ ከባቢ መፈለግ፣ የሙያ ስራ ዘርፎች ላይ የመሰማራት ፍላጎት ማጣት እና ከፍተኛ ክፍያ መጠየቅ ለጀርመን ኢንዱስትሪዎች ዋነኛ ፈተና መሆኑንም ነው ኒስትሩ የገለጹት።

አሁን ላይ ጀርመን የክህሎት ወይም ተግባር ሙያ ስራ ዘርፎች፣ የማህበረሰብ እንክብካቤ፣ የአረጋዊያን ጤና እና ትምህርት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ የሰራተኞች እጥረት ገጥሟታልም ተብሏል፡፡

የብረት እና ኤሌክትሪካል ሙያ ዘርፎችም ከፍተኛ የሰራተኛ እጥረት የገጠማቸው ዘርፎች ሲሆኑ የሰው ሀይል እጥረቱ በኢኮኖሚው ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ችግሩን መፍታት እንደሚያስፈልግ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡
አል ዐይን ነው የዘገበው።

@fastmereja
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለአገር አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ

ሪዞርቱ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ መጠናቀቁ ተገልጿል። በውስጡም ፕሬዝዳንታዊ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ዘመናዊ መኝታ ክፍሎች እና ሌሎች የመዝናኛ ስፍራዎችን የያዘ ነው።

ሪዞርቱ በተገነባበት ስፍራ የሚገኘው የጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ሰው ሰራሽ ሐይቅም በውሃ ላይ መዝናናት ለሚፈልጉ ጎብኝዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ሆኖ መዘጋጀቱን ኢዜአ ዘግቧል።

በተጨማሪም ቀደምት የዳውሮ ንጉስ ሃላላ የተገነባው የሃላላ ድንጋይ ካብ (ሃላላ ኬላ) ታሪካዊነቱን እንደጠበቀ በስፍራው ተጨማሪ የመስህብ አካል በመሆን ያገለግላል።

@fastmereja
የሚዲያ ባለሙያዉ ሰይፉ ፋንታሁን ፤ በድሬዳዋ ትራፊክ ፖሊስ ላይ በመቀለዱ ይቅርታ ጠየቀ

እዉቁ የቴሌቪዥን እና ራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጁ ሰይፉ ፋንታሁን ፤ በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ በድሬዳዋ ትራፊክ ፖሊስ ላይ በመቀለዱ ይቅርታ ጠይቋል። ሰይፉ ፤ በፕሮግራሙ ከተመልካቾች ተላከ ባለዉ እና ባቀረበዉ መልዕክት ነዉ የድሬዳዋ ፖሊስን ይቅርታ እንዲጠይቅ የተደረገዉ።

የፕሮግራም አዘጋጁ አግባብ የሌለዉና የከተማዋን ፖሊስ ስም ያጠፋ ተግባር መፈጸሙን የድሬዳዋ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነትና የለዉጥ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ገመቹ ታቻ ለዳጉ ጆርናል ተናግረዋል።

የከተማዉ ፖሊስ መምሪያ ተፈጽሞብኛል ያለዉን የስም ማጥፋት በሚመለከት ከግለሰቡ ጋር ከተነጋገረ በኋላ በትናንትናው እለት በነበረዉ ፕሮግራሙ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል ብለዋል ኮማንደር ገመቹ።

የከተማዉ ፖሊስ የአሰራርም ሆነ ሌሎች ለዉጦችን ማካሄዱን ኮማንደሩ ያነሱ ሲሆን ፤ ግለሰቡ በሚዲያ ያሰራጨዉ መልዕክት ቀልድ ብቻ ሳይሆን ስም ማጥፋት እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም ግለሰቡ በትናንትናው ፕሮግራሙ ይቅርታ መጠየቁን ፖሊስ መምሪያዉ ትልቅነት ነዉ በሚል መቀበሉን አክለዋል።

ኮማንደሩ በመልዕክታቸዉ ፤ የሚዲያ ሰዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በሚዲያዎች ላይ የሚያስተላልፉት መልዕክት ጥንቃቄ የተሞላዉ ሊሆን እንደሚገባ ጨምረው ለዳጉ ጆርናል ተናግረዋል።

Via: ዳጉ ጆርናል

@fastmereja
ዛሬም ድል ተመዝግበዋል
በዛሬው እለት ሚያዝያ 23/2015 ከ20 አመት በታች ሴቶች 3,000 ሜ መሰናክል ኢትዮጵያ ወርቅና ብር አግኝታለች!
🇪🇹 አለምናት ዋለ 1ኛ ወርቅ፣፣
🇪🇹 ፍሬህይወት ገሠሠ 2ኛ ብር፣

እስከአሁን
3 ወርቅ፣ 6 ብር፣ 3 ነሃስ፣
ድምር 12 ሜዳልያ

@fastmereja
መረጃ ለማግኘት የመጀመሪያ ምርጫችሁ የቱ ነው?
Anonymous Poll
7%
ቴሌቪዥን
5%
ሬዲዮ
2%
ጋዜጣ እና መፅሔት
86%
ማህበራዊ ሚዲያ
ለሶሰተኛ ሚስትነት ወጣቷን ከትምህርት ቤት የጠለፉት በቁጥጥር ስር ዋሉ!
#FastMereja
ከሰንበቴ ከተማ የተጠለፈቸው ወጣት በባቲ ከተማ አስ/ር ፖሊስና ሚሊሻ 3 ጠላፊዎችን ጨምሮ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተማሪ ሀምዲያ አህመድ ወሌ ትባላለች ሠንበቴ 04 ቀበሌ ነዋሪ ስትሆን በቀን 20/8/2015 ዓ/ም 1ኛ.አልይ አመድ ሙሴ፣ 2ኛ.አህመድ አደም፣ 3ኛ.አልይ አሜ መሀመድ የተባሉት ግለሠቦች በተራ ቁጥር 1 ለተጠቀሰው ግለሠብ ለአቶ አልይ አመድ ሙሴ 3ኛ ሚስት ለማድረግ በማሰብ ልጅቷን ከትምህርት ቤት በባጃጅ በመጥለፍ የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 አ.አ B23937 በሆነ መኪና በአዴሌላ ገዋኔ አዋሽ ሰባት ከደረሱ በሗላ ተመልሰው በሚሌ ባቲ ሲሄዱ የባቲ ከተማ አስ/ር ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት በጋራ በመሆን ልጅቷንና 3 ጠላፊ ግለሠቦችን ከነመኪናው በቁጥጥር ስር በማዋል ከሰንበቴ ከተማ አስ/ር ፖሊስ ማስረከብ ተችሏል ሲል ከባቲ ከተማ አስ/ር ፖሊስ ኮሚኒኬሺንና ሚዲያ ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja
FastMereja.com pinned «መረጃ ለማግኘት የመጀመሪያ ምርጫችሁ የቱ ነው?»
ሻሸመኔ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግን ተቀላቀለ!
#FastMereja
ሻሸመኔ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማን ሽንፈት ተከትሎ ከ15 የውድድር ዘመናት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መመለሱን አረጋግጧል! ሻሸመኔ ከተማ ለመጨረሻ ጊዜ በሀገሪቱ ትልቁ ሊግ ተሳትፎ ያደረገው በ2000 ሚድሮክ ሚሊኒየም ፕሪምየር ሊግ ላይ ነበር ሲል ሶከር ኢትዮጵያ ነው የዘገበው።

@fastmereja